የአሜሪካ የታችኛው ሕግ አውጭ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመምከር ስብሰባ ጠርቷል።
November 28, 2023 የአሜሪካ የታችኛው ሕግ አውጭ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመምከር ለቀጣዩ ሐሙስ ስብሰባ ጠርቷል። የምክር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ፣ “በኢትዮጵያ፣ ተስፋ ወይስ የበረታ ስጋት፤ የአሜሪካ ፖሊሲ ኹኔታ’’ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በጠራው ምክክር ጉዳዩ ላይ በቀጥታ ይመለከታቸዋል የተባሉ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ምስክርነት እንደሚያዳምጥና ሰፋ ያለ ምክክር እንደሚያደርግ አስታውቋል። በምክር […]
ትግራይ የአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች የሶስት አመት ደሞዝ ጠየቁ
November 28, 2023 በትግራይ ከልል አድዋ ከተማ የሚገኘው የአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች ከመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ደመወዝ ስላልተከፈላቸው የከፋ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ለዋዜማ ተናግረዋል። ከ13 ዓመታት በላይ በፋብሪካው ውስጥ በሠራተኛነት ማገልገላቸውን ለዋዜማ የተናገሩ አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ሠራተኛ፣ ከ30 ወራት በላይ ደመወዝ ባለማግኘታቸውና እስከ አኹን ወደ ሥራ ገበታቸው ባለመመለሳቸው ርሳቸውን ጨምሮ በርካታ ሠራተኞች […]
የፈረንሳዩ የቴሌኮም ኩባንያ “ኦሬንጅ” ከኢትዮ ቴሌኮም የባለቤትነት ድርሻ የግዢ ጨረታ ሂደት ራሱን አገለለ
November 28, 2023 – Konjit Sitotaw የፈረንሳዩ የቴሌኮም ኩባንያ “ኦሬንጅ” ከኢትዮ ቴሌኮም የባለቤትነት ድርሻ የግዢ ጨረታ ሂደት ራሱን ማግለሉን ሰምቼያለኹ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። “ኦሬንጅ”፣ ከኢትዮ ቴሌኮም የ45 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለመያዝ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2021 ዓ፣ም ፍላጎቱን አሳይቶ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል። ኾኖም “ኦሬንጅ” በጨረታው የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌለው በጽሁፍ እንደገለጠለት የዜና ወኪል ዘግቧል። ኩባንያው፣ ስትራቴጂውን በፍጥነት ለመተግበርም ኾነ እሴት […]
በጐንደር የሚገኘው ዐቢየ እግዚእ ቤተ ክርስቲያን አይነ ስውሩ የአቋቋም አስተማሪ በለሊት ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ
November 28, 2023 በጐንደር የሚገኘው ዐቢየ እግዚእ ቤተ ክርስቲያን የአቋቋም አስተማሪ የነበሩት እኒኽ መምህር፥ በሰው እጅ ተወግረው መገደላቸው ተሰምቷል። ጎንደር ዓቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተክርስቲያን የአቋቋም መምህር ፤ የታች ቤት ፣ የላይ ቤትና የሳንኳ አቋቋም ተጠያቂው ሊቅ መምህር ፍስሐ ዓለምነው ኅዳር 17 በግምት ከሌሊቱ 10:00 ገደማ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። መምህሩ በትላንትናው ዕለት […]
ተያይዘን እንውደቅ ወይስ እንተሳሰብ ? ለጊዜውም ቢሆን በቁና ከመዝረፍና ከማትረፍ እንዴት እንቆጠብ ? ( ሙሼ ሰሙ )
November 28, 2023 ( ሙሼ ሰሙ ) በውጭ ምንዛሪና በጥሬ እቃ እጥረት፤ በሰላምና መረጋጋት እጦት፣ በመንግስታዊ ተቋማት ሙስናና አገልግሎት ንፍገት የሚዘጉና በቋፍ የሚገኙ ድርጅቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በአስጊ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱና የሚበተኑ ሰራተኞች ቁጥርም በአሳሳቢ ሁኔታ እያደገ መሆኑ በመገናኛ ብዙሃን በስፋት እየተዘገበ ነው። በብረት፣ በመአድን፣ በቅባት እህል፣ በውኋና ለስላሳ መጠጥ፣ በቡና፣ በግንባታ፣ በሆቴልና ቱሪዝም በጨርቃ […]
ሶስት ግዙፍ የስኳር ፋብሪካዎች ስራ አቁመዋል፣ እስከወዲያኛው የመዘጋት አደጋም አለባቸው
November 28, 2023 ዋዜማ- ኢትዮጵያ 50 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች ከገነባች አምስት ዓመት አልሞላትም። አንዳንዶቹ ግንባታቸው ሊያልቅ የተቃረቡ ናቸው። በሀገሪቱ ባለው የፀጥታ ችግር፣ በኤሌክትሪክ ኀይል አቅርቦት ችግርና በአስተዳደር ጉድለት ብዙ ተስፋ የተጣለባቸው እነዚህ ፋብሪካዎች አሁን ምርት አቁመው የሚታደጋቸውን አካል እየጠበቁ ነው። እስከወዲያኛው የመዘጋት አደጋ ያንዣበበባቸውም አሉ። ዋዜማ በጉዳዩ ላይ የሚከተለውን መረጃ አሰባስባለች። […]
በአወዛጋቢው ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ ሕይወትና ሥራዎች ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።
November 28, 2023 – Konjit Sitotaw “የአድአው ጥቁር አፈር፤ ተስፋዬ ገብረአብ ሕይወትና ምስጢር” የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሐፉ የተስፋዬን አወዛጋቢ ሕይወትና ምስጢራት ከቢሾፍቱ እስከ አስመራ በመጓዝ የሚተርክ መሆኑ ተገልጿል። በጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ሽመልስ (ጉቺ) የተዘጋጀው “የአድአው ጥቁር አፈር፤ ተስፋዬ ገብረአብ ሕይወትና ምስጢር” መጽሐፍ የአነጋጋሪውን ጸሐፊ ቤተሰቦች፣ የቀድሞ ጋዜጠኞች እና ከፍተኛ ባለስልጣናት በማነጋገርና አያሌ ጥናጦችን በማካሄድ አመት ከሰባት ወር […]
ቀጥታ ሐማስ 11 ተጨማሪ ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 30 ህጻናትን ጨምሮ 33 እስረኞችን ፈታች
ቀጥታ ሐማስ 11 ተጨማሪ ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 30 ህጻናትን ጨምሮ 33 እስረኞችን ፈታች Related Video and Audio VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44 Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? BBC Play video በሐማስ […]
ቲፋኒ ሐዲሽ ዕጽ ተጠቅማ በማሽከርከር ከተያዘች በኋላ እርዳታ እደሚያስፈልጋት ተናገረች
ከ 1 ሰአት በፊት ኤርትራዊ የዘር ሐረግ ያላት እውቋ አሜሪካዊት ኮሜዲያን ቲፋኒ ሐዲሽ ዕጽ ተጠቅማ ስታሽከረክር በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ የባለሙያ ድጋፍ ለማግኘት እንደምትጠር አስታወቀች። ቲፋኒ ባለፈው አርብ ሞተሩ ያልጠፋ መኪናዋ ውስጥ እራሷን ስታ ተገኝታ የቤቨርሊ ሂልስ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏት ነበር። ከክስተቱ በኋላ የ43 ዓመቷ ቲፋኒ “ይህ ዳግም አይከሰትም” ስትል ለኢንተርቴይንመት ቱናይት ተናግራለች። ቲፋኒ […]
በመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ ሲጓዙ የነበሩ 53 ኤርትራውያን ስደተኞች በደቡብ ኢትዮጵያ ተያዙ
ከ 5 ሰአት በፊት በመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ ተጭነው ወደ ኬንያ ሲጓዙ የነበሩ 53 ሕገ-ወጥ ኤርትራውያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኧሌ ዞን አስታወቀ። ሕገ-ወጥ ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከትላንት በስቲያ እሁድ ኅዳር 16/2016 ዓ.ም. ምሽት እንደሆነ የዞኑ ሰላም እና የፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አምሳሉ አንጋቶም ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በደላሎች አማካኝነት […]
