የተባበሩት መንግሥታት ለጋዛ እርዳታ ማድረግ ያቆሙ አገራትን አወገዘ

ከ 9 ሰአት በፊት በጋዛ እርዳታ በማስተባበርና በማሰራጭት ከፍተኛ ሥራ የሚሠራው የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ (በእንግሊዝኛ ምሕጻሩ UNRWA) ለጋዛ ድጋፍ ያቆሙ አገራትን አወገዘ። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ውሳኔውን “አስደነጋጭ” ብለውታል። ይህ የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ ከ2 ሚሊዯን ለሚልቁ የጋዛ ነዋሪዎች ምግብና መጠለያን በዋናነት ሲያቀርብ ቆይቷል። አሁን ዋንኛ የገንዘብ ድጋፍ ለኤጀንሲ ይሰጡ የነበሩት ዩኬና ሌሎች የምዕራብ አገራት መለገስ አቆመዋል። […]

በአራን የሚደገፉት የሁቲ አማፂያን ለምን ከአሜሪካ እና አጋሮቿ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባትን መረጡ?

ከ 6 ሰአት በፊት ዩናይትድ ስቴትስ፣ አውስትራሊያ፣ ባሕሬን፣ ካናዳ እና ኔዘርላንድስ ጦራቸውን አጣምረው የሁቲ አማፂያንን ለመደምሰስ ቆርጠው ተነስተዋል። ነገር ግን ይህ ጦርነት በቀላሉ የሚወጡት እንዳልሆነ እሙን ነው። ኢራን በገንዘብ የምትደግፋቸው የሁቲ አማፂያን ካለፈው ኀዳር ወር ጀምሮ ቀይ ባሕርን አቋርጠው በሚጓዙ የንግድ መርከቦች ላይ ከ30 በላይ ጥቃቶች ሰንዝረዋል። የዩኤስ መከላከያ ባለሥልጣናት አማፂያኑን ሳንደመስስ አርፈን አንቀመጠም እያሉ […]

አላባማ የሞት ቅጣት የተፈደበትን ግለሰብ በናይትሮጂን የገለደችው ለምንድነው?

ከ 9 ሰአት በፊት የሞት ቅጣት የተፈረደበት ወንጀለኛ ከዚህ በፊት ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ ፍርዱ ተፈፅሞበታል። የአላባማ ባለሥልጣናት ይህን መሣሪያ መጠቀም የፈለጉት ለምን ይሆን? አከራካሪ የሆነውስ ለምንድነው? ኬኔት ዩጂን ስሚዝ መጀመሪያ የሞት ቅጣቱን እንዲቀበል የታቀደው መርዛማ በሆነ መድኃኒት ነበር። ቅጣቱ ደግሞ ኅዳር 2022 እንዲፈፀም ነበር ዕቅዱ። ነገር ግን ቅጣቱን እንዲፈፅሙ አደራ የተጣለባቸው ሙያተኞች በሁለት ገመድ መድኃኒቱን […]

ናይጄሪያ፡ የአባታቸውን ሕይወት ለማትረፍ የተዋጣ 70ሺህ ዶላር የዘረፉ ታሰሩ

28 ጥር 2024, 09:31 EAT የዝነኛው ናይጄሪያዊ ኮሜዲያንና ተዋናይ ጆን ኦካፎር ሁለት ልጆች ታሠሩ። ልጆቹ የታሰሩት ለአባታቸው ሕክምና የተዋጣን ገንዘብ ሰርቀው ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ነው። ጆን ኦካፎር የጤና እክል ገጥሞት ለሕክምና ከፍተኛ ገንዘብ የተዋጣለት ባለፈው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ነበር። የ62 ዓመቱ ተዋናይና ኮሜዲያን በይበልጥ ‘ሚስተር ኢቡ’ በሚለው ስሙ ነው የሚታወቀው። ‘ሚስተር ኢቡ’ ባለፈው ኅዳር […]

የምጽአት ቀን መቃረብን ስለሚቆጥረው ሰዓት ሰምተዋል? እውን የዓለምን ፍጻሜ የሚያመለክት ነው?

28 ጥር 2024, 08:07 EAT ስለ ምጽአት ቀን ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት በ1990ዎቹ አጋማሽ ነው። አስተማሪዬ ናት ስለ ምጽአት ቀን ሰዓት የነገረችኝ። አስተማሪያችን ክፍሉን ለሞላነው ተማሪዎች ጉዳዩን ስታስረዳ ፊቷ ላይ በሚነበብ መመሰጥ ነበር። ከዚህ ቀደም የሆኑ ነገሮች ሁሉ በአንድ ዓመት ይታጨቃሉ አለችን። ግራ መጋባት ፊታችንን ላይ ጎልቶ ቢታይ የሚገርም አይሆንም። ሕይወት የጀመረችው መጋቢት አካባቢ ነው፤ […]

ሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ የክሩዝ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች

28 ጥር 2024, 09:25 EAT ሰሜን ኮሪያ ተከታታይ የክሩዝ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች። ሚሳኤሎቹ ያረፉት ምሥራቃዊ ጠረፍ የዉሃ አካል ላይ ነው። ከቅርብ ወራት ወዲህ ሰሜን ኮሪያ ተከታታይ የሚሳኤል ሙከራዎችን ማድረጓ በአካባቢው ውጥረት እንዲሰፍን አድርጓል። ትናንት እሑድ የተተኮሱት ክሩዝ ሚሳኤሎች የተደረጉት ሲንፖ ወደብ አቅራቢያ ነው። ምን ያህል ሚሳኤሎች ስለመተኮሳቸውም ሆነ የሚሳኤሎቹ ዓይነት በዝርዝር አልታወቀም። ባለፈው ረቡዕ ሰሜን […]

የአፍሪካ ዋንጫ፡ ናይጄሪያ እና አንጎላ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ተሸጋገሩ

28 ጥር 2024, 09:18 EAT በአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ በአዴሞላ ሉክማን ሁለት ጎሎች ካሜሩንን በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ተሸጋገረች። ደካማ የሚባል አቋም ያሳየችው ካሜሩን ሻንጣዋን ልትሸክፍ ግድ ሆኗል። የጣሊያኑ አታላንታ አጥቂ ለአጋማሽ ዘጠኝ ደቂቃዎች ሲቀሩት ባስቆጠራት ጎል ሀገሩን ቀዳሚ አድርጓል። ሉክማን ከናፖሊው አጥቂ ቪክተር ኦሲምሄን ያገኘውን ኳስ ኦናናን ተክቶ የተሰለፈው ግብ ጠባቂው ፋብሪስ ኦንደዋን ተሻግሮ አስቆጥሯል። […]

ልጆች በሚጠቀሟቸው የቆዳ ቅባቶች ይዘት ላይ ወላጆች ቁጥጥር እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ

28 ጥር 2024, 08:08 EAT በመላው ዓለም ታዳጊዎች የውበት መጠበቂያ ምርቶች የመጠቀም ልማድ መስፋፋት ልጆችን ሊድን ለማይችል የቆዳ በሽታ ሊያጋልጣቸው እንደሚችል የብሪታኒያ የቆዳ ሐኪሞች ማኅበር አስጠነቀቀ። ታዳጊዎች በቲክቶክ እና ዩቲዩብ ላይ የሚከተሏቸው ተጽእኖ ፈጣሪዎች አልያም ወላጆቻቸው የሚጠቀሟቸውን የቆዳ ማስዋቢያ ምርቶች እንዲገዙላቸው ይጠይቃሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ለአዋቂዎች ተብለው የሚዘጋጁት ምርቶች የሕጻት ቆዳን በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ እንደ […]