ቅዱስ ላሊበላ ከተማ እንግዷቿን በመቀበል የነበረ ግርማ ሞገሷን በመላበስ ተናገራለች
January 7, 2025 ” ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በእግሩ ነው የመጣው ፤ ቀጥሎ በትራንስፓርት እየመጣ ያለ እንግዳ አለ ” – የላሊበላ ከተማ አስተዳደር የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በተለይ በላሊላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን በደማቁ ይከበራል። ድንቁ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን የሚገኝበት አማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተኩስ ቀጠና ከሆነ አንድ አመት ከወራት በላይ […]
ገና በላሊበላ
January 7, 2025 – VOA Amharic የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት – ገና በዓል በልዩ ኹኔታ ከሚከበርባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች በቀዳሚነት የምትጠቀሰው፣ በዐማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ናት። በዩኔስኮ የሰው ልጆች ቅርስ ኾኖ የተመዘገቡት የ11 ውቅር አብያተ መቅደሶች መገኛዋ ላሊበላ፣ በገና በዓል ሰሞን፣ ዐያሌ የአገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችንና ተሳላሚ ምእመናንን በሞቀ አቀባበል ታስተናግዳለች… … […]
የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ
Monday, 06 January 2025 21:35 የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ Written by Administrator መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ፤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና […]
“የህወሓት አመራሮችን ልዩነት በድርድር ለመፍታት የተደረገው አልተሳካም” ጄነራል ታደሰ ወረደ
January 7, 2025 – VOA Amharic በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በድርድር ለመፍታት፣ በክልሉ የጸጥታ አመራር አካላት ለወራት የተካሔደው ጥረት እንዳልተሳካ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ሌተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ገለጹ። ምክትል ፕሬዝደንቱ ትላንት እሑድ ለክልሉ ብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ በጉባኤ ላይ የተሳተፉትና ያልተሳተፉት በሚል የለዩዋቸው ሁለቱ የተከፋፈሉት የህወሓት አመራሮች… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ […]
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንቶች የመንግሥቱን መዋቅር ሥፋት ለመቀነስ ያደረጓቸው ጥረቶች አልተሳኩም
January 7, 2025 – VOA Amharic ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመንግሥታቸውን ወጪ መቀነስ ይፈልጋሉ። ‘የመንግሥት ብቃት መምሪያ’ የሚል መጠሪያ የተሰጠውም አማካሪ ኮምሽን በዋናነት ይህን ጥረት እንደሚመራ ይፋ ተደርጓል። ይሁን እንጂ ውጥኑ በጽንሰ-ሐሳብ ደረጃ ሲቀርብ አዲስ አይደለም። የአሜሪካ ድምጿ ዶራ መኩዋር ባጠናቀረችው ዘገባ እንደጠቆመችው፣ የዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች ገና ከሃገረ መንግሥቱ ምሥረታ ወቅት አንስቶ የመ… … ሙሉውን ለማየት ወይም […]
በአሜሪካ ምክር ቤት የምርጫ ውጤት ማረጋገጫ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
January 7, 2025 – VOA Amharic በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ዶናልድ ትረምፕ በፕሬዝደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን ማረጋገጫ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል። ከ50 ግዛቶች የተላኩትን የድምጽ ቆጠራ ውጤቶችን የማረጋገጡን ሥነ ሥርዓት የመምራት ኅላፊነት የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆኑ፣ በፕሬዝደንታዊ ምርጫው የተሸነፉት ካመላ ሄሪስ የዶናልድ ትረምፕን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፣ የራሳቸውንም መሸነፍ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። በጋራ ም/ቤቱ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ […]
በአሜሪካ በረዶ ትምህርት ቤቶችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲዘጉ አደረገ
January 7, 2025 – VOA Amharic በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ከትላንት ዕሁድ ጀምሮ የጣለው በረዶና ኅይለኛ ነፋስ ትምህርት ቤቶችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲዘጉ አስገድዷል። በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍሎች በመጣል ላይ ያለው በረዶ በተለይም በአንዳንድ ሥፍራዎች በአሥርት ዓመታት ያልታየ መጠን ሊሆን እንደሚችል በመነገር ላይ ነው። የአሜሪካ ድምጽ የሚገኝበት ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ያሉ ግዛቶች … … ሙሉውን […]
አስር የአልሻባብ አባላት በአየር ጥቃት ተገደሉ
January 7, 2025 – VOA Amharic የአሜሪካ ጦር በፈጸመው የአየር ጥቃት 10 የአል ሻባብ አባላት መገደላቸውን የሶማሊያ መንግሥት አስታውቋል። የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በመግለጫው እንዳለው፣ የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው ቢርሃኒ በተባለና ከኪሲማዮ ሰሜን ምዕራብ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ሥፍራ ነው። የሚኒስቴሩ መግለጫ የወጣው ትላንት እሑድ ሲኾን፣ የአየር ጥቃቱ መቼ እንደተፈጸመ ግን አላሳወቀም። የሶማሊያው የማስታወ… … ሙሉውን ለማየት […]
የሕወሃት ባለስልጣናትን ለማደራደር የተደረገው ጥረት አልሰመረም
January 7, 2025 – DW Amharic በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ልዩነት በድርድር ለመፍታት የተደረገ ጥረት እንዳልተሳካ የትግራይ ሐይሎች አዛዥ እና የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ። ይህ የማደራደር ጥረት ያልተሳካው ልዩነቶች በንግግር ለመፍታት ከመፈለግ ይልቅ፥ አንዱ ሌላውን ለማጥፋት ካለፍላጎት የሚነሳ ነው ብለዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
የመሬት መንቀጥቀጡ እና ሊወሰድ ይገባል የተባለው ቀጣይ ጥንቃቄ
January 7, 2025 – DW Amharic በአፋር ዞን ሶስት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች እንዲሁም በአጎራባች ክልሎች የተከሰተው ከፍተኛ ስጋት የደቀነው የመሬት መንቀጥቀት ባለፉት 24 ሰዓታት መቀዛቀዝ ብያሳይም መዘናጋት እንዳይፈጥር ጥሪ ቀረበ፡፡ የአከባቢው ነዋሪዎች እና ባለሙያ ባለፉት 24 ሰዓታት የመሬት መንቀጥቀጡ መጠነኛ መቀነስ ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ