የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን የንጹሐን ግድያ ቀጥሏል።
January 8, 2025 ታጣቂዎች አደረሱት በሚባል ጥቃት ከዘጠኝ ዓመታት በላይ የንጹሐን ግድያ ልጓም ባልተገኘለት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን አሁንም “ ንጹሐን ተገድለዋል ” ተብሏል። ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የዞኑ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ባለፉት 48 ሰዓታት ብቻ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ” ብለዋል። በዞኑ ኬረዳና ጀሎ በተሰኙት ቀበሌዎች አንታዮ ዦላና አድማሱ […]
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ፤ ተማሪዎች በምግብ ጥራት እና መጠን ላይ ያሰሙት ሮሮ
January 8, 2025 – DW Amharic የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “አዲሱ የምግብ ባጀት ተግባራዊ እንደሆነ ቢነገረንም የሚቀርብልን ምግብ በጥራትም ሆነ በመጠን የተሻሻለ ነገር የለም” ብለዋል። የተማሪዎች ህብረትም የተማሪዎ ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ከመስራት ይልቅ እንቅፋት ሆኗል ነው ያሉት፣ ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ባጀቱን ተግባራዊ ማድረግ እንዳልጀመረ አመልክቷል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
ትግራይ፤ ዛሬም ድንኳን ዉስጥ የሚኖሩት የጦርነት ተፈናቃዮች
January 8, 2025 – DW Amharic በትግራይ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጦርነቱ ተፈናቃዮች አሁንም በመጠልያዎች ዉስጥ ናቸው። ተፈናቃዮቹ መንግስት ረስቶናል፣ በበሽታና ሌሎች ችግር እያለቅን ነው የሚሉ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ ወደቀዬአቸው ሊመልሷቸው ጥሪ ያቀርባሉ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ለመመለስ እቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑ ይገልፃል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተፈተኑ አካባቢዎች የገና በዓል አከባበር
January 7, 2025 – DW Amharic በአፋር ክልል ዞን 03 ሁለት ወረዳዎች በተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የዘንድሮን ገና በዓል እንደ አቀዱት ሳይሆን ባላሰቡት እያሳለፉ መሆናቸዉን ገለፁ። ግጭት ባሉባቸዉ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችም ከዘመድ ከአዝማዱ መገናኘት ቀላል እንዳልሆነ የገና በዓልን እንደለመዱት እና እንደምመኙት ደማቅ አለመሆኑን ተናግረዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
የፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሥራች ዣን ማሪ ለ ፔን አረፉ
January 7, 2025 – VOA Amharic በጸረ ስደተኛ እና በመድብለ ባሕላዊ ኅብረተሰብ ጠል ንግግራቸው የሚታወቁት የፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሥራች ዣን ማሪ ለ ፔን በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በከረረው ቀኝ ክንፍ አቋማቸው ብርቱ ደጋፊዎች የነበሯቸው እና በተቃዋሚዎቻቸው በስፋት ይወገዙ የነበሩት የብሔራዊ ግንባር ፓርቲው መሥራች ማረፋቸውን የፓርቲያቸው ፕሬዝደንት ዦርዳን ባርዴላ ዛሬ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስታ… … […]
“በዚህች ቤተክርስቲያን ያለን አንድ መሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው” ሩሲያውያን እና ዩክሬናውያን
ከ 2 ሰአት በፊት አገሮቻቸው በጦርነት እየተፋለሙ የሚገኙት ሩሲያውያን እና ዩክሬናውያን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበትን የገና በዓል በድምቀት አክብረዋል። በአንዳንድ ስፍራዎች ደግሞ ክርስቲያናዊ ቤተሰብነት ይቀድማል በሚል በአንድነት ነው ያከበሩት ነው። በዩናይትድ ኪንግደም፣ በርሚንግሃም በሚገኝ በአንድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የልደት በዓልን በአንድ ላይ ያከበሩት ሩሲያውያን እና ዩክሬናውያን ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነትን በተላበሰ መልኩ ዕለቱን አስበውታል። በበርሚንግሃም […]
በትግራይ ወርቅ ለማውጣት የሚውሉ አደገኛ ኬሚካሎች የደቀኑት ከባድ አደጋ
ከ 9 ሰአት በፊት ከሁለት ዓመቱ ደም አፋሳሽ ጦርነት ማብቃት በኋላ በትግራይ ክልል ሕገወጥ የማዕድን ማውጣት ተግባር በስፋት እየተካሄደ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተነገረ ነው። በዚህ ሕገወጥ የማዕድን ማውጣት ሂደት በትግራይ ኃይሎች ውስጥ የሚገኙ ግለሰቦች፣ የፀጥታ ኃላፊዎች እንዲሁም በክልሉ አስተዳደር ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እጃቸው እንዳለበት ነዋሪዎች እና በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ ባለሥልጣናት ያምናሉ። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት […]
የቤንዚን የችርቻሮ ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመቶ ብር ተሻገረ
ከ 3 ሰአት በፊት የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመቶ ብር ተሻገረ። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማክሰኞ ምሽት፣ ታኅሳስ 29/ 2017 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቋል። ማሻሻያውን ተከትሎ 91 ብር ሲሸጥ የነበረው ቤንዚን ብር 101.47 ገብቷል። በዚህም መሰረት የቤንዚን ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመቶ ብር ተሻግሯል። […]
የአሜሪካዋ ሎስአንጀለስ በሰደድ እሳት ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አወጀች
ከ 5 ሰአት በፊት የእሳት ሰደድ በከፍተኛ ሁኔታ የተዛመተባት የአሜሪካዋ ግዛት ሎስአንጀለስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች። እሳት ሰደዱ ከ10 ሄክታር ተነስቶ በሰዓታት ውስጥ ወደ 2 ሺህ 900 ሄክታር መዛመቱን ተከትሎ ነው ይሄ እርምጃ የተወሰደው። የሰደዱ አደጋ የተጋረጠባቸው 30 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ እንደተላለፈላቸው እና 13 ሺህ ህንጻዎች አደጋ ላይ መሆናቸውን የግዛቲቱ የእሳት […]
የጣልያኗ መንደር ነዋሪዎቿ እንዳይታመሙ ከለከለች
ከ 8 ሰአት በፊት አንዲት የጣልያን መንደር ነዋሪዎቿ በጠና እንዳይታመሙ ከለከለች። ቤልካስትሮ የተሰኘችው መንደር ነዋሪዎች “አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ከሚያስፈልገው ማንኛውም በሽታ እንዳይያዙ” መመሪያ እንደተላለፈላቸው የአካባቢው ከንቲባ አንቶኒዮ ቶርቺያ ተናግረዋል። ቤልካስትሮ በደቡባዊ ካላብሪያ የምትገኝ እና አነስተኛ እና ድሃ ከሆኑ መንደሮች አንዷ ናት። ከንቲባው መመሪያው “ግልጽ በሆነ መልኩ ቀልድን የተላበሰ እርምጃ” መሆኑን ገልጸው ነገር ግን የአካባቢው የጤና […]