መንግሥት ገቢ ከመሰብሰብ ባሻገር ለሕዝብ ኑሮ ትኩረት ይስጥ!

January 19, 2025 ርዕሰ አንቀጽ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማደግ ያለበት በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ከሚሰበሰብ ታክስ ብቻ ሳይሆን ከግብርና፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከማዕድን፣ ከአገልግሎትና ከሌሎች ሀብት አመንጪ ዘርፎች ጭምር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ ያለ ተደራራቢ ታክሶች፣ የመንግሥታዊ አገልግሎቶች ክፍያና ታሪፍ ጭማሪዎች፣ የትራፊክ ቅጣትና ሌሎች ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የታክስና የቀረጥ ገቢዎች በዜጎች ኑሮ ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ […]

የኢትዮጵያን ትንሳዔ ለማብሰርና ለመከወን ምን እናድርግ?

እኔ የምለዉ የኢትዮጵያን ትንሳዔ ለማብሰርና ለመከወን ምን እናድርግ? አንባቢ ቀን: January 19, 2025 በጌታነህ አማረ ኢትዮጵያ ማለት ታላቅ አገር ቀደምት የሰው ዘር መገኛና የሥልጣኔ ባለቤት የሆነች አገር እንደነበረች ታሪክ ሲያወሳን ይኖራል። በዚያውም ልክ ይህች ታላቅ ነበረች የምትባል አገር አሁን ላይ በድህነት፣ በጦርነት፣ በግጭትና በስደት እየተሰቃየች የምትገኝ አገር አንድ ቀን ተመልሳ ታላቅና በዓለም ላይ ስሟ ከፍ […]

የምድራችን (የሰው ልጆች) ተማፅኖ — አረንጓዴ ፖለቲካ!

ተሟገት የምድራችን (የሰው ልጆች) ተማፅኖ — አረንጓዴ ፖለቲካ! አንባቢ ቀን: January 19, 2025 (ወጥመዶችና ማምለጫችን) በታደሰ ሻንቆ የወጥመዶች ዓለም በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ዘንድ ያሉ ውዝግቦችና ግጭቶች ምንም ተቀባቡ ምን፣ መሬትን ውኃን አፈርን ማዕድናትን ንግድንና መሰል ጥቅሞችን የተመለከቱ ናቸው፡፡ በእነዚህ ውዝግቦች ውስጥ ትናንትናን ለዛሬ ማጣቀስ እንዳለ ሁሉ፣ ‹ይህ አገር ከተመዘዘ ለጥቅሜ አይተኛምና ከወዲሁ ላዳቀው› የሚል ሁሉ ሥሌት […]

‹‹መንግሥት ከሁሉም ነገር በላይ ቅድሚያ ሰጥቶ የኢኮኖሚ ጫናውን ለመቀነስ የነዳጅ ድጎማውን መቀጠል ይኖርበታል›› ሰርካለም ገብረ ክርስቶስ (ዶ/ር)፣  የነዳጅ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ

ዳዊት ታዬ January 19, 2025 ቆይታ የነዳጅ ግብይት ሥርዓትን ለመዘርጋትና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ አዲስ አዋጅ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡ በኢትዮጵያ በነዳጅ ሥርጭት ግብይትና በአጠቃላይ በዘርፉ ያሉትን ማነቆዎች ሊያቃልል ይችላል የተባለው ይህ አዋጅ፣ አሁንም ክፍተት እንዳለበት እየተገለጸ ነው፡፡ በፀደቀው አዋጅና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ የነዳጅ ግብይት ላይ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች መካከል […]

ስለካፒታል ገበያ ምንነትና ፋይዳ ያልተቋረጠና የተብራራ መረጃ ማድረስ ያሻል!

January 19, 2025 ናታን ዳዊት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡ አገራዊ ኢኮኖሚውን ከመደገፍና ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች የሚውል ካፒታል ለማሰባሰብ እንደ አንድ አማራጭ የሚወሰድና ለኢትዮጵያ እንደ አዲስ ምዕራፍ የሚታይ ዕርምጃ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ረዥም ዕድሜ ያለው አገር ካፒታል ገበያ ብርቅ ሆኖባት እስከዛሬ መቆየቱ አግባብ እንዳልነበር ካሰብንም ገበያው ዘግይቶም ቢሆን መጀመሩ እንደ አገር ትልቅ […]

የመገለጡ ቀን እና ትውፊቱ

የጥምቀት ክብረ በዓል በምንጃር ሸንኮራ ኢራንቡቲ ኪንና ባህል የመገለጡ ቀን እና ትውፊቱ ሔኖክ ያሬድ ቀን: January 19, 2025 ከአንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ስድስት ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ማለትም ጥር 11 ቀን 31 ዓ.ም. (5531 ዓመተ ዓለም) ሰማያዊው በመሬታዊው እጅ የተጠመቀበት ነው፡፡ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 ዓመቱ በመጥምቁ (አጥማቂው) ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀበትን ቀኑን በማስታወስም […]

የባህልና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል በጎንደር

ዝንቅ የባህልና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል በጎንደር በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: January 19, 2025 የአማራ ክልል ለ16ኛ ጊዜ ያዘጋጀው የባህልና ኪነጥበብ ፌስቲቫል ከጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት በጎንደር ከተማ ተካሂዷል። ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በፌስቲቫሉ ላይ የተለያዩ የዞንና የወረዳ የባህልና የኪነጥበብ ቡድኖች ባህላዊና ኪነጥበባዊ ትዕይንታቸውን በመስቀል አደባባይ አቅርበዋል። ፎቶዎቹ የፌስቲቫሉን ልዩ […]

በምርጫ ወቅት ማጭበርበር አምስት ዓመታት እንደሚያስቀጣ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዜና በምርጫ ወቅት ማጭበርበር አምስት ዓመታት እንደሚያስቀጣ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ ዮናስ አማረ ቀን: January 19, 2025 የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ን ለመተካት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተረቀቀው አዲስ አዋጅ፣ በተጭበረበረ መረጃ ለመወዳደርና ለመመረጥ የሚሞክሩ ግለሰቦችን በአምስት ዓመት እስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ […]

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት ዲፕሎማሲዊ ትርፍ ወዴት ያመዝን ይሆን?

ፖለቲካ በሲሳይ ሳህሉ January 19, 2025 የጋራ ጠላትን በአንድ የተባበረ ክንድ ለመዋጋት፣ ቀጣናዊ ጠንካራ የጋራ ኃይል ለመገንባት፣ የጋራ ኢኮኖሚና የገበያ ትስስር ለመፍጠር፣ ግጭቶችን፣ ድንበር ዘለል የሽብር እንቅስቃሴና አዋኪ ኃይልን በኅብረት ለመከላከል በሚል የሁለትዮሽና የሦስትዮሽ ወይም ቁጥራቸው የበዙ የአገሮች ወደ አንድ በመምጣት የወዳጅነት ስምምነት (Pact) ፈጥረው የተሳካ ሥራን ሲያናውኑ የተስተዋሉባቸው ክስተቶች ብዙ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል መረጃዎች […]

መነሻቸውን ከደቡብ አሜሪካ ያደረጉ አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በቦሌ ኤርፖርት ጠንካራ ፍተሻ እንዲደረግባቸው ተጠየቀ

መግለጫው በተሠጠበት ወቅት ዜና መነሻቸውን ከደቡብ አሜሪካ ያደረጉ አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በቦሌ ኤርፖርት ጠንካራ ፍተሻ እንዲደረግባቸው… ሲሳይ ሳህሉ ቀን: January 19, 2025 መነሻቸውን በተለይ ከደቡብ አሜሪካ አድርገው በኢትዮጵያ በኩል በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የሚተላለፉ ዕፅ አዘዋዋሪዎች፣ በአካላቸው ውስጥ ይዘውት የሚንቀሳቀሱትን አደገኛ ዕፅ ለመያዝ ጠንካራ ፍተሻ የሚያደርግ ማሽን እንዲተከል ተጠየቀ፡፡ መቀመጫውን ሆንግ ኮንግ ያደረገውና ቮይስ ፎር […]