ከዩክሬን ጋር በተያያዘ ከሚካሄደው አዲስ ንግግር በፊት አሜሪካ፣ ሩሲያ እና አውሮፓ ምን እያሰቡ ይሆን?

ከ 5 ሰአት በፊት ለዓለም አቀፍ ፖለቲካ ሌላ የተመሰቃቀለ ሳምንት ሆኖ አልፏል። ዓለም በዶናልድ ትራምፕ እና በቮልዲሚር ዜሌንስኪ መካከል ያልተለመደ የተባለውን የተካረረ የቃላት ልውውጥ በቀጥታ ተከታትሎታል። የዩክሬን መሪ መከላከያቸውን ለማጠናከር ወደ ተግባር የገቡትን የአውሮፓ አጋሮቻቸውን ጎብኝተዋል። የሩስያ ቦምቦች ዩክሬንን ላይ በተከታታይ መዝነባቸውን ቀጥለዋል። ነገር ግን እነዚህ ዋና ዋና ተዋንያን በሚቀጥለው ሳምንት በሳዑዲ አረቢያ እንደ አዲስ […]

በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የነበሩባቸው ጀልባዎች ተገልብጠው 180ዎቹ ደብዛቸው ጠፋ

8 መጋቢት 2025 ከጂቡቲ የተነሱ ስደተኞችን ያሳፈሩ ጀልባዎች ከየመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጠው የደረሱበት ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን የሚገኙባቸው ከ180 በላይ ስደተኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ። አደጋው የደረሰባቸው ጀልባዎች ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ተነስተው የተሻለ ሕይወትን ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲሁም የባሕረ ሰላጤው አገራት በሕገወጥ እና በአደገኛ መንገድ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞችን ያሳፈሩ ነበሩ። በጀልባዎቹ […]

አሜሪካ ከ15 ዓመታት በኋላ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው በአልሞ ተኳሾች የሚፈጸም የሞት ቅጣት

ከ 7 ሰአት በፊት በአሜሪካ ከአስራ አምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ አንድ ሞት የተፈረደበት እስረኛ በአልሞ ተኳሾች በጥይት አርብ ዕለት ተገድሏል። የደቡብ ካሮላይና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብራድ ሲግሞን የተሰኘው ፍርደኛ የሞት ቅጣቱ በጥይት ተፈጻሚ እንዲሆንበት ብይኑን ረቡዕ ዕለት ነበር ያስተላለፈው። በሕጉ መሠረት የዓይን እማኞች ግድያው ሲፈጸም እንዲከታተሉ ተፈቅዶላቸዋል። ነገር ግን ከዚህ ጋር ተያይዞ ስጋቶች መነሳታቸው አልቀረም። […]

ታዋቂዋ ደራሲ ቺማማንዳ በእርግዝናዋ ወቅት “መጻፍ ተቸግሬ ነበር” አለች

ከ 7 ሰአት በፊት ታዋቂዋ ደራሲ ቺማማንዳ ንጎዚ አዲቼ የመጀመሪያ ልጇን አርግዛ በነበረበት ወቅት “አስደንጋጭ በሆነ መልኩ መጻፍ አልቻልኩም ነበር” ትላለች። “በዚህ ሁኔታ ላይ መገኘት በጣም አስፈሪ ነው። ምክንያቱም ለሕይወቴ ትርጉም የሚሰጠኝ መጻፍ ብቻ ነው” ስትል የ47 ዓመቷ ተወዳጇ ናይጄሪያዊት ደራሲ ለቢቢሲ ተናግራለች። “[ክስተቱ] ሙሉ በሙሉ አካላዊ ስለመሆኑ እርግጠኛ አልነበርኩም። ነገር ግን አንድ የሆነ ነገር […]

የሶሪያ የጸጥታ ኃይሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁኃንን ገድለዋል የሚል ክስ ቀረበባቸው

ከ 7 ሰአት በፊት የሶሪያ የጸጥታ ኃይሎች በአገሪቱ የባሕር ዳርቻ አካባቢው በቀጠለው አለመረጋጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአላዋይት ማኅበረሰብ አባላትን ገድለዋል የሚል ውንጀላ ቀረበባቸው። መቀመጫውን በብሪታንያ ያደረገው የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ (SOHR)፣ አርብ እና ቅዳሜ በአላዋይት ማኅበረሰብ አባላት ላይ ባነጣጠረ ጥቃት 30 “ጭፍጨፋዎች” ተካሄደዋል ያለ ሲሆን በአጠቃላይ 745 ንፁኃን ዜጎች ተገድለዋል ብሏል። ቢቢሲ ይህንን መረጃ ከገለልተኛ ወገን […]

የአብይ አህመድ የባህር ወደብ ፕሮፖጋንዳ ባዶነት

Mengistu Musie የአብይ አህመድ የባህር ወደብ ፕሮፖጋንዳ ባዶነት ====================== የአብይ አህመድ ፕሮፖጋንዳ መረብ እና የዲጅታል ሰራዊቱ እስከ ወዶ ገብ ግለኞች በአማራ ሕዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ ሰላማዊ ዜጎችን በየቀኑ የመግደል ጀኖሳይዳል ጦርነትን ለማለባበስ በየግዜው ወደማህበራዊ ሚዲያ የሚገፋው ፕሮፖጋንዳ ተፈጻሚነት የለውም፡፡ ምናልባት ለአንድ አመት ግዜ ከሶማሌ ላንድ ጋር ውል ፈጸምን በሚል እና የባሕር በር ተገኘ ብለው […]

‹‹የምግብ ደኅንነት ችግራችንን ለመቅረፍ ከግብርና እስከ ገበያ የሚመራ ባለሥልጣን መዋቀር አለበት›› አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የምግብና የሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር

ምሕረት ሞገስ March 9, 2025 ቆይታ አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የምግብና የሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምግብና በሥነ ምግብ ሳይንስ አግኝተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2007 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሪነት፣ በአስተማሪነት፣ በረዳት ፕሮፌሰርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ አሁን በተባባሪ ፕሮፌሰርነት እየሠሩ […]

ከድህነት ማጥ ውስጥ ለመውጣት ሁሉም ዘርፎች ትኩረት ይሻሉ!

March 9, 2025 ርዕሰ አንቀጽ መሰንበቻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሆሚቾ ጥይት ፋብሪካ ጉብኝታቸው ባደረጉት ንግግር፣ ከዚህ ቀደም በአገር ውስጥ ተተኳሽ ጥይቶችን የማምረት ሙከራዎች ቢኖሩም ከሦስት ዓመታት በፊት ድረስ ከውጭ ስታስገባ እንደነበርና አሁን ግን እዚሁ በማምረት ለውጭ የመላክ አቅም መገንባቱን ገልጸዋል፡፡ ለበርካታ አገሮች ጥይቶች ለመሸጥ ስምምነት መፈጸሙን፣ በሦስት ወራት ውስጥ 30 ሚሊዮን ዶላር ያህል […]

በሕግ አምላክ የሚለው የፖለቲካ ትግላችን

ተሟገት በሕግ አምላክ የሚለው የፖለቲካ ትግላችን አንባቢ ቀን: March 9, 2025 በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ ላይ የጣለው ልዩ ልዩነታችን በጭራሽ አይደለም፡፡ ሕመማችን፣ ጠንቀኛው በሽታችን ራሱ ልዩ ልዩነታችን ቢሆን ኖሮማ የዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብታችንና ነፃነታችን ሕጎች በልዩ ልዩነታችን ልክ በነፃ እንድንደራጅ፣ በዚያው ልክ የተለያዩ አመለካከቶችን በነፃነት እንድንገልጽ ባልፈቀዱ፣ ባልደነገጉ፣ ለዚህም […]

አገር በቀል መፍትሔ የሚሹት ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች

የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ማኅበር ከተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን አምስተኛ ዓመታዊ የተዋልዶ ጤና ጉባዔውን ባደረገበት ወቅት ማኅበራዊ አገር በቀል መፍትሔ የሚሹት ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አበበ ፍቅር ቀን: March 9, 2025 በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በኩል ይሰጥ የነበረው ዕርዳታ በመቋረጡ በርካታ ድርጅቶች ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍ […]