በጋምቤላ ክልል በእርሻ ልማት የተሰማሩ የአሥር ኢንቨስተሮች ንብረት በሐራጅ ሊሸጥ መሆኑ ተሰማ

በተመስገን ተጋፋው April 21, 2024 ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ በጋምቤላ ክልል በእርሻ ልማት የተሰማሩ ከአሥር በላይ የሆኑ ኢንቨስተሮች ከልማት ባንክ የተበደሩትን ብድር መመለስ ባለመቻላቸው ባንኩ ንብረታቸውን በሐራጅ ሊሸጥባቸው መሆኑ ተሰማ፡፡ የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሎው አቡፕ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት ከ2014 እስከ 2015 ዓ.ም. ድረስ ክልሉ ላይ በነበረው የፀጥታ ችግር በርካታ ኢንቨስተሮች በታጣቂዎች ንብረታቸው ተወስዷል፡፡ […]

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታዳጊዎችን ጨምሮ አራት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

22 ሚያዚያ 2024, 13:46 EAT በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን፤ “ከምዕራብ ጉጂ ዞን መጥተዋል” የተባሉ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ታዳጊ ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች መገደላቸውን ጥቃቱ የተፈጸመበት ቆቦ ቀበሌ ሊቀመንበር እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። የኮሬ ዞን አስተዳደር ባወጣው መግለጫ “ለንጹሐን አርሶ አደሮች” ሞት ምክንያት ለሆነው ጥቃት “በምዕራብ ጉጂ ዞን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ እና ፀረ-ሰላም” ሲል […]

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች

22 ሚያዚያ 2024, 15:51 EAT ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ የተከለከሉ አበረታች መድኃኒቶችን ወስዳ በመገኘቷ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ መታገዷ ተገለጠ። የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው ተቋም ነው። ተቋሙ በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ሰሌዳው ላይ በለጠፈው መግለጫ አትሌቷ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ቅጣት ማስተላለፉን አሳውቋል። የዓለም አትሌቲክስ አካል የሆነው ይህ […]

ዩክሬን እና ሩሲያ ሱዳን ውስጥ በእጅ አዙር ጦርነት እያካሄዱ ነው?

22 ሚያዚያ 2024, 13:34 EAT መስከረም 2016 ዓ.ም. ላይ በማይገመት ቦታ፣ ጨርሶ ሊገመቱ በማይችሉ ሁለት መሪዎች መካከል ስብሰባ ተደረገ። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪ ከሱዳኑ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጋር በአየርላንድ በሚገኝ አየር ማረፊያ መገናኘታቸው ብዙዎችን አስደንቆ ነበር። ይህን የሁለቱን መሪዎች ውይይት በዩክሬን ጦር ውስጥ ያሉ የልዩ ኃይል አባላት እንዳመቻቹት ተገልጿል። ዜሌንስኪ በኒው ዮርክ የመንግሥታቱ […]

ከሦስት ቀናት በፊት በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳው እሳት እስካሁን አልጠፋም

22 ሚያዚያ 2024, 15:01 EAT በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከሦስት ቀናት በፊት [ሚያዚያ 10፣ 2016 ዓ.ም.] የተነሳው እሳት በቁጥጥር ሥር አለማዋሉን የክልሉ ባለሥልጣን ገለጹ። የክልሉ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አባይ መንግሥቴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እሳቱ ከተነሳበት ቀን ጀምሮ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና አመራሮች ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም እሳቱን […]

ለቻይና በመሰለል የተጠረጠሩ ሦስት ግለሰቦች ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

22 ሚያዚያ 2024, 15:12 EAT የጀርመን ባለሥልጣናት ሦስት ለቻይና ሲስልሉ ነበር ብለው የጠረጠሯቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ይፋ አደረጉ። ዋነኛው ተጠርጣሪ ቶማስ አር ለቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የደኅንነት መሥሪያ ቤት በመሰለል ተከሷል። የጀርመን ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ግለሰቡ ከጀመርን የጥናት እና ምርምር ድርጅቶች ጋር የሚሠራ ኩባንያ አለው። ተጠርጣሪዎቹ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ ምሥጢራዊ መረጃዎችን ሰብሰበዋል፤ በተለይ ደግሞ […]

የእስራኤል ወታደራዊ ደኅንነት ኃላፊ በሐማስ ጥቃት ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ

22 ሚያዚያ 2024, 13:02 EAT የእስራኤል ወታደራዊ ደኅንነት ኃላፊ ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. የፈጸመውን ጥቃት ቀድመው ባለማስቆማቸው ኃላፊነቱን ወስደው ከሥልጣናቸው ለቀቁ። የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የባለሥልጣኑን ተተኪ ከተመረጠ በኋላ ሜጀር ጄኔራል አሮን ሃሊቫ ጡረታ እንደሚወጡ አስታውቋል። የወታደራዊ ደኅንነት ኃላፊው “የተሰጠንን አደራ በአግባቡ አልተወጣንም” ሲሉ በሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸው አምነዋል። ሜጀር ጄኔራል አሮን ሃሊቫ በእስራኤል ታሪክ እጅግ አስከፊ […]

በሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ በማስነሳት የተጠረጠሩ ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ   – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር  

April 22, 2024 በናሆም አየለ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ባለፈው ሐሙስ የተቀሰቀሰውን የሰደድ እሳት፤ እስካሁን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር እንዳልተቻለ የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሳ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ለእሳት ቃጠሎው መንስኤ ሳይሆኑ አይቀሩም በሚል የተጠረጠሩ ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ገልጸዋል።  በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት […]

The Horn of Africa States: The Continuing Challenges – OpEd

Horn of Africa. Source: NASA  April 21, 2024  0 Comments By Dr. Suleiman Walhad If one were travelling across the globe today, one would notice that the world is sick and ailing and wherever one looks, one would find countries in crisis. The Europeans are busy fighting the Russians in a proxy war in Ukraine with the […]

በአማራና በትግራይ ክልሎች ያገረሸው የሰላም ዕጦት

የራያ አላማጣ አካባቢ ተፈጥሯዊ ገጽታ ፖለቲካ በዮናስ አማረ April 21, 2024 ያለፈው ሳምንት የተጀመረው በአወዛጋቢዎቹ የወልቃይትና የራያ አካባቢዎች ግጭት ስለመጀመሩ በሚጠቁሙ ወሬዎች ነበር፡፡ ሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. አማራና ትግራይ ክልሎች እንደገና ግጭት ውስጥ ስለመግባታቸው አንዳንድ መረጃዎች መነገር ጀመሩ፡፡ በማግሥቱ ማክሰኞ ዕለት ደግሞ የትግራይ ታጣቂዎች የአላማጣ ከተማን መቆጣጠራቸው ጭምር ይነገር ጀመር፡፡ ሁኔታውን አስመልክቶ ከመንግሥት […]