መከላከያ ሠራዊት ጄነራል ምግበይ ኃይለ ላይ ያቀረበውን ክስ የትግራይ የሰላምና የጸጥታ ቢሮ “ኃላፊነት የጎደለው ነው” አለ

24 መጋቢት 2025 የትግራይ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ብርጋዲየር ጄነራል ምግበይ ሃይለን “ለፋኖ ድጋፍ ይሰጣሉ” የሚለውን ጨምሮ ሌሎችም ያቀረባቸውን ክሶች ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲል ወቀሰ። የሰላምና ጸጥታ ቢሮው፤ “እሳቱ ባለበት ለማርገብ ከመጣር ይልቅ ማርገብገብ፣ ላጋጠመህ የራስ ችግር ለተግባራዊ መፍትሔ ከመጣር ይልቅ የማይመለከተው ኣካል በመፍጠርና ጣት በመቀሰር ሰላምና ዕድገትን እንዳይጸና የሚያደርግ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” […]

‘ምግብ ተቆጣጥሮኝ ነበር’፡ 191 ኪሎግራም በመቀነስ ከሞት አፋፍ የተመለሰው ሰው

24 መጋቢት 2025 አዮን ፖላርድ ሆስፒታል አልጋ ሲይዝ 286 ኪሎግራም ነበር የሚመዝነው። ኩላሊቱ መሥራት እያቆመ ነበር። ለአንድ ቀንም በሕይወት ስለመቆየቱ እርግጠኛ አልነበረም። በወቅቱ 27 ዓመቱ ነበር። ኩላሊቱ በቀዶ ሕክምና መቀየር ነበረበት። ነገር ግን ከልክ ባለፈ ውፍረቱ ምክንያት ቀዶ ሕክምናው ሊካሄድ አልቻለም። “ሰውነቴ እስከሚችለው ድረስ ራሴን እየገፋሁ ነበር። ሐኪሞቹ ቀጣዩቹ ስምንት ሰዓታት በሕይወቴ ቁልፍ ሰዓታት መሆናቸውን […]

በስኮትላንድ በታዳጊው አሜን ተክላይ ግድያ ሶስተኛ ተጠርጣሪ ተያዘ

24 መጋቢት 2025, 08:00 EAT በስኮትላንድ፣ ግላስጎው ነዋሪ የነበረው ታዳጊ አሜን ተክላይ ግድያ ጋር በተያያዘ ሶስተኛ ተጠርጣሪ ተያዘ። የ15 ዓመቱ አሜን ከሶስት ሳምንታት በፊት በከተማዋ ሜሪሂል አካባቢ ክላሬንደር ጎዳና ላይ በተፈጸመበት ጥቃት በጸና ቆስሎ መገኘቱ ይታወሳል። ምንም እንኳ የድንገተኛ ሕክምና ባለሙያዎች በስፍራው ቢደርሱም ሕይወቱ እዚያው ማለፉ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት የ16 ዓመት ታዳጊ የሆነው ሶስተኛው ተጠርጣሪ […]

በአንድ ወቅት በሩሲያ ሥር የነበረው የአሜሪካ ደሴት

24 መጋቢት 2025 ኡናላስካ ደሴት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ወታደራዊ መቀመጫ ነበር። ፓስፊክ ውቅያኖስና ቤሪንግ ባሕር የሚገናኙበት ቦታ ላይ ይገኛል። ከሰሜን አሜሪካ ወደ ሰርቢያ ሲጓዙ ነው ይህንን የአሜሪካ ደሴት የሚመለከቱት። ወደ ምሥራቅ እስያ ቅርብ ስለሆነ ከአላስካ ሩቅ ደሴቶች አንዱ ነው። በምድር ላይ ከባድ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል። 1,100 ማይል የሚሰፋው የአሉይታን ደሴት አካልም ነው። […]

እስራኤል የጋዛው ሆስፒታል ላይ ባደረሰችው ጥቃት በህክምና ላይ የነበሩ የሐማስ ኃላፊ ተገደሉ

24 መጋቢት 2025 እስራኤል እሑድ አመሻሹን ጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ባደረሰችው ጥቃት ነባር የሐማስ አመራር እና ረዳታቸው መገደላቸውን ሐማስ ለቢቢሲ አሳወቀ። በኻን ዩኒስ ግዛት ናስር ሆስፒታል ላይ በደረሰው ጥቃት የሐማስ የፋይናንስ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ኢስማኢል ባርሁም መገደላቸው ተሰምቷል። ግለሰቡ ከአራት ቀናት በፊት በእስራኤል ጥቃት በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በሆስፒታሉ ሕክምና እያገኙ እንደነበር የሐማስ ባለሥልጣን ለቢቢሲ […]

የቱርኩ ፕሬዝደንት ተቀናቃኛቸውን ማሰራቸውን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ተፋፋመ

24 መጋቢት 2025 የፕሬዝደንት ጣይብ ረሲፕ ኤርዶዋን ቀንደኛ ተቀናቃኝ በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተከትሎ በመላው ቱርክ የተነሳው ከፍተኛ ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል። ኤክሬም ኢማሞግሉ የኢስታንቡል ከንቲባ ሲሆኑ ባለፈው ከሶስት ዓመታት በኋላ ለሚካሄደው ምርጫ የሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ (ሲኤችፒ) ዕጩ ሆነው እሑድ ዕለት ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ሰውየው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ ቱርክ ላለፉት 10 ዓመታት አይታ በማታወቅ ተቃውሞ […]

ከአሜሪካ የተባረሩት የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር በአገራቸው ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

24 መጋቢት 2025 የትራምፕን አስተዳደር አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ከአሜሪካ እንዲባረሩ የተደረጉት የደቡብ አፍሪካው አምባሳደር በአገራቸው ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። አምባሳደር ኢብራሂም ራሱል እሁድ ዕለት፣ መጋቢት 14/ 2017 ዓ.ም በኬፕታውን በሚገኘው ዓለም አቀፉ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። አምባሳደሩን በአየር ማረፊያው ሲጠባበቁ የነበሩ የአፍሪካ ናሺናል ኮንግረስ ፓርቲ፣ የደቡብ አፍሪካ ኮሚዩኒስት […]

ቴክኖሎጂ በረቀቀበት ዘመን የመሬት መንቀጥቀጥን መገመት ለምን ከባድ ሆነ?

24 መጋቢት 2025 ብሬንት ደሚትራክ ራሱን የርዕደ መሬት ነቢይ ሲል ይጠራል። ባለፈው ጥቅምት አጋማሽ በ10 ሺዎች ለሚቆጠሩ የማኅበራዊ ሚድያ ተከታዮቹ በምዕራባዊ ካሊፎርኒያ የመሬት መንቀጥቀጥ ይከሰታል ሲል ተናገረ። ከሁለት ወራት በኋላ 7.3 ሬክተር ስኬል የሆነ ርዕደ መሬት ሰሜናዊ ካሊፎርኒያን ነቀነቃት። በዚህ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሥፍራው ነዋሪዎች በሱናሚ እንመታለን የሚል ስጋታቸው ጨመረ። የብሬንት ተከታዮችም ቁጥር ያሻቅብ ጀመር። […]

Ethiopia’s army claims to have killed 300 Fano fighters in renewed clashes  – Al Jazeera

News|Conflict The armed group contradicts the army’s claim of having ‘destroyed’ the former ally in the Amhara region. Published On 22 Mar 202522 Mar 2025 Ethiopian troops have killed more than 300 Fano armed group fighters, former allies against rebels in the Tigray region, in two days of renewed clashes in the northern Amhara region, according to […]

Drone attacks killing hundreds of civilians across Africa, says report – The Guardian

Calls grow to control military use of unmanned aerial vehicles which, despite claims of precise targeting, are claiming civilian lives Mark Townsend Mon 10 Mar 2025 07.00 GMT Almost 1,000 civilians have been killed and hundreds more injured in military drone attacks across Africa as the proliferation of unmanned aerial vehicles continues unchecked on the continent, according […]