ብቸኛው ሞርጌጅ ባንክ 80 ሚሊዮን ብር አተረፈ
በዳዊት ታዬ November 27, 2024 የ2016 ሒሳብ ዓመት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት በኢትዮጵያ ብቸኛው የግል ሞርጌጅ ባንክ በመሆን ኢንዱስትሪውን የተቀላቀለው ጎህ ቤቶች ባንክ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በኋላ 80.1 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ፡፡ ባንኩ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በኋላ ያገኘው ትርፍ ከቀዳሚው ዓመት ከ77 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው መሆኑንም የባንኩ የ2016 ሒሳብ ዓመት ሪፖርት አመልክቷል፡፡ […]
በትግራይ ክልል ሕገወጥ የወርቅ ምርት ምክንያት የሕፃናትና የባህላዊ አምራቾች ሕይወት አደጋ ላይ መውደቁ ተገለጸ
በናርዶስ ዮሴፍ November 27, 2024 በትግራይ ክልል ሕገወጥ የወርቅ ምርት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ሕፃናት በሜርኩሪ ምክንያት፣ እንዲሁም ባህላዊ ወርቅ አምራቾች ለሕጋዊ ወርቅ አምራቾች በተሰጡ ቦታዎች ላይ እስከ 30 ሜትር የዘለቀ የወርቅ ቁፋሮ ላይ በመሰማራታቸው ሕይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው በማዕድን ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በሚሊኒየም አዳራሽ ለሦስተኛ ጊዜ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ […]
የተገፉ እናቶችን ያጠነከረው ድጋፍ
የማነ ብርሃኑ November 27, 2024 ምን እየሰሩ ነው? በሴቶችና ሕፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራው ፍቅር ለሕፃናትና ለእናቶች የበጎ አድራጎት ድርጅት የተመሠረተው በ2007 ዓ.ም. ነው፡፡ በችግር ምክንያት ተገፍተው ከነልጆቻቸው ጎዳና የወደቁ እናቶችንና ሕፃናትን በማንሳት መሠረታዊ ፍላጎታቸው ተሟልቶላቸው እንዲኖሩ የማድረግ ዓላማንም የሰነቀ ነው፡፡ ድርጅቱ ከጎዳና ያነሳቸውን ሕፃናት፣ በሕፃናት መዋያ እያዋለ የምግብ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም በልጆቻቸው […]
‹‹ካለፈው ስህተታችን እየተማርን ካልሄድን ለመጪው ትውልድ የምናፍርበትን ጠባሳ ጥለን እንሄዳለን›› ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሐፊ
ማኅበራዊ ‹‹ካለፈው ስህተታችን እየተማርን ካልሄድን ለመጪው ትውልድ የምናፍርበትን ጠባሳ ጥለን እንሄዳለን›› ቀሲስ… በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: November 27, 2024 በሱራፌል አሸብር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰላም ጥሪ አቀረበ፡፡ ጉባዔው ማክሰኞ ኅዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በሰጠው መግለጫ፣ ‹‹ካለፈው ስህተታችን እየተማርን ካልሄድን ለመጪው ትውልድ የምናፍርበትን ጠባሳ ጥለን እንሄዳለን›› ሲልም ጥሪ አቅርቧል፡፡ መንግሥት […]
ሦስቱን የአባላዘር በሽታዎች ለመግታት
ማኅበራዊ ሦስቱን የአባላዘር በሽታዎች ለመግታት የማነ ብርሃኑ ቀን: November 27, 2024 ኤችአይቪ ኤድስ፣ ቂጥኝና ሔፒታይተስ ቢ ከእናት ወደ ልጅ በመተላለፍ የእናትን፣ የሕፃንንና የቤተሰብን አኗኗር የሚያቃውሱ ተላላፊ የአባላዘር በሽታዎች ናቸው፡፡ ራስን በመጠበቅ ተላላፊነቱን መቆጣጠር የሚቻል ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ችግሩ ሲከሰት ይስተዋላል፡፡ ከችግሮቹ ዋነኛውም የግንዛቤ እጥረት ነው፡፡ ጤና ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት በአዳማ ከተማ ለሚዲያ ባለሙያዎች ባዘጋጀው መድረክ […]
የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎችና ተሟጋቾች በሚደርስባቸው ጫና አገር ጥለው መሰደዳቸው ተገለጸ
ዜና የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎችና ተሟጋቾች በሚደርስባቸው ጫና አገር ጥለው መሰደዳቸው ተገለጸ ሲሳይ ሳህሉ ቀን: November 27, 2024 የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶችና የመብት ተሟጋቾች በፀጥታ አካላት የሚደርስባቸው ወከባ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ በፍጥነት ሊቀረፉ ይችላሉ የሚል ተስፋ የነበረ ቢሆንም ምንም ዓይነት መሻሻል እንዳልታየባቸውና በርካቶች አገር ጥለው እየተሰደዱ መሆናቸውን፣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል አስታወቀ፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በኢትዮጵያ ከሰብዓዊ […]
በአቶ አብነት ገብረ መስቀል የገንዘብ ዕግድ ይነሳልኝ አቤቱታ ላይ መቃወሚያ ቀረበ
ዜና በአቶ አብነት ገብረ መስቀል የገንዘብ ዕግድ ይነሳልኝ አቤቱታ ላይ መቃወሚያ ቀረበ ዮናስ አማረ ቀን: November 27, 2024 ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ውድቅ በተደረገው የአቶ አብነት ገብረ መስቀል የገንዘብ ዕግድ ይነሳልኝ ጥያቄ ላይ በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ጠበቆች መቃወሚያ ቀረበበት፡፡ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአንድም ሁለት ጊዜ ውድቅ የተደረገው የአቶ አብነት የዕግድ ይነሳልኝ ጥያቄ […]
የግል ኩባንያዎች ነዳጅ አስመጥተው ለአገር ውስጥ ገበያ የማቅረብ ንግድ ላይ እንዲሰማሩ ሊፈቀድ ነው
በዮሐንስ አንበርብር November 27, 2024 ኢትዮጰያ ከውጭ የምታስገባው ነዳጅ የሚከማችበት የጂቡቲ ሆራይዘን ዴፖ መንግሥት ለበርካታ ዓመታት በብቸኝነት የያዘውን ነዳጅ አስመጥቶ ለአገር ውስጥ ገበያ የማቅረብ ንግድን ለግል ኩባንያዎች የመፍቀድ ውጥን መያዙን፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናገሩ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራለትን የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ በዝርዝር […]
ተጨማሪ በጀቱ የዋጋ ንረቱን እንዳያባብስና የግብር ጫና እንዳያመጣ ሥጋት ፈጥሯል
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ዜና ተጨማሪ በጀቱ የዋጋ ንረቱን እንዳያባብስና የግብር ጫና እንዳያመጣ ሥጋት ፈጥሯል ሲሳይ ሳህሉ ቀን: November 27, 2024 መንግሥት ለ2017 ዓ.ም. ያቀረበው ተጨማሪ በጀት የዋጋ ንረቱን እንዳያባብሰውና በግብር ከፋዩ ኅብረተሰብ ላይ ጫና እንዳያመጣ ሥጋት እንዳላቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተላከለትን የፌዴራል መንግሥት […]
የሕዝብ አስለቃሹ የሙስናው ራስ ኢሚግሬሽን ቢሮ ዋና ሃላፊ የብልፅግና ፓርላማ ጥሪ ረግጠው ከሃገር ወጡ
November 27, 2024 ” ዋና ኃላፊዋ በሀገር ውስጥ የሉም። ነገር ግን ደብዳቤያችን ከደረሳቸው በኃላ ነው የወጡት ” – የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት አመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት […]