የቻግኒ ሙስሊሞች የአምሳለ ኦነጉን መሪ አየር አሳጠሩት!
December 18, 2023 – Konjit Sitotaw የቻግኒ ሙስሊሞች የአምሳለ ኦነጉን መሪ አየር አሳጠሩት! ይህ እንግዳ ዳኛው የአገዛዙ የአዊ ዞን አስተዳዳሪ ሌሎች 2 የኦሮሙማ ስምሪቶች አሉት። እነሱም 1) እንደ እናት ጡት 2 ሁነው የሚንከላወሱትን ሸንጎ (አምሳለ ኦነግ) ለሚባሉ ስብስቦች ስምሪት ሰጭነትና፣ 2) የአካባቢው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢነት ናቸው። ታዲያ ሰሞኑን በቻግኒ ከተማ ህዝበ ሙስሊበ ሙስሊሙን ሰብስቦ “ፋኖ ዓላማ አሃዳዊ […]
አቶ ታዬ ደንደአ እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ
18 ታህሳስ 2023, 14:08 EAT ከሰላም ሚኒስቴር ዴኤታነት ተነስተው መንግሥትን ለመጣል ሲያሴሩ ነበር በሚል ከሳምንት ገደማ በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ታዬ ደንደአ እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ለቢቢሲ ተናገሩ። ወ/ሮ ስንታየሁ ባለቤታቸው በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ አንድ ሳምንት እንደሆናቸው አስታውሰው እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን እንዲሁም ጠበቆቻቸውም እንዲያናግሯቸው እንዳልተፈቀደ ተናግረዋል። […]
በሰሜን ሸዋ ዞን የአውራ ጎዳና መንደር ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን ነዋሪዎች ገለፁ
December 18, 2023 – VOA Amharic በዐማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና ወይም ቆርኬ ከተማ ላይ፣ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ፈጽመውታል ባሉት ጥቃት፣ ሰላማዊ ዜጎች እንደተገደሉና ከቀዬአቸው እንደተፈናቀሉ፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት እና ተጎጂዎች አስታወቁ፡፡ በ“ኦሮሚያ ልዩ ኀይል” እንደተፈጸመ በገለጹት ጥቃት፣ ከዐዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በሚወስደው አውራ ጎዳና ዳር የምትገኘዋ ከተማ ነዋሪዎች ንብረት እንደተዘረፈና እንደወደመ፣ […]
ቲሊሊ ወረዳ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገባች!
December 18, 2023 ቲሊሊ ወረዳ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገባች! በትናንትናው ዕለት ማለትም ታህሳስ 07/2016 ዓ.ም ከቲሊሊ ወረዳ ወጥቶ ወደ ሠከላ ወረዳ ለመግባት በመንገድ ላይ እያለ አሽፋ መገንጠያ ላይ በቲሊሊ ወረዳ ፋኖዎች መመታቱን ገልፀን ነበር። የመከላከያ 15(አስራ አምስት) የፊት አብሪዎችን በመምታት ድሉን የጀመረው የቲሊሊ ጀግና ፋኖ ሙሉው መከላከያ ከቲሊሊ ወጥቶ አሽፋ ላይ ፋኖን ቢገጥምም የፋኖን ጉልበት […]
ግዙፉ ነዳጅ አምራች ኩባንያ በቀይ ባሕር በኩል ነዳጅ ማመላለስ አቋረጠ
18 ታህሳስ 2023, 16:50 EAT ግዙፉ ነዳጅ አምራች ቢፒ (ብሪቲሽ ፔትሮሊየም) በደኅንነት ስጋት ምክንያት ነዳጅ የጫኑ መርከቦቹ በቀይ ባሕር በኩል ለተወሰነ ጊዜ ማለፋቸውን እንደሚያቆሙ አስታወቀ። ኩባንያው ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦቹ በቀይ ሕር የሚያደርጉት ጉዞን ለማቋረጥ የወሰነው በቅርቡ በሁቲ አማጽያን መርከቦች ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ነው። ይህን ውሳኔ በጊዜያዊነት ያስተላለፈው በአካባቢው ያለው “የደኅንት ሁኔታ አስጊ ስለሆነ […]
የዲያስፖራው ማህበረሰብ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መነሻ እና መዳረሻ ( በኤሊያስ መሰረት )
December 18, 2023 ከቅርብ ግዜ ወዲህ የዲያስፖራው ማህበረሰብ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መነሻ እና መዳረሻ እየሆነ ይገኛል። በዚህ ዙርያ ሄይንሪክ ቦል ስቲፍቱንግ በዋሽንግተን ዲሲ ቢሮው አማካኝነት ባዘጋጀው Trans-Atlantic Fellowship ላይ በመካፈል ይህን የዲያስፖራ አካሄድ የቃኘሁበትን ረዘም ያለ ፅሁፍ ላጋራችሁ: (ፅሁፉ በአዲስ ስታንዳርድ፣ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ቦርከና፣ የአፍሪካ ምርምር ተቋም ላይ ቀርበዋል)። ( ኤሊያስ መሰረት ) Elias Meseret Diaspora Dilemma: Shadows […]
ከ10 ዓመት በኋላ አስከሬናቸው በተዘጋ ቤት በተገኘው ሴት ሞት የተጋለጠው የሆላንዳውያን ብቸኝነት
ከ 6 ሰአት በፊት በሆላንድ በ70ዎቹ የሚገኙ ሴት ከሞቱ ከአስር ዓመት በኋላ አስከሬናቸው በቤታቸው መገኘቱ አገሪቷ ብቸኝነትን ለመቅረፍ ለጀመረችው ብሔራዊ ዘመቻ መነሻ ሆኗል። የአገሪቱ ፖለቲከኞችም እያንዳንዱ ዜጋ በማኅበረሰቡ ውስጥ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል በሚል በርካታ ተነሳሽነቶች ጀምረዋል። አሳዛኝ ክስተቱ የተፈጠረው ከዛሬ አስር ዓመት በፊት ነበር። የ74 ዓመቷ ቤፕ ደ ብሩን አስከሬን በሮተርዳም በሚገኘው ቤታቸው ተገኘ። አስከሬናቸው […]
‘ረሃብ በረታብን’ – ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በልመና ያጨናነቋት የጂቡቲ ከተማ
ከ 6 ሰአት በፊት “እንዴት ናችሁ?”. . . . . . “Akkam jirtu?” በጎናችን እያለፉ ለነበሩት ስደተኞች ያቀረብነው ሰላምታ ነበር። በጂቡቲ በረሃ በየጥጋ ጥጉ ተስፋ ቆርጠው ለተቀመጡ እና ነገ የሚያመጣውን ለማይገምቱ፣ ቀጣዩ ምግባቸውን ማን እንደሚመጸውታቸው ለማያውቁ ኢትዮጵያውያን ይህ ሰላምታ ያልጠበቁት ነበር። በቀይ ባሕር ዳርቻዋ የጂቡቲ ከተማ ኦቦክ ነው የምንገኘው። ይህቺ ከተማ የመንን አሻግረው ለሚያልሙ ኢትዮጵያውያን […]
እስራኤል ተኩሳ የገደለቻቸው ታጋቾች እርዳታ የሚማጸኑ ጽሁፎች በጨርቅ ላይ አስፍረው ነበር ተባለ
ከ 5 ሰአት በፊት የእስራኤል መከላከያ ተኩሶ የገደላቸው እስራኤላዊ ታጋቾች እርዳታን የሚማጸኑ ጽሁፎች በጨርቅ ላይ ጽፈው ነው ተባለ። ጽሁፎቹንም ለማስፈር የተራረፈ ምግብ መጠቀማቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። አርብ እለት የተገደሉት ሶስቱ እስራኤላዊ ታጋቾች በነጭ ጨርቅ ላይ እርዳታን የሚጠይቅ ጽሁፎች አስፍረው እንዲሁም እያውለበለቡ ነበር ተብሏል። ሶስቱ ታጋቾች ተተኩሰው በተገደሉበት ህንጻ ለተወሰነ ጊዜ ቆይተው ሊሆን እንደሚችል ባለስልጣናቱ ያምናሉ። […]
ከስድስት ዓመታት በፊት በሊቢያ የታገተው ደቡብ አፍሪካዊ በአል-ቃኢዳ ታጣቂዎች ነጻ ወጣ
ከ 5 ሰአት በፊት ከአል- ቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው እስላማዊ ታጣቂዎች ከስድስት ዓመታት በፊት በሊቢያ ታግቶ የነበረውን ደቡብ አፍሪካዊ የድንገተኛ አደጋ የህክምና ባለሙያ ማስፈታታቸውን አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ። ጊፍት ኦፍ ዘ ጊቨርስ የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ለረዥም ጊዜ ታግቶ ቆይቷል ያለውን፤ ታጋቹን ጌርኮ ቫን ዴቨንተር “ያለ ቅድመ ሁኔታ” እንዲለቀቅ ማመቻቸቱን አስታውቋል። እ.ኤ.አ. በ 2017 […]
