ማይክ ሐመር እና ጌታቸው ረዳ

September 13, 2024 – Konjit Sitotaw  በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር፣ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ጥቅምት 23 ሁለተኛ ዓመቱን ከመድፈኑ በፊት የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ የመበተንና መልሶ የማቋቋም መርሃግብር ማስጀመር እንደሚያስፈልግ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር ትናንት ተወያይተዋል። ጌታቸውና ሐመር፣ ወደ ጦርነት መመለስ አማራጭ እንዳልኾነና የፖለቲካ ልዩነቶችን በንግግር መፍታት እንደሚያስፈልግም ተስማምተዋል። ጌታቸው […]

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም የትግራይ ፖለቲከኞች ችግሮቻቸው በሰላም እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ

September 13, 2024 – DW Amharic  የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም የትግራይ ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በሰላም እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ። የቀድሞው የህወሓት ከፍተኛ አመራር የተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት ሰላም ሊያደፈርስ እንደማይገባ ገልጸዋል። የትግራይ የፀጥታ ኃይሎች የጊዚያዊ አስተዳደሩን ተግባራት የመከልከል ኃላፊነት እንደሌላቸው አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ብርሃኑ ጁላ ለዘላበደው ሕገወጥ ንግግር ማብራሪያ ይሰጠኝ ሲል ኦብነግ ጠየቀ

September 13, 2024 – Konjit Sitotaw  ኦብነግ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ኦብነግ “በግብጽ ድጋፍ የተቋቋመ የኢትዮጵያ ጠላት ነው” በማለት ተናግረውታል በተባለ በበይነ መረብ በተሠራጨ ንግግር ዙሪያ ማብራሪያ ጠይቋል። ኦብነግ፣ የኤታማዦር ሹሙ ንግግር “መሠረተ ቢስ”፣ “በሕጋዊነቱ ላይ የተቃጣ” እና “በሰላም ሂደቱ ላይ የተፈጸመ ትንኮሳ” ነው ብሏል። ፓርቲው፣ መንግሥት የንግግሩን “ትክክለኛነት እንዲያረጋግጥ” እና “ትክክለኛ […]

በአፅዋማት የታጠረው የዘንድሮው አዲስ ዓመት መግቢያ

September 13, 2024 – DW Amharic የዘንድሮ አዲስ ዓመት በፆም ቀን መዋሉ በተለይ የኦርቶዶክስ ክርስትና በሚከተሉ አማኞች ዘንድ በዓሉን አንድ ወት በሆነ የእርድ ስነስርዓት ለመፈፀም አላስቻላቸውም። አንዳንዶቹ በዋዜማው እርድ ሲያከናውኑ፣ ሌሎች ደግሞ በበዓሉ ቀጣይ ቀን ዛሬ እርድ ፈፅመዋል፣ ብዙዎቹ ደግሞ ከቅዳሜ ጀምሮ እርድ ለማከናወን ቀጠሮ የያዙ ናቸው።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የቀጠለው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሀገራት ውዝግብ

September 13, 2024 – DW Amharic  የኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ውል መደበኛ ሥምምነት ሆኖ እንደሚፈረም የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ለዲፕሎማቶች ተናግረዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የግብጽ ወታደሮች በሶማሊያ መሠማራት ለሶማሊላንድ አሳሳቢ ብለውታል። ሶማሊላንድ በሐርጌሳ የሚገኝ የግብጽ ባሕላዊ ቤተ-መጻህፍት ዘግታ ሠራተኞቹ በ72 ሰዓታት ለቀው እንዲወጡ አዛለች።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሱዳን ግጭት በኢትዮጵያ የስደተኞችን ቀውስ አባብሷል

September 13, 2024 – DW Amharic  በቅርቡ በቤኒሻንጉል የተከፈተው መጠለያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሱዳናዉያንን ያፈናቀለዉ የርስ በርስ ጦርነትን የሸሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች መኖሪያ ሆኗል። ከ50,000 በላይ ሱዳናዊያን ተፈናቃዮች ኢትዮጵያ ዉስጥ ተጠልለዋል። አትዮጵያ በአጠቃላይ አንድ ሚሊዮን ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። 3.5 ሚሊዮን የዉስጥ ተፈናቃዮችም አልዋት።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ደቡብ ምዕራብ ሸዋ የከፋው የግጭት ተጽእኖ እንዲቆም፤ ግልጽ ደብዳቤ

September 13, 2024 – DW Amharic  የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጻፉት ደብዳቤ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች 79 ሰዎች መገደላቸውን ገለጹ። ነዋሪዎቹ ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ጭምር እንዲደርስ እንፈልጋለን ባሉት ደብዳቤ “ከታጣቂዎቹ ወግነዋል” በሚል ክስ የ21 ሰዎች ቤቶች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መቃጠላቸውን አስታውቀዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያም – የኢትዮጵያ አብዮት 50ኛ ዓመት

September 13, 2024 – DW Amharic  የቀድሞው የደርግ ሊቀመንበር የኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ከልጅነት አንስቶ ዛሬ እስካሉበት የስደት ዘመን ድረስ የተጓዙባቸውን ግላዊ ታሪኮች፣ የሕይወት ገጠመኞች እና ወቅታዊና ነባር ፖለቲካዊ ግምገማዎችን -አካተዉ መንግሥቱ ኃ/ማርያም፡ የስደተኛው መሪ ትረካዎች በቅርቡ በመጽሐፍ መልክ ለአንባብያን ቀርቧል። አብዮቱ ከፈነዳ ዛሬ ልክ 50ኛ ዓመቱ!… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ