በሊቢያ የስደተኞች የጅምላ መቃብር መገኘቱን የመንግሥታቱ ድርጅት አስታወቀ

ከ 4 ሰአት በፊት ሊቢያ ውስጥ ቢያንስ የ65 ስደተኞችን አስከሬኖች ያያዘ የጅምላ መቃብር መገኘቱን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ። ስደተኞቹ የሞቱበትን ሁኔታ እና የየት አገር ዜጎች ስለመሆናቸው አስካሁን የታወቀ ነገር እንደሌለ ድርጅቱ ገልጾ፣ ነገር ግን በሊቢያ በረሃ በኩል ወደ ሜዲትራኒያን ባሕር በድብቅ ሲወሰዱ ሳይሞቱ እንደማይቀሩ ይታመናል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አንድ አካል የሆነው ዓለም አቀፉ […]

ታጣቂዎች በሞስኮ የሙዚቃ አዳራሽ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ 60 ሰዎች ተገደሉ

ከ 3 ሰአት በፊት ታጣቂዎች በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው ታዋቂው የክሮከስ አዳራሽ ላይ ተኩስ ከፍተው ቢያንስ 60 ሰዎች ሲገድሉ፣ 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። ቢያንስ አራት ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች የበርካቶችን ሕይወት በቀጠፈው ጥቃት ውስጥ መሳተፋቸውንም ቢቢሲ ያረጋገጠው ቪዲዮ ያሳያል። ክራስኖጎርክስ ተብሎ በሚታወቀው ስፍራ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሮክ የሙዚቃ ዝግጅት ሊቀርብ በነበረበትም ወቅት […]

‘ጭንቅ ውስጥ’ ነን የሚሉት ተማሪዎች ከንግድ ባንክ የወሰዱትን ገንዘብ ምን ላይ አዋሉት?

22 መጋቢት 2024 ከአንድ ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመውን የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት እክልን ተከትሎ ባንኩ እስካሁን ትክክለኛ መጠኑን ያልገለጸው ከፍተኛ ገንዘብ በደንበኞቹ ወጪ ተደርጎበታል። በባንኩ ላይ የተከሰተውን የሲስተም ብልሽት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞች የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ማውጣታቸው እና ማዘዋወራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከዚህ ጋር በተያያዘ ስማቸው ሲነሳ ቆይቷል። በአገሪቱ በሚገኙ […]

አሜሪካ ጋዛን አስመልክቶ ለተመድ ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ በሩሲያ እና ቻይና ውድቅ ተደረገ

ከ 2 ሰአት በፊት አሜሪካ የታጋቾችን መለቀቅ ከጋዛ ተኩስ አቁም ጋር በማያያዝ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ሩሲያ እና ቻይና ውድቅ አደረጉት። ሩሲያ እና ቻይና ይህንን የአሜሪካ የውሳኔ ሃሳብ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውንም በመጠቀም ነው ተቀባይነት እንደሌለው ያሳወቁት። ቀደም ሲል ሌሎች አገራት በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የተለያዩ የውሳኔ […]

ንጉሣዊውን አገዛዝ የገረሰሰው የኢራን እስላማዊ አብዮት ግቡን አሳካ ወይስ. . .?

ከ 4 ሰአት በፊት ኢራን የእስላማዊ አብዮቷን 45ኛ ዓመት እያከበረች ነው። በ1979* ለለውጥ የታገሉ ሰዎችም ሐሳባቸውን እየሰነዘሩ ነው። አንዳንዶች ቁጭት ላይ ናቸው፤ ሌሎች ደግሞ ኢራን ትክክለኛው መስመር ላይ ናት ብለው ያስባሉ። “ከ45 ዓመታት በፊት የትኛውም አብዮተኛ አንድ ቀን እንደ ወንጀለኛ እቆጠራለሁ ብሎ አያስብም” ይላሉ ሳዴግ ዚባካላም። በ1979 አብዮት ሲፋፋም ወደ ጎዳና ወጥተው ድምፃቸውን ካሰሙ በሚሊዮን […]

ችላ ተብለው በአሳሳቢ ደረጃ በመላው ዓለም እየተስፋፉ የመጡት የአባላዘር በሽታዎች

ከ 4 ሰአት በፊት እንደ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ በመላው ዓለም በየቀኑ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ይያዛሉ። ነገር ግን በትክክል በወሲብ የሚተላለፍ በሽታ ምንድን ነው? ዓይነቶቹ እና ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን? የአባላዘር በሽታ (በወሲብ የሚተላለፍ ኢንፌክሽን) ማለት በወሲባዊ ግንኙነት አማካይነት ከአንድ ሰው ወደ ሌላ የሚተላለፍ በሽታ ማለት […]

ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን የአሜሪካ ኩባንያ ትጥቅ እንዲያቀርብ መወሰኑን ፖለቲከኞች ተቃወሙ

ከ 3 ሰአት በፊት የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር ለአገሪቱ ብሔራዊ ቡድን ትጥቆችን ከሚያቀርበው ከአዲዳስ ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጦ ሌላ አቅራቢ በመለወጡ ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ተቃውሞ ገጠመው። የእግር ኳስ ማኅበሩ ለበርካታ ዓመታት ለብሔራዊ ቡድኑ ትጥቆችን ሲያቀርብ የነበረውን የጀርመን ኩባንያ አዲዳስን በመተው ከአውሮፓውያኑ 2027 ጀምሮ የአሜሪካው ናይኪ ትጥቆችን እንዲያቀርብ ተስማምቷል። ይህንን ውሳኔ ከተቃወሙት ውስጥ የአገሪቱ የምጣኔ ሀብት ሚኒስትር […]

Ethiopian official urges stronger cooperation with China

(Xinhua) 10:52, March 22, 2024 ADDIS ABABA, March 21 (Xinhua) — A senior Ethiopian government official has called for further augmenting Ethiopia-China cooperation through common platforms and initiatives. Ethiopia and China have enjoyed a longstanding relationship that spans over five decades, and there is a need “to enhance cooperation and foster enduring friendship between our two […]