በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ምን አይነት ጥንቃቄ ልናድርግ ይገባል?
ከ 6 ሰአት በፊት በኢትዮጵያ ባለፉት ወራት በተለይ በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በየቀኑ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው። በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ በሚገኙ ሠፍራዎች የመሬት መሰንጠቅ ተከስቷል። ዶፈን በተባለው ተራራ ላይ ደግሞ መሬት ፈንድቶ ጋዝ እና ድንጋይ ሲተፋ ታይቷል። በበርካታ ሥፍራዎች ፍል ውሀ እየፈለቀም ይገኛል። በተለይ በአዋሽ፣ መተሐራ እና አቦምሳ አካባቢዎች የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በአዲስ አበባ […]
“ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም” የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ከ 1 ሰአት በፊት ከኢትዮጵያ ጋር የባህር በር መግባቢያ ስምምነት የተፈራረመችው ራሷን እንደነጻ አገር ያወጀችው የሶማሊላንድ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም” አሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዲራህማን ዳሂር አደን አገራቸው ዕውቅና ማግኘትን ከፍ ያለ ስፍራ ብትሰጠውም “ህዝባቸውንንም ሆነ አገራቸውን የሚጎዳ መሆን የለበትም” ሲሉ ታህሳስ 27/ 2017 ዓ.ም በፓርላማ ባደረጉት ንግግር አብራርተዋል። […]
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በበረዶ ውሽንፍር በተመቱባት አሜሪካ ሰባት ግዛቶቿ የአስቸኳይ ጊዜ አወጁ
ከ 1 ሰአት በፊት በአሜሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በበረዶ ውሽንፍር መመታቸውን ተከትሎ ሰባት ግዛቶቿ የአስቸኳይ ጊዜ አወጁ። በአገሪቱ በአስር ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የክረምት አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ቅዝቃዜ እና በረዶ ያስከትላል የሚል ትንበያን ተከትሎ ከ60 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አሜሪካ እንዲጠነቀቁ መመሪያ ተላልፏል። አብዛኛው የካናዳ እና ከካንሰስ እስከ ኢስት ኮስት ያሉ 30 የአሜሪካ ግዛቶች በዚሁ የአየር […]
ሩሲያ ጋዜጠኛዬ በዩክሬን የድሮን ጥቃት ተገደለብኝ አለች
ከ 5 ሰአት በፊት መንግሥታዊው የሩሲያ ጋዜጣ ኢዝቨስቲያ ሪፖርተር በዩክሬን ጥቃት መገደሉን ሩሲያ አስታወቀች። ጋዜጠኛው የተገደለው ሩሲያ በተቆጣጠረቻት በዩክሬን ምስራቃዊዋ ግዛት ዶኔትስክ ነው። ሩሲያ የዩክሬን ጦር ጋዜጠኛውን አሌክሳንደር ማርቴምያኖቭን አነጣጥሮ ገድሎታል ስትል ወንጅላለች። ዩክሬን ጥቃቱን በተመለከተ እስካሁን የሰጠችው አስተያየት የለም። ሪፖርተሩን የጫነ የሲቪል መኪና በድሮን ጥቃት እንደተፈጸመበት ኢዝቪስቲያ ጋዜጣ አስታውቋል። በዚሁ ጥቃት ሌሎች አራት የሚዲያ […]
እስራኤልና አሜሪካን የሚገዳደረው በኢራን የሚመራው ቡድን በቀጣይ ምን ይጠብቀዋል?
ከ 6 ሰአት በፊት በኢራን የሚደገፈው የአሳድ መንግሥት መውደቅ ‘አክሲስ ኦፍ ሬዚስታንስ’ ለሚባለው ቡድን ጥሩ ዜና አይደለም። ይህ ጥምረት በመካከለኛው ምሥራቅ ቁልፍ ከሆኑት አንዱ ነው። ይህን ቡድን ካዋቀሩ አንዱ የሆኑት ቃሲል ሱሌይማኒ ባግዳድ ውስጥ ከተገደሉ አምስት ዓመት ተቆጥሯል። የኢራን ልዩ ኃይል ኮማንደር ነበሩ። ኢራን በቀጠናው ያላትን እንቅስቃሴ በመንደፍ ዋነኛው ሰውም ነበሩ። ሱሌይማኒ ከመገደላቸው ከሦስት ወራት […]
ሞተር ብስክሌት የሚያክለው ቱና ጃፓን ውስጥ በ1.3 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ
ከ 5 ሰአት በፊት በጃፓኗ ቶኪዮ የሞተር ብስክሌት ክብደት እና ስፋት ያለው ብሉፊን የተባለ ቱና በ207 ሚሊዮን ዩን ተሸጧል። ገንዘቡ ወደ ዶላር ሲመነዘር 1.3 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ነው። የቶኪዮ የሱሺ (ጥሬ ዓሳ) ሬስቶራንቶች ናቸው ግዙፉን ዓሳ የገዙት። ብሉፊን ቱና እጅግ ተወዳጅ ከሆኑ ዓሳዎች መካከል ነው። ቶዮሱ በተሰኘው የቶኪዮ የዓሳ ገበያ በየዓመቱ ጨረታ ይካሄዳል። ከዚህ ቀደም […]
ለካንሰር ህክምና ሲባል የአንዲት ሴት ስምንት የአካል ክፍሎቿ እንዲወገዱ ተደረገ
ከ 5 ሰአት በፊት ብዙም ያልተለመደ ካንሰር እንዳለባት በመታወቁ ስምንት የአካል ክፍሎቿ እንዲወገድላት የተደረገች ሴት ህክምናዋን ጨርሳ ወደ ሥራዋ ተመለሰች። በዩናይትድ ኪንግደም ዌስት ሱሴክስ ሆርሻም ነዋሪ የሆነችው ፌይ ሉዊዝ እአአ በ2023 ትርፍ አንጀቷ ላይ ዕጢ ከተገኘ በኋላ ስለቀብር ሥነ ሥርዓትቷ ዕቅድ ማውጣት ጀምራ ነበር። “የቀዶ ህክምናዎች ሁሉ ቁንጮ” ከተባለለት ህክምና በኋላ ግን ከካንሰር ነጻ በመሆኗ […]
ኢትዮጵያዊነት አሰባሳቢ የፖለቲካ አጀንዳ ወይስ አራት ኪሎ የመግቢያ ትኬት
ፖለቲካ በዮናስ አማረ January 5, 2025 ወደ 252 ገጣሚያንና ጸሐፍት ተወዳድረው በ1984 ዓ.ም. የፀደቀው በአሥር ስንኞችና በ45 ቃላት ተቀምሮ የቀረበው የዜግነት ክብር የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ስለኢትዮጵያዊነት ጥልቅ ሐሳብ መያዙን ገጣሚው ይናገራል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያዊነት ሰውነት ነው›› ሲል ይናገራል፡፡ ዛሬ በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ግጥምን የጻፈው ደረጀ ይርጋ የዛሬ ስድስት ዓመት ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር […]
ከገና ገበያ
ማኅበራዊ ከገና ገበያ አበበ ፍቅር ቀን: January 5, 2025 በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ የሆነው የገና በዓል በየዓመቱ ታኅሣሥ 29 በድምቀት ይከበራል፡፡ የእግዚ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በተለይ በኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ይታሰባል፡፡ በዓሉ ከመንፈሳዊነቱም ባሻገር በባህላዊ ክንዋኔዎች የሰዎችን የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ የገና […]
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ማድረጊያ በሁሉም ነዳጅ ማደያዎች ሊተከል መሆኑ ተነገረ
የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር ማድረጊያ ቦታ ማኅበራዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ማድረጊያ በሁሉም ነዳጅ ማደያዎች ሊተከል መሆኑ ተነገረ ሔለን ተስፋዬ ቀን: January 5, 2025 በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች ሁለት፣ ሁለት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ማድረጊያ እንዲተክሉ ሊደረግ መሆኑን፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ በሚገኙ በእያንዳንዳቸው ማደያዎች ሁለት ሁለት የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ ለመትከል ከኩባንያዎች ጋር መግባባት ላይ […]