አቶ አህመድ ሽዴ አቶ ተክለወልድ አጥናፉን ተክተዋል።

February 13, 2024 – Konjit Sitotaw  አቶ አህመድ ሽዴ አቶ ተክለወልድ አጥናፉን ተክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴን በተክለወልድ አጥናፉ ምትክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሾሙ፣ Abiy Ahmed (PhD) has appointed Ahmed Shide, minister of Finance, as the new chair of the Board of the Commercial Bank of Ethiopia (CBE), succeeding Teklewold […]

19 ሺህ 590 ሰዎች የአስተዳደር በደል አቤቱታ በግማሽ ዓመት ውስጥ ለተቋሙ ማቅረባቸው ተገለጸ

February 13, 2024 – Konjit Sitotaw  19 ሺህ 590 ሰዎች የአስተዳደር በደል አቤቱታ በግማሽ ዓመት ውስጥ ለተቋሙ ማቅረባቸው ተገለጸ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በ6 ወራት ውስጥ በ938 አቤቱታ ዓይነቶች ስር 19 ሺህ 590 ሰዎች የአስተዳደር በደል ተፈፅሞብናል በማለት ለተቋሙ አቤቱታቸውን ማቅረባቸውን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በ2016 በጀት ዓመት 6 ወራት ስራዎች በስራ አስፈፃሚዎች በገመገመበት […]

የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ከጠ/ሚ ዐቢይ ጋር ለመወያየት ወደ ጅግጅጋ ማቅናት

February 13, 2024 – Konjit Sitotaw  የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ፣ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ለመወያየት ወደ ጅግጅጋ እንደሚያቀኑ የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ፕሬዝዳንት ቢሂ ከዐቢይ ጋር የሚወያዩት፣ ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በተፈራረሙት የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ዙሪያ እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ዐቢይ፣ ትናንት ወደ ሶማሌ ክልል አቅንተው አዲሱን የጎዴ አውሮፕላን ማረፊያ የመረቁ ሲኾን፣ ቢሂ ጅግጅጋ ስለመግባታቸው ግን የወጣ ኹነኛ መረጃ […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ከማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር ተወያዩ

February 13, 2024  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ከማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ላይ ተወያዩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁኔታና ቀጣይ የቤት ሥራዎች […]

ስለ ግብረሰዶማዊነት እና ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ ?

February 13, 2024  ስለ ግብረሰዶማዊነት እና ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ ? ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ነው ስላላቸው ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ? – ግብረ ሰዶማዊነት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተገለጸው ለአንድ ሀገርና ሕዝብ ከነጎረቤቶቹ መጥፋት ምክንያት የሆነ ተግባር […]

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት ” ከእውነት የራቀ ነው ” – የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ

February 13, 2024  ” የቀረበው ሪፖርት ከእውነት የራቀ ነው ” – የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ በትግራይ ክልል ” ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረዋል ” በሚል ፓርላማ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት ” ከእውነት የራቀ ነው ” ሲል የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወቀሰ፡፡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥር 28 ቀን 2016 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ […]

ዋልታ እና ዋፋ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስር ሊጠቃለሉ ነው

13 የካቲት 2024 አንድ “ግዙፍ ሚዲያ” ለመፍጠር በሚል ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት እንዲሁም ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን፤ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስር ሊጠቃለሉ ነው። በፋና እና በዋልታ ውስጥ የ25 በመቶ ድርሻ ያለው የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) በጉዳዩ ላይ አለመሳተፉን ለቢቢሲ ገልጿል። ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው እነዚህ ተቋማት ከሌሎች በተለየ መንግሥታዊ ዜና […]

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሆስፒታል በመግባታቸው የኔቶ ስብሰባቸውን ሰረዙ

ከ 9 ሰአት በፊት የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን በወራት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ሆስፒታል በመግባታቸው ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ስብሰባ የሚያደርጉትን ጉዞ ሰረዙ። የ70 ዓመቱ ኦስቲን ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ ሆስፒታል ጥብቅ የሕክምና ክትትል በሚያስፈልጋቸው ህሙማን ክፍል ውስጥ ናቸው። ፔንታገን እንዳለው ሚኒስትሩ ሆስፒታል የገቡት ድንገተኛ የሽንት ፊኛ ችግር ገጥሟቸው ነው። […]

አምቡላንሱ ውስጥ የተገደለው የጋዛው ነፍስ አድን ፈጥኖ ደራሽ

13 የካቲት 2024 ማስጠንቀቂያ፡ ይህ ጽሑፍ አሰቃቂ ክስተቶች የሚገለጹበት ይዘት አለው። ዜናው የተሰማው ከሰዓት 8 ሰዓት ገደማ ነው። የሕክምና ሠራተኛው ማህሙድ አል-ማስሪ እና ሌሎች የሥራ አጋሮቹ ሰሜናዊ ጋዛ ከሚገኘው አል-አውዳ ሆስፒታል ሆነው በተጠንቀቅ ይጠብቃሉ። ዜናው በድምፅ ማጉያ ተነበበ። እንዲህ ይላል “አምቡላንስ ቁጥር 5-15 ተመትቷል።” ይህ አምቡላንስ የማህሙድ አባት አምቡላንስ ነው። እሳቸውም እርዳታ ሰጪ ናቸው። ማህሙድ […]

በቴክሳስ ልጇን ይዛ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተኩስ የከፈተችው ታጣቂ ተገደለች

ከ 9 ሰአት በፊት በአሜሪካ ቴክሳስ በሚገኘው ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከልጇ ጋር የነበረች አንዲት ታጣቂ ለአምልኮ በተሰባሰቡ ምዕመናን ላይ ተኩስ ከከፈተች በኋላ በፖሊስ በተሰጠ አጸፋ ተገድላለች። ተጠርጣሪዋ ጄንሰስ ኢቮኒ ሞሬኖ እንደምትባል እና ዕድሜዋም 36 እንደነበር ፖሊስ ገልጿል። የኢቮኒ የ7 ዓመት ልጅም በተኩስ ልውውጡ ክፉኛ ተጎድቷል። መርማሪዎች ታጣቂዋ ይዛው የነበረው መሳሪያ ሰደፍ ላይ “ፍልስጤም” የሚል […]