የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርሕና 79ኛዉ ጉባኤ

September 24, 2024 – DW Amharic  አንዳዶች የሐገራት መሪዎች ኒዮርክ ቅምጥል ሆቴሎች ዉስጥ የሚንደላቀቁ፣ የሚቀብጡ፣ የሚገባበዙበት ዓመታዊ ድግስ ይሉታል።መሪዎች ላጭር ጊዜም ቢሆን ለዓለም የልባቸዉን የሚናገሩበት አጋጣሚ የሚሉትም አሉ።የደካማ-ድሆቹ ሐገራት መሪዎች የኃያላን-ሐብታሞቹን ድጋፍና ርጥባን ለማግኘት የሚሻሙበት ሥብሰባ ነዉ ባዮችም አሉ።ሌሎች ሌላ።ጉባኤዉ ሁሉንም ነዉ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የስፖርት ዘገባ

September 24, 2024 – DW Amharic  በሳምንቱ መጨረሻ እጅግ ተጠባቂ በነበረው የማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል ፍልሚያ ሲቲ በሜዳው ጉድ ከመሆን የማታ ማታ ተርፏል ። አርሰናል ሙሉ ግማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜውን አንድ ተጨዋች ጎድሎበትም አይበገሬነቱን ዐሳይቷል ። ቸልሲ እና በሻምፒዮንስ ሊጉም ድል የቀናው ሊቨርፑል በተመሳሳይ የግብ ልዩነት ተጋጣሚዎቻቸውን አሰናብተዋል ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በኔዘርላንድስ በግጭት ተሳታፊ ናቸው በተባሉ ኤርትራውያን ላይ እስር ተፈረደባቸው

ከ 7 ሰአት በፊት የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት ባለፈው ዓመት የካቲት በኤርትራውያን መካከል በተፈጠረው ግጭት ውስጥ ጉልህ ሚና ነበራቸው ባላቸው ተሳታፊዎች ላይ የእስር ቅጣት ወሰነ። በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች ዘ ሄግ ከተማ ውስጥ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ ተቃዋሚ ኤርትራውያን ተገኝተው በተሽከርካሪዎች፣ በሌሎች ንብረቶች እና በፖሊስ ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው የግጭቱ አስተባባሪ እና ዋነኛ ተሳታፊዎች ናቸው የተባሉ […]

በአፍሪካ ተጽዕኖዋ የበረታው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአህጉሪቱ ምን ትፈልጋለች?

ከ 9 ሰአት በፊት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአህጉረ አፍሪካ የምታሳድረው ተጽዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መጥቷል። በአህጉሪቱ ላይ ጫና ለማሳደር ገንዘብ ፈሰስ ማድረግን ጨምሮ ሌሎችንም መንገዶች ትጠቀማለች። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ቅድሚያ የምጣኔ ሃብት ፖሊሲን ታራምዳለች። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ እና የሳህል ቀጣና ከሌሎችም አገራት ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን ፈርማለች። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሕገ ወጥ ንግድ እና ከመንግሥታት […]

አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ወደ ሶማሊያ የሚላኩ የጦር መሳሪያዎች “በአሸባሪዎች እጅ ሊወድቁ” እንደሚችሉ አስጠነቀቁ

ከ 5 ሰአት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ፤ “የውጭ ኃይሎች” ወደ ሶማሊያ የሚልኳቸው የጦር መሳሪያዎች “በአሸባሪዎች እጅ ሊወድቁ ይችላሉ” የሚል ስጋታቸውን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፖለቲካ እና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝሜሪ ዲካርሎ ገለጹ። አምባሳደር ታዬ፤ ይህንን ስጋታቸውን የገለጹት በአሜሪካ ኒውዮርክ እየተካሄደ ካለው የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ትናንት ሰኞ መስከረም […]

እስራኤል በሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 492 ሰዎች ተገደሉ

ከ 7 ሰአት በፊት በሊባኖስ ሄዝቦላህ ላይ ባነጣጠረው የእስራኤል የአየር ጥቃት ቢያንስ 492 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል። በዚህም ከ20 ዓመታት ወዲህ እጅግ አስከፊው ቀን ሆኖ ተመዝግቧል። ሄዝቦላህ እአአ ከ2006 ወዲህ የገነባቸውን መሰረተ ልማቶችን ለማውደም የእስራኤል ጦር በወሰደው እርምጃ አንድ ሺህ 300 የቡድኑን ዒላማዎችን መምታቷን ገልጻለች። በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ደግሞ ቤታቸውን ጥለው ተወሰደዋል። […]

ቴሌግራም ‘የተጠርጣሪ’ ደንበኞቹን አንዳንድ መረጃዎች ለሕግ አካላት አሳልፎ ሊሰጥ ነው

ከ 8 ሰአት በፊት በዓለም ታዋቂ ከሆኑ የመረጃ መለዋወጫ መተግበሪያዎች አንዱ የሆነው ቴሌግራም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የደንበኞቹን መረጃዎች ለሕግ አካላት አሳልፎ ሊሰጥ ነው። በዚህም የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ስልክ ቁጥሮች፣ የኢንተርኔት አድራሻ እና ሌሎች መረጃዎ በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት በመሳሰሉ የሕግ ተርጓሚዎች በሚፈለግበት ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችል የመተግበሪያው አስተዳዳሪ ተቋም አሳውቋል። የቴሌግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፔቨል ዱሮቭ ይህ አዲስ […]

በባሕር ላይ ለቀናት ስትንሳፈፍ ነበረ በተባለች ጀልባ ላይ 30 አስክሬኖች ተገኙ

ከ 8 ሰአት በፊት በሴኔጋል ለበርካታ ቀናት በባሕር ላይ ሲንሳፈፍ ነበር በተባለ አንድ ጀልባ ላይ የ30 ሰዎች አስክሬኖች መገኘታቸውን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አስታወቁ። የአገሪቱ መከላከያ በኤክስ ገጹ ባወጣው መግለጫ፣ ከመዲናዋ ዳካር 70 ኪሎሜትር ርቆ ጀልባ ሲንሳፈፍ ከታየ በኋላ የባሕር ጠረፍ ጥበቃዎች በቦታው መገኘታቸው ተገልጿል። ከእንጨት የተሠራውን ጀልባ ወደ ወደብ ከወሰዱት በኋላ እየፈራረሰ ያለ የሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። […]