የአዲስ አበባ ፖሊስ አርቲስት አንዷለም ጎሳን ከዕጮኛው ሞት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር እንዳዋለው ገለጸ

11 መጋቢት 2025 ተሻሽሏል ከ 5 ሰአት በፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ ታዋቂው ድምጻዊ አንዷለም ጎሳን ከዕጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ጋር በተያያዝ በቁጥጥር ስር አውሎት ምርመራ እያደረገበት መሆኑን አስታወቀ። ቀነኒ አዱኛ መጋቢት 01/2017 ዓ.ም. ሌሊት 10 ሰዓት አካባቢ እጮኛዋ ጋር ከሚኖሩበት ሕንጻ 5ኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መውደቋ ለህልፈቷ ምክንያት መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል። […]

ትግራይ ውስጥ እየሆነ ያለው ምንድን ነው?

11 መጋቢት 2025 ለወራት የቆየው በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው አለመግባባት ተባብሶ እንደቀጠለ ነው። ባለፉት ወራት በደብረፂዮን (ዶ/ር) የሚመራው ወገን የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥልጣን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎች ሲወስድ ቆይቷል። በአቶ ጌታቸው የሚመራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርም ይህ ሙከራ በክልሉ አለመረጋጋት በማስፈን ያለውን ችግር እንደሚያባብስ በመግለጽ ቢያስጠነቅቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጥረቱ እየተባባሰ ይገኛል። ባለፉት ቀናት በክልሉ ያሉት ታጣቂ ኃይሎች […]

አቶ ጌታቸው የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል ጣልቃ ለመግባት በቂ ምክንያት እንዳለው ተናገሩ

ከ 3 ሰአት በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን ጨምሮ “የትኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለማድረግ” በቂ ምክንያት እንዳለው ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ጉዳይ ከትግራይ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው። ግማሽ ሰዓት ገደማ በፈጀው ቃለ መጠይቅ በቅርቡ ስላገዷቸው የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች እና በክልሉ ስለነገሰው ውጥረት […]

በአዲስ አበባ የንግድ ባንክ ጥበቃ ሠራተኛ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ

ከ 4 ሰአት በፊት በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ካርል አደባባይ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለቢቢሲ ተናገረ። ክስተቱ ያጋጠመው ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም. ሲሆን፤ ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው ‘የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም’ በሚል ምክንያት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። […]

በዓመት አንድ ጊዜ የሚወሰደው የኤችአይቪ መከላከያ ክትባት ወሳኝ የደኅንነት ሙከራን አለፈ

ከ 5 ሰአት በፊት የኤችአይቪ ቫይረስን ይከላከላል የተባለው እና በየዓመቱ የሚሰጠው ክትባት ከደኅንነት አንጻር አስተማማኝ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን ወሳኝ የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራ ማሟላቱን ተመራማሪዎች ያወጡት ሪፖርት አመለከተ። ሌናካፓቪር የተባለው ይህ ፀረ ኤችአይቪ ክትባት ቫይረሱ በሰዎች ህዋሳት ውስጥ እንዳይባዛ የሚያደርግ አቅም እንዳለው ላንሴት በተባለው የሕክምና መጽሔት ያወጣው ሪፖርት ያሳያል። አሁን ወሳኝ የተባለው ይህንን የመጀመሪያ ደረጃ የደኅንነት […]

በህሙማን ላይ የወሲብ እና የቁማር ሱስ ያስከተለው መድኃኒት

ከ 9 ሰአት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ከቁጥጥር የወጣ የሰውነት እንቅስቃሴ ህመም (movement disorders) የገጠማቸው ሴቶች የተሰጣቸው መድኃኒት ያለው የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልተነገራቸው ለቢቢሲ ገለጹ። ሕክምና ከወሰዱ መካከል 20 ሴቶች ለቢቢሲ እንደገለጹት የተሰጣቸው መድኃኒት “አሉታዊ ወሲባዊ ባህሪ” እንዲያዳብሩ የሚያደርግ መሆኑ አልተነገራቸውም። መድኃኒቱ ሕይወታቸውን እንዳመሳቀለውም ተናግረዋል። ጂኤስኬ የተባለው መድኃኒት አምራች ድርጅት ባወጣው እና ቢቢሲ በተመለከተው ሪፖርት ላይ […]

የዩኤስኤይድ ሠራተኞች ምስጢር የያዙ ወረቀቶችን እንዲያቃጥሉ ትዕዛዝ ተሰጣቸው

ከ 8 ሰአት በፊት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዩኤስኤይድ) ሠራተኞች ምስጢራዊ መረጃ የያዙ ወረቀቶችን እንዲያቃጥሉ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ተሰማ። ይህ ትዕዛዝ መሰጠቱ ሠራተኞችን ግራ ያጋባ ሲሆን ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ ይችላል የሚለውን ግምትም ያጠናከረ ሆኗል። የድርጅቱ ጊዜያዊ ፀሐፊ የሆኑት ኤሪካ ዋይ ካር ለሠራተኞቻቸው በላኩት ኢሜል ከዋሺንግተን ቢሮ ምስጢራዊ እና ግላዊ መረጃዎችን በማስወገዳቸው ምስጋና አቅርበዋል። ሠራተኞቹ […]

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የ30 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

ከ 8 ሰአት በፊት የአሜሪካ እና የዩክሬን ባለስልጣነት በሳዑዲ አረቢያ ካደረጉት የአንድ ቀን ወይይት በኋላ ዩክሬን በአሜሪካ የቀረበውን የ30 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን ተናግራለች። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሃሳቡን ለሩሲያ እንደሚያቀርቡ እና “ኳሱ በነሱ ሜዳ መሆኑን” ተናግረዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ እንዳሉት አሁን ሩሲያ “በአዎንታዊ” ሐሳብ እንድትስማማ ማሳመን የአሜሪካ […]

በርካታ አፈታሪኮች፣ ምልኪዎች እና ትንግርቶች ያሏት ሙሉ ጨረቃ

ከ 9 ሰአት በፊት ሙሉ ጨረቃ በምትታይበት ወቅት አስገራሚ ክስተቶች እንደሚፈጠሩ ለዘመናት በርካታ አፈ ታሪኮች ተነግረዋል። አማልክት የሚገለጡበት፣ ከሰው ወደ ተኩላነት መቀየር፣ አዕምሯቸው የሚሰወር. . . ሌላም ሌላም ሙሉ ጨረቃ ስትታይ የሚካሄዱ ፌስቲቫሎች፣ ምልኪዎች ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ባለው ዘመን ቀጥለዋል። ሙሉ ጨረቃ በየወሩ በ29ኛው ቀን ትከሰታለች። መሬት በፀሐይ እና በጨረቃ መካከል ስትሆን ጨረቃዋ ሙሉ ሆና፣ […]

በትግራይ ክልል ላለው ወቅታዊ ሁኔታ፤ የፌደራል መንግስት “አስፈላጊውን ድጋፍ” እንዲያደርግ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አሳሰበ    – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

March 12, 2025 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ “በጸጥታ ኃይሎች ስም” እየተንቀሳቀሱ ባሉ አካላት፤ “የፕሪቶሪያ ውል ሲፈርስ እና የትግራይ ህዝብ ወደ ዳግም ጥፋት ሲገባ ዝም ተብሎ መታየት የለበትም” አለ። የፌደራል መንግስት እነዚህ አካላት የትግራይ ህዝብንም ሆነ ጊዜያዊ አስተዳደሩን የማይወክሉ መሆኑን ተገንዝቦ “አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ አለበት” ብሏል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በትግራይ ክልል ያለውን “ወቅታዊ ሁኔታ” በተመለከተ […]