በአማራ ክልል ተመላሽ ፍልሰተኞች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ገለጹ
November 27, 2024 – VOA Amharic ከተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አማራ ክልል ተመልሰው የነበሩ ሰዎች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ተናገሩ። ቪኦኤ ያነጋገራቸው፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ የሚገኙ ከስደት ተመላሾች፣ መንግሥት ሊያቋቁማቸውን የገባውን ቃል ባለመጠበቁ፣ በድጋሚ ለመሄድ ዝግጅት ላይ መኾናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ተንቀሳቅሰው መሥራት አለመቻላቸው ችግሩን እንዳባባሰው ገልጸዋል። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ […]
በሱዳን ጦርነት የሟቾቹ ቁጥር ከተገመተውም በላይ እንደሆነ አዲስ ጥናት አመለከተ
November 27, 2024 – VOA Amharic በሱዳን ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ብዛት ከዚህ በፊት ከተገመተው ሊበልጥ እንደሚችል አንድ ዐዲስ ጥናት አመለከተ። ግጭቱ 11 ሚሊዮን ሰዎችን ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅል፣ በዓለም አስከፊ የተባለውን ረሃብ ማስከተሉን ጥናቱ ጠቁሟል። ሄንሪ ሪጅዌል የላከው ዘገባ ነው። ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በኬኒያ የንብ ርባታ ማኅበረሰቦች የአየር ንብረት ለውጡን እንዲቋቋሙ እየረዳ ነው
November 27, 2024 – VOA Amharic የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር በሞቃታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦች በዓለም ሙቀት መጨመር ከሁሉም በላይ ተጎጂዎች መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ተደጋጋሚ ድርቅ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ እንደ እርሻ እና የእንስሳት እርባታ ያለውን የኖረ መተዳደሪያቸውን የማይቻል አድርገውታል። በኬንያ ያሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ታዲያ እንደነዚህ ያሉ ማህበረሰቦች ተለዋዋጭ የአየር ሁኔታን ለ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ […]
የአቶ ታዬ ደንደአን ተጨማሪ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
November 26, 2024 – VOA Amharic የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ መከላከያ ምስክሮች የመጥሪያ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግሥት ሥርዓት ችሎት፣ የተከሳሹን ቀሪ የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። “የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ ኾነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ኀይሎች ጋራ በመተሳሰር ለጥፋት… … ሙሉውን ለማየት […]
መንግሥት ያቀረበው የ582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጥያቄ በፓርላማ ጸደቀ
November 26, 2024 – VOA Amharic የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ባካሔደው መደበኛ ስብሰባው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረበውን የ582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ አጸድቋል፡፡ ይህም በአጠቃላይ የፌዴራል መንግሥቱን የ2017 ዓ.ም. በጀት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ አድርሶታል። ምክር ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ ኅዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄደው ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ… … […]
እስራኤል እና ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ጆ ባይደን አረጋገጡ
ከ 8 ሰአት በፊት እስራኤል እና የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ለ13 ወራት የዘለቀውን ውጊያ ለመቋጨት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አረጋገጡ። “በሊባኖስ እና በእስራኤል ድንበር ላይ እየተደረገ ያለው ፍልሚያ ማክሰኞ ከሌሊቱ አስር ሰዓት ጀምሮ በአገሬው ሰዓት ይቋጫል” ሲሉ ባይደን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ባይደን የተኩስ አቁሙ ግጭትን በዘላቂነት ወደ ማቆም ስምምነት ለመድረስ ያለመ እንደሆነ አመልክተዋል። […]
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የጣሉትን እገዳ አምነስቲ አወገዘ
ከ 4 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የጣሉትን እገዳ ኣለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪው አምነስቲ አወገዘ። የመብቶች እና የዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተሰኙት ድርጅቶች ላይ የተጣለው እገዳ በሲቪል ማኅበረሰቡ ምኅዳር ላይ የተቃጣው አፈና እየጨመረ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ሲል አምነስቲ ማክሰኞ፣ ኅዳር […]
“መምህር በመሆኔ አዘንኩ” – የኢትዮጵያ መምህራን እሮሮ
ከ 9 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ መምህራን በተለያየ አቅጣጫዎች ሰቆቃቸውን እያሰሙ ነው። ለ17 ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህራን መንግሥትን መክሰሳቸው ታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው በአራት ክልሎች የሚገኙ የኢትዮጵያ መምህራንም በደል እየተፈጸመብን ነው ብለዋል። መምህራን ከደሞዝ መቆራረጥ ጀምሮ በግዴታ መዋጮ እንዲያወጡ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፣ ለምን ብለው የጠየቁት ደግሞ ለድብደባ፣ ለእስር እና ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዋል። የመምህራን ማኅበር በበኩሉ […]
‘ማንም አይጠቀምም’ ሲሉ ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ለትራምፕ የታሪፍ ጭማሪ ዛቻ ምላሽ ሰጡ
ከ 7 ሰአት በፊት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሦስቱ ታላላቅ የአሜሪካ የንግድ አጋሮች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ለመጣል የገቡት ቃል የአራቱንም አገራት ኢኮኖሚ ሊጎዳ እንደሚችል የካናዳ፣ የሜክሲኮ እና የቻይና ባለስልጣናት አስጠነቀቁ። “የጋራ ንግዶቻችንን አደጋ ላይ እስክንጥል ድረስ ለአንዱ ታሪፍ ሌላው ምላሽ ይሰጣል” ሲሉ የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሺንባም ተናግረዋል። ትራምፕ ሰኞ ምሽት ከሜክሲኮ እና ካናዳ በሚገቡ […]
አዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ለአፍሪካ ምን ይዘው ይመጣሉ?
ከ 9 ሰአት በፊት በቅርብ ጊዜያት አሜሪካንን የመሩ ፕሬዝደንቶች ለአፍሪካ ትኩረት ሲሰጡ አልታዩም። ተንታኞች አዲሱ የትራምፕ አስተዳደርም የተለየ ይዞ ነገር ይመጣል ብለው አያስቡም። ዶናልድ ትራምፕ ጥር 12/2017 ዓ.ም. የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ ማርኮ ሩቢዮ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይሆናሉ። እርግጥ ነው ሹመታቸው በሴኔቱ መፅደቅ አለበት። ሩቢዮ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጉዳይ ፈርጠም ያሉ ናቸው […]