የአውሮፓ ኅብረት ባወጣው ሕግ ሳቢያ ቡና ላኪዎች ኤክስፖርት ለማድረግ እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ

በተመስገን ተጋፋው September 25, 2024 የአውሮፓ ኅብረት ቡናን ጨምሮ ወደ አባል አገሮቹ የሚላኩ ሰባት የምርት ዓይነቶች ከደን ጭፍጨፋና መመናመን ነፃ መሆናቸው ሳይረጋገጥ፣ ለግብይት እንዳይቀርቡ የሚከለክል ሕግ በማውጣቱ ምክንያት፣ በርካታ ቡና ላኪዎች ወደ አውሮፓ ኤክስፖርት ለማድረግ መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ የአርፋሳ ጄኔራል ትሬዲንግ ኤክስፖርት ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ንጉሤ ለገሠ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአውሮፓ ኅብረት ቡናን ከደን ጭፍጨፋና መመናመን […]

ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት ዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት በቅርቡ በቻይና ይፋ እንደሚደረግ ተገለጸ

የቻይና ኤምባሲ የአፍሪካ አገሮች ዲፕሎማቶች በተገኙበት ውይይት ሲደረግ ዜና ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት ዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት በቅርቡ በቻይና ይፋ እንደሚደረግ ተገለጸ ሲሳይ ሳህሉ ቀን: September 25, 2024 ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካና ከእስያ 19 አባል አገሮችን በመሥራችነት የያዘው ዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት፣ በመጪው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት በቻይና ሆንግ ኮንግ ይፋ እንደሚደረግ ተገለጸ፡፡ በዓለም አቀፍ ድንበር ተሻጋሪ ወይም […]

ለአፍሪካ ኅብረት የተለያዩ ተልዕኮዎች ከ600 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ድጋፍ ፀደቀ

ዜናፖለቲካ በናርዶስ ዮሴፍ September 25, 2024 በአውሮፓ ኅብረት ሥር የሚገኘው የአውሮፓውያን የሰላም ፋሲሊቲ ለአጋር የአፍሪካ አገሮች፣ በሁለት መስኮች ከ600 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ድጋፍ ማፅደቁ ተገለጸ።  ይህ የተነገረው ትናንት ማክሰኞ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም. በአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድን መሪ ዣቪየር ኒኖ ፔሬዝ (አምባሳደር) በሁለቱ ኅብረቶች መካከል ስላሉ የጥምረት ሥራዎችና የጋራ እ.ኤ.አ. በ2030 ድረስ […]

ለአማራ ተወላጅ እስረኞችና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ዜና ለአማራ ተወላጅ እስረኞችና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ ዮናስ አማረ ቀን: September 25, 2024 ያለ ፍርድ በማረሚያ ቤት ተይዘው የሚገኙ ታዋቂ የአማራ ተወላጅ እስረኞችን ለመደገፍና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት፣ ታዋቂው ፖለቲከኛ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጥሪውን ያቀረቡት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ […]

የሕወሓት ሊቀመንበር ከእሳቸው በተቃራኒ የቆሙ አመራሮችን መውቀስ ጀመሩ

ዜና የሕወሓት ሊቀመንበር ከእሳቸው በተቃራኒ የቆሙ አመራሮችን መውቀስ ጀመሩ ልዋም አታክልቲ ቀን: September 25, 2024 ‹‹ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ የያዘውን ቂም እኔ ላይ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ላይ እንዲወጣ አልፈቅድም›› ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሕወሓት ሊቀመንበር ‹‹እኔ በማንም ላይ የያዝኩት ቂም የለም››  ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በትግራይ ጦርነት ወቅት የተፈጠሩ ልዩነቶችን በማስታወስ፣ በአሁኑ ጊዜ ከእሳቸው ተቃራኒ የቆሙ የሕወሓትና የትግራይ ጦር ከፍተኛ አመራሮችን በአደባባይ መውቀስ […]

ነዳጅ ከጂቡቲ በተጨማሪ በበርበራ ወደብ ለማስገባት የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

በሔለን ተስፋዬ September 25, 2024 በጂቡቲ የሚገኘው ሆራይዘን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ በጂቡቲ የሚገኘው ሆራይዘን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ የሚሰጠው አገልግሎት አቅም በመቀነሱ ምክንያት፣ ከጂቡቲ በተጨማሪ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ በኩል ነዳጅ ለማስገባት ምክረ ሐሳብ ቀርቦ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው። በጂቡቲ የሚገኘው ሆራይዘን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ የሚሰጠው አገልግሎት አቅም መቀነሱ፣ በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል እየፈጠረ መሆኑን፣ በነዳጅና […]

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የህወሓት ቡድን አስጠነቀቁ።

September 25, 2024 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የህወሓት ቡድን አስጠነቀቁ። ፕሬዜዳንቱ በማስጠንቀቂያቸው ” ቡድን ” ሲሉ የጠሩት ሃይል የወረዳና የከተማ የህዝብ ምክር ቤቶች ለመረበሽ እየሄደበት ያለው ርቀትና በማድረግ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት ብለዋል። መስከረም 14/2017 ዓ.ም በፕሬዜዳንቱ ፊርማ ተፈርሞ ለሁሉም የወረዳና የከተማ ም/ቤቶች የተፃፈው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ ” የህዝብ […]

Egypt Sends Military Aid to Somalia as Territorial Tensions with Ethiopia Persist  – Army Recognition 05:12 

On Tuesday, September 24, 2024, Egypt confirmed it had sent military aid to Somalia, demonstrating its support for the Horn of Africa nation, currently in conflict with Ethiopia over a breakaway territory. This aid comes in the midst of growing tensions between Somalia and Ethiopia, aggravated by the issue of Somaliland’s recognition, a region that seceded from […]

የብራንድንበርጉ አካባቢያዊ ምርጫ ውጤትና አንድምታው

September 25, 2024 – DW Amharic FDP ከSPD እና ከአረንጓዴዎቹ ፓርቲዎች ጋር የሚያቀራርቡት ጥቂት ጉዳዮች ብቻ ናቸው። በዚህም FDP በበርሊኑ ጥምር መንግሥት ውስጥ መቀጠል አለመቀጠሉ እያነጋገረ ነው። ፓርቲው ከጥምሩ መንግሥት እንዲለቅ የሚወተውቱት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ጥምረቱ እስከ መጪው ገና ይቀጥላል ብለው አያምኑም ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ