አቶ ታዬ ደንዳአ እና እነ ዮሐንስ ቧያለው ቅሬታ እና መቃወሚያ ለፍርድ ቤት አቀረቡ

ከ 36 ደቂቃዎች በፊት በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ሲሰሙ፣ በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ስር ያሉ ተከሳሾች ደግሞ የክስ መቃወሚያቸውን አቀረቡ። ፀረ ሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት በሚል የተከሰሱት የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ታዬ ደንዳአ ላይ የዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮች ተሰምተዋል። ሐሙስ ግንቦት […]

የኢትዮጵያ ሠራዊት ከሶማሊያ መውጣት ለአልሻባብ የመጠናከር ዕድል ይፈጥራል?

ከ 5 ሰአት በፊት ሰኞ ታኅሣሥ 22/2016 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጽህፈት ቤት የወጣው ዜና በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ግንኙነት ላይ ትልቅ ለውጥ ያስከተለ ነበር። ምን አልባት በሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ታሪክ ውስጥ በጉልህ ከሚጠቀሱት ሊሆን ይችላል። ዜናው፣ ኢትዮጵያ ሶማሊያ ግዛቴ ከምትላት እና ራሷን ነጻ አገር ብላ ከወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ለመጠቀም የሚያሰችላትን የመግባቢያ […]

ሶማሊያ የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ተመረጠች

ከ 4 ሰአት በፊት ሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ተመረጠች። በጦርነት ስትታመስ ለኖረችው ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር የምክር ቤቱ አባል ሆና መመረጧ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ተደርጎ ተወስዶላታል። ሶማሊያ ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ከመግባቷ በፊት እአአ በ1970ዎቹ የምክር ቤቱ ተለዋጭ አባል ነበረች። ሶማሊያ የምክር ቤቱ አባል መሆኗ ከጽንፈኛው […]

እስራኤል ትምህርት ቤት ላይ ተኩሳ በርካታ ሕጻናት መገደላቸው ከተገለጸ በኋላ አሜሪካ በጥቃቱ ዙሪያ ግልጽነት እንዲኖር አሳሰበች

ከ 4 ሰአት በፊት ሐሙስ ማለዳ ተፈናቃዮች በተጠለሉበት የማዕከላዊ ጋዛ ትምህርት ቤት በርካታ ሕጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 35 ሰዎችን ተገድለውበታል ስለተባለው የአየር ጥቃት እስራኤል ሙሉ በሙሉ “ግልጽ” መሆን እንዳለባት አሜሪካ አሰሰበች። የአካባቢው ጋዜጠኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት አንድ የጦር አውሮፕላን በኑሴይራት ከተማ የስደተኞች መጠለያ በመሆን በሚያገለግለው ትምህርት ቤት የላይኛው ወለል ላይ በሚገኙ የመማሪያ ክፍሎች ላይ ሁለት ሚሳኤሎችን መተኮሱን […]

እስካሁን ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው ከልክ ያለፈ ውፍረትን የመለኪያ ዘዴ የተሳሳተ ነው ተባለ

ከ 5 ሰአት በፊት በሚሊዮን የሚቆጠሩ በመካከለኛ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች እጅግ ከልክ ያለፈ ውፍረት እንዳላቸው በስህተት እንዲያምኑ ተደርገዋል ሲል በጣሊያን የተካሄደ ጥናት ይፋ አደረገ። ጥናቱ ትኩረት ያደረገውም የሰውነት ክብደት ከቁመት አንጻር ሳይሆን በሰውነት ውስጥ በተካማጨ ስብ መጠን ላይ መሆኑን አመልክቷል። ይህ በስብ መጠን ላይ የሚያተኩረው ከልክ ያለፈ ውፍረትን የመለካት አካሄድ በውፍረት ማን እንደተጎዳ […]

በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተጠያቂ በተደረገበት የጀምላ ግድያ ቢያንስ 150 ተገደሉ

ከ 1 ሰአት በፊት በማዕከላዊ ሱዳን ከሀገሪቱ ጦር ጋር ውጊያ ላይ ያለው የሱዳን ፈጥኖ ዳራሽ ኃይል (አርኤስኤፍ) ተጠያቂ በተደረገበት የጅምላ ግድያ 35 ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 150 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተዘገበ። ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እና የሱዳን መንግሥት ጦር ሀገሪቱን ለመቆጣጠር የገቡበት ጦርነት 13ኛ ወሩን አስቆጥሯል። አርኤስኤፍ በቀረበበት ክስ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት ባይኖርም ትላንት የሀገሪቱን ጦር […]

The gospel’s good news for queer people — and their enemies  – Sojourners 

BY KATHERINE PATER JUN 6, 2024 Let’s get the awkward, middle-school sex-ed piece out of the way, shall we? In Acts 8, we hear the story of how Philip baptizes an Ethiopian eunuch. Dictionaries define a eunuch as a man who has been castrated, especially (in the past) one employed to guard the women’s living areas. […]

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰሩ እንዲፈቱ እና የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ ኢሰመኮ ጠየቀ

6 ሰኔ 2024, 07:08 EAT በአማራ ክልል ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ የታሰሩ እንዲፈቱ፣ መደበኛ ሕግ ተግባራዊ እንዲሆን እና የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ። ባለፈው ዓመት ማብቂያ አካባቢ በአማራ ክልል ያለው የፋኖ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ከአቅሙ በላይ መሆን በመግለጽ የአማራ ክልል መስተዳደር የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ ገብነት መጠየቁን ተከትሎ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተግባራዊነት […]

እነ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ‘ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር’ በመንቀሳቀስ ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

6 ሰኔ 2024, 14:38 EAT አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ የሆነችው ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 20 ግለሰቦች “ገንዘብ ለሽብር ቡድን ሎጂስቲክ መግዣ ለማዋል” እንዲሁም “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ ተጠርጥረው ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ […]

ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት እና ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር የሚነጋገር ቡድን ሰየመች

6 ሰኔ 2024, 14:12 EAT የቤተከርስቲያኗን ጉዳይ እና ፍላጎትን በተመለከተ ከመንግሥት እና ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር የሚገናኝ ቡድን ማዋቀሩን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ። ሲኖዶሱ ይህንን እና ሌሎች ውሳኔዎቹን ያሳወቀው ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም. ድረስ ሲያካሂደው የቆየው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫ ነው። በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ቤተክርስቲያኗ በአሁኑ […]