ትረምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ተረፉ
September 17, 2024 – VOA Amharic … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በደብረጽዮን የሚመራው ማዕከላዊ ኮሚቴ እነ አቶ ጌታቸውን አገደ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩም እንዲስተካከል ጠየቀ
ከ 5 ሰአት በፊት በደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው አዲሱ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 16 ከፍተኛ አመራሮቹን ከፓርቲው ፖለቲካዊ ሥራዎች ማገዱን አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ የታገዱት አመራሮች፣ በህወሓት ውክልና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያላቸው ኃላፊነት ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ እንደሚፈልግ ገልጿል። ህወሓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ እና በከፍተኛ አመራሮቹ ተቀባይነት ሳያገኝ […]
አንጋፋው ምሁር እና ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ከ 3 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ሊቀ መንበር አንጋፋው ምሁር እና ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የፕሮፌሰሩን ማለፍ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ “[ፕ/ር በየነ] ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውንን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ” ብለዋል። ፕሮፌሰር በየነ ከታኅሣሥ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥታዊው የፖሊሲ ጥናት ኢንስትዩት […]
በጎንደር እና በአካባቢው ግጭቶች ሲካሄዱ መሰንበታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
ከ 34 ደቂቃዎች በፊት በታሪካዊቷ በጎንደር ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ሌሎች አካባቢዎች ሰሞኑን በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ መደረጉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። የሰሜን ጎንደር ዞን መቀመጫ በሆነችው በደባርቅ እንዲሁም በዳባት እና በአምባ ጊዮርጊስ ከተሞች ውጊያው ሲደረግ የሰነበተ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ በማዕከላዊ ጎንደር ዋና ከተማ በሆነችው ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ነዋሪዎቹ […]
እየተስፋፋ ባለው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ በርካቶች እየተያዙ መሆናቸውን ሳይንቲስቶች ገለጹ
ከ 1 ሰአት በፊት በቅርቡ በዋነኝነት ሊስፋፋ በሚችል አዲስ የኮቪድ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ሳይንቲስቶች ገለጹ። በሰኔ ወር ጀርመን ውስጥ የተገኘው ኤክስኢሲ የተሰባለው ዝርያ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዴንማርክ እና በሌሎች በርካታ አገራት ውስጥ መከሰቱ ተገልጿል። ምንም እንኳን ክትባቶች ከባድ ጉዳት እንዳይደረስ ለመከላከል የሚረዱ ቢሆኑም፣ አንዳንድ አዳዲስ ዝርያዎች በመጪው ክረምት ወራት ዝርያው እንዲሠራጭ […]
በሱዳን ጦርነት አስከፊ ከተባለው እልቂት ጀርባ ያለው ማን ነው?
ከ 6 ሰአት በፊት ማስጠንቀቂያ፡ ይህ ጽሑፍ አንዳንድ አንባቢዎችን ሊረብሹ የሚችሉ ይዘቶች አሉት። ለ40 ዓመቱ አርሶ አደር አሊ ኢብራሂም ቅዠት የሚመስለው ክስተት የጀመረው ሰኔ 5 ቀን ከሰዓት በኋላ ነበር።በዕለቱ የከባድ የጦር መሳሪያዎች ድምፅ ከየአቅጣጫው ይሰማ ጀመር። “ከልጅነታችን ጀምሮ እንዲህ ዓይነት ድምጽ ሰምተን አናውቅም።” የሚለው አሊ የቦምብ ጥቃቱ ለአራት ሰዓታት ያህል እንደቆየ፣ ቤቶች እንደወደሙ፣ ለማምለጥ ምንም አቅም […]
‘በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፍኩት ፎቶ ምክንያት ተገረፍኩ’
ከ 6 ሰአት በፊት *ማሳሰቢያ ይህ ጽሁፍ የአንባብያንን ስሜት ሊረብሹ የሚችሉ ይዘቶችን አካቷል። አንዳንድ ስሞችም ተቀይረዋል። በኢራን የሚገኙ ሴቶች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያላቸው ተሳትፎ በመንግሥት ሹማምንት ይሰለላል። የስላለው ውጤት ታይቶ አንዳንዶች ወደ እስር ቤት ይላካሉ። ሌሎች ደግሞ ዛቻ ይደርስባቸዋል አልያም ይደበደባሉ። ይህ ኢራን የሚገኙ ሴቶች ለቢቢሲ የገለጹት ነው። ከሁለት ዓመት በፊት በኢራን ማህሳ አሚኒ የተባለች […]
የፌስቡክ ባለቤት ሜታ የሩሲያውን የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን ከመድረኮቹ አገደ
ከ 5 ሰአት በፊት የፌስቡክ ባለቤት የሆነው ሜታ በሚያስተዳድራቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች አማካኝነት ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ያልተገባ ተጽእኖ ለመፍጠር እየሞከሩ ነው በሚል በርካታ የሩሲያ መንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን ገጽ ዘጋ። ሜታ ባወጣውወ መግለጫ “በጥንቃቄ ካደረግነው ምልከት በኋላ በሩሲያ መንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ መገናኛ ብዙኃን ላይ እርምጃ ወስደናል። በዚህም ሮሽያ፣ አርቲ እና ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸውን […]
አርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ፣ ሪያል ማድሪድ…የዘንድሮውን የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማን ያነሳል? እነማንስ ጎልተው ይወጣሉ?
ከ 5 ሰአት በፊት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ [ማክሰኞ መስከረም 8] ምሽት ይጀምራል። 36 ክለቦች እንደ አዲስ በተዋቀረው ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። ቀደም ሲል ለባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ ይፋለሙ የነበሩት 32 ቡድኖች ብቻ ነበሩ። ፍጻሜውን ሙኒክ ላይ የሚያደርገውን የዘንድሮውን ዋንጫ ማን ሊያነሳ እንደሚችል የቢቢሲ የእግር ኳስ ተንታኞች ግምታቸውን ሰጥተዋል። የትኛው ቡድን አስገራሚ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል እና ጎልተው […]
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስሩ ያለው የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ትምህርት ክፍል እንዲዘጋ ወሰነ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
September 14, 2024 በናሆም አየለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ18 ዓመት በፊት የተቋቋመውን የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ትምህርት ክፍልን፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሊዘጋ ነው። በፍልስፍና ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጠው ትምህርትም፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንዲቋረጥ ዩኒቨርስቲው ውሳኔ አስተላልፏል። አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ከእዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው፤ የትምህርት ክፍሎቹ ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት አዲስ ተማሪዎችን ባለመቀበላቸው ነው። የአልማዝ ኢዮቤሊዮውን […]