በፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቅ የተፈቀደለት ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በእስር ላይ መሆኑ ተገለጸ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 10 ሰኔ 2025 የ’ኢትዮጵያ ኢንሳይደር’ የበይነ-መረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቅ ቢፈቅድም በእስር ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። ባለፈው እሁድ አዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም መጀመሪያ እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ […]

ዐቃቤ ሕግ በሙዚቀኛ አንዱዓለም ጎሳ ላይ ክስ ባለመመሥረቱ በዋስ መፈታቱን ጠበቃው ገለጹ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ከ 9 ሰአት በፊት በእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ በእስር ላይ የነበረው ሙዚቀኛ አንዱአለም ጎሳ ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ ባለመመሥረቱ በዋስ መለቀቁን ጠበቃው ሊበን አብዲ ለቢቢሲ ተናገሩ። ከእጮኛው ሞት በኋላ ለሶስት ወራት በእስር ላይ የቆየው አንዱዓለም ጎሳ በ50 ሺህ ብር ዋስ ማክሰኞ፣ ሰኔ 3/2017 ዓ.ም. መፈታቱን ጠበቃው ገልጸዋል። የሕግ ባለሙያው […]

በፌደራል መንግሥት የ2018 በጀት ውስጥ ለአዲስ አበባ ከተማ የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ ሳይካተት ቀረ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 11 ሰኔ 2025, 06:37 EAT በቀጣይ ዓመት የፌደራል መንግሥት አጠቃላይ በጀት ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚደረግ የበጀት ድጋፍ ሳይካተት ቀረበ። በቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ ለክልሎች እና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተመደበው የፌደራል መንግሥት የበጀት ድጋፍ፤ ከዘንድሮው ጋር ሲነጻጸር በ92 ቢሊዮን ብር አድጓል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ሰኔ […]

ትራምፕ በሎስ አንጀለስ በሺዎች ወታደሮች ማሰማራታቸውን “የአምባገነን ቅዠት” ሲሉ የግዛቲቷ አስተዳዳሪ ፈረጁ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 11 ሰኔ 2025, 08:14 EAT የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ስደተኞችን መክበብ እና በቁጥጥር ስር ማዋል ፖሊሲ ጋር ተያይዞ በተነሳው ተቃውሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች መሰማራታቸውን “የአምባገነን ፕሬዚዳንት ቅዠት” ሲሉ የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ ዘለፉ። ተቃውሞ በሌሎች ከተሞች የተዛመተ ሲሆን ሎስ አንጀለስን የምትካተትበትን የካሊፎርኒያን ግዛት የሚያስተዳድሩት ጋቪን ኒውሶም “ሁኔታውን ያቀጣጠለው ትራምፕ” ነው ሲሉ […]

ዩኬ ቀኝ አክራሪ የእስራኤል ሚኒስትሮችን በፍልስጤማውያን ላይ ‘ጥቃት በማነሳሳት’ ማዕቀብ ጣለች

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 11 ሰኔ 2025, 09:25 EAT ዩናይትድ ኪንግደም ሁለት የእስራኤል ቀኝ ዘመም ሚኒስትሮች እስራኤል በኃይል በያዘችው ዌስት ባንክ “በፍልስጤም ማኅበረሰቦች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት በማነሳሳት” ማዕቀብ ጥላለች። ኢትማር ቤን ጋቪር እና በዛለል ስሞትሪች የተባሉት ሚኒስትሮቹ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እንዳይገቡ እና በዩኬ ያላቸውን ንብረትም እንዳያንቀሳቀስ እግድ እንደተጣለባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ማክሰኞ ዕለት […]

እውን ኮካ እና የድንች ጥብስ መጠቀም ለማይግሬን ህመም መፍትሔ ይሆናል?

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 11 ሰኔ 2025, 06:38 EAT በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያሰቃይ ህመም ነው። የሰዎችን ወደፊት፣ የሥራ ሁኔታ ይለውጣል፤ ዓለማቸውንም ያጠብባል። ለዚህም ነው “የሚፈውስ” መፍትሔ ተገኘ ወይም በትንሹ እንኳ ማይግሬን ህመምን ያስታግሳል ነው ሲባል ሰዎች የሚሞክሩት። ለማይግሬን ህክምናዎች ቢኖሩም በሽታውን ጨርሶ የሚያጠፋ መፍትሔ የለውም። በትዕዛዝ የሚሰጡ መድኃኒቶች በጣም ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ፤ […]

እስራኤል ታዋቂዋ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሬታ ቱንበርግን ከአገር ማባረሯን ገለጸች

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 11 ሰኔ 2025, 08:21 EAT ስዊዲናዊቷ ተሟጋች ግሬታ ቱንበርግ እና 11 ሰዎች ለጋዛ እርዳታ ጭነው በመርከብ ሲሄዱ በአለም አቀፍ ውሃ ላይ በእስራኤል ከተያዙ ከአንድ ቀን በኋላ ከአገር እንድትባረር መደረጉን እስራኤል አስታወቀች። ግሬታ ከአገር ለመውጣት መስማማቷን ተከትሎ ማክሰኞ ዕለት ከቴላቪቭ ወደ ፈረንሳይ መብረሯን የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ፓሪስ አየር ማረፊያ […]

በፍቅር አጋሩ መጠጥ ላይ የጽንስ ማቋረጫ እንክብል ‘የጨመረው’ አሜሪካዊ በግድያ ወንጀል ተከሰሰ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ከ 9 ሰአት በፊት የፍቅር አጋሩ ሳታውቅ መጠጧ ላይ የጽንስ ማቋረጫ እንክብል ጨምሯል የተባለው አሜሪካዊ በግድያ ወንጀል ተከሰሰ። ጀስቲን አንቶኒ ባንታ የተባለው ግለሰብ ለቀድሞ ፍቅረኛው ፕላን ሲ የተባለውን የጽንስ ማቋረጫ መድኃኒት ሳታውቅ እንደሰጣት ግለሰቧ መክሰሷን ተከትሎ ነው ባለፈው ሳምንት አርብ በቁጥጥር ስር የዋለው። በግለሰቡ ላይ ለወራት የዘለቀ ምርመራ መደረጉን የቴክስሳስ […]