በሰሞኑ የሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን ግጭት የሰዎች ሕይወት ማለፉና በርካቶች መፈናቀላቸው ተሰማ

June 5, 2024 – DW Amharic  በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮ እና ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች ካለፈው ሳምንት ሀሙስ ጀምሮ እንደ አዲስ ተቀሰቀሰ በተባለው ግጭት ሰላማዊ ዜጎች ጭምር የግጭቱ ሰለባ እየሆኑ ነው ተባለ፡፡ በተለይም በአቤዶንጎሮ ወረዳ ጎልቶ ተስተውሏል በተባለው በዚሁ አዲስ ግጭት የሰዎች ህይወት ስለማለፉና ነዋሪዎችም መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የህወሓትን ሕጋዊ ሰውነት ሊመልስ የሚችል ሕግ ፀደቀ

June 5, 2024 – DW Amharic  አንድ የምክር ቤት አባል ማሻሻያው ህወሓትን ወደ ሕጋዊ መስመር ለመመለስ ያለመ፣ድርጅቱ አሁንም በአማራ እና አፋር ክልሎች ችግር እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ ማሻሻያውን ተቃውመዋል። ህወሓት በተለይ በአማራ ሕዝብ ላይ በማይካድራ፣ በራያ ቆቦ፣ በጭና ፣ በአጋምሳ፣ በኮምቦልቻ ፣ በጋሸና ፣ ሰሜን ሸዋ “በርካቶችን ጨፍጭፏል” ሲሉ ተቃውመዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ከአውሮጳ ኅብረት ፓርላማ ምርጫ ምን ይጠበቃል?

June 5, 2024 – DW Amharic ለአራት ቀናት በአውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራት የሚካሄደው ይህ ምርጫ ከቀድሞዎቹ የምክር ቤት ምርጫዎች በተለየ ትኩረት ስቧል። ውጤቱም አጓጊ ሆኗል። ምክንያቶቹም በተለይ ካለፉት አራትና ሦስት ዓመታት ወዲህ አውሮጳን ጨምሮ በዓለማችን የተከሰቱ ማኅበራዊ ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ለውጦች በምርጫው ውጤት ላይ ሊያሳድሩ የሚችሏቸው ተጽእኖዎች ናቸው ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ያደገው ዓለም የዘነጋው የቆዳ በሽታ «ቁንጭር»

June 5, 2024 – DW Amharic  በረሃማ አካባቢ በብዛት ያጋጥማል። ከደን መመናመን ጋር ተያይዞ ግን በአሁኑ ጊዜ ወትሮ በማይታይበት አካባቢም መከሰት ጀምሯል። በተለያየ አካባቢ አጠራሩ ቢለያይም ቁንጭር በመባል ይታወቃል። በመላው ዓለም በየዓመቱ ወደ 12 ሚሊየን ሰዎችን ያጠቃል የቆዳ በሽታ ነው። ያደገው ዓለም ግን ዘንግቶት ምርምር አያደርግበትም፤ መድኃኒትም አልተገኘለትም።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በተለያየ ጊዜ በለንደን ተጥለው የተገኙ 3 ጨቅላዎች እህትና ወንድም መሆናቸው ታወቀ፣ ፖሊስ ወላጆቻቸውን እየፈለገ ነው

ከ 23 ደቂቃዎች በፊት በተለያዩ ዓመታት ለንደን ከተማ ውስጥ መንገድ ላይ ተጥለው የተገኙ ጨቅላ ህጻናት የተመሳሳይ ወላጆች ያሏቸው በመሆናቸው እህት እና ወንድም እንደሆኑ በምርመራ ሲረጋገጥ፣ እናት እና አባታቸው በፖሊስ እየተፈለጉ ነው። ይህ ይፋ የሆነው ከቅርብ ወራት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ከተማ ውስጥ ተጥላ የተገኘች አንዲት ጨቅላ ከዚህ ቀደም ተጥለው የተገኙ ሁለት ልጆች እህት መሆኗ በተረጋገጠበት […]

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በረሃብ አፋፍ ላይ እንደሚገኙ ተመድ አስጠነቀቀ

ከ 5 ሰአት በፊት ከአንድ ዓመት ባለፈው የእርስ በእርስ ጦርነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሱዳናውያንን ለረሃብ አደጋ ማጋለጡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። በሱዳን መንግሥት ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል የሚደረገው ጦርነት ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሱዳናውያንን ከመኖሪያቸው ያፈናቀለ ሲሆን፣ ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝዝ ቀላል የማይባለው “ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ” ተጋልጧል ተብሏል። በጋዛ እና ዩክሬን እየተካሄዱ ባሉ ጦርነቶች ትኩረት የተነፈገው […]

ከታገዱበት ፓርቲ ጋር ለመጣመር እና ፕሬዝዳንት ለመሰየም ዕድል ያገኙት ጃኮብ ዙማ

ከ 5 ሰአት በፊት በአውሮፓውያኑ 2018 በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የሥልጣን ሽኩቻ ነበር። ይህንን ተከትሎ ሲርል ራማፎሳ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን ጃኮብ ዙማን ተክተዋል። ስድስት ዓመት ወደ ኋላ እንመለስ። የ82 ዓመቱ ጃኮብ ዙማ ከፕሬዝዳንትነታቸው ሲለቁ የፖለቲካ ሕይወታቸው ያበቃ መስሎ ነበር። ነገር ግን ያልታሰበው ሆነና አንሰራርተው አሁን ብቅ አሉ። ይህም ‘የዙማ ሱናሚ’ […]

ባይደን የአሜሪካን ድንበር የሚያቋርጡ ስደተኞች ለመገደብ አዲስ መመሪያ አስተላለፉ

ከ 4 ሰአት በፊት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሜክሲኮ የአሜሪካን ድንበር በማቋረጥ በአሜሪካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ቁጥር ለመገደብ የሚያስችል ትዕዛዝ አስተላለፉ። በሕገ-ወጥ መንገድ የአሜሪካን ድንበር እያቋረጡ ጥገኝነት የሚጠይቁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ጉዳይ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደርን ሲያስተች ቆይቷል። በአዲሱ ፕሬዝዳንታዊ መመሪያ መሠረት ባለስልጣናት ድንበር አቋርጠው የገቡ ሰዎች የጥገኝነት ጥያቄያቸው ሳይታይ ከአሜሪካ በኃይል እንዲያስወጡ ይፈቅድላቸዋል። ዋይት ሃውስ […]