ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ የተባለውን አገልግሎት መስከረም ላይ በኢትዮጵያ እንደሚጀምር ገለጸ

ከ 13 ደቂቃዎች በፊት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፤ ኤም-ፔሳ የተሰኘው የሞባይል ገንዘብ መላላኪያ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር ገለጸ። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እናት ድርጅት የሆነው ቮዳኮም ግሩፕ ሊሚትድ የኤም-ፔሳ አገልግሎት መስከረም 2016 ዓ.ም. አጋማሽ እንደሚጀመር ገልጧል። ቮዳኮም ግሩፕ የ2023 አንደኛ ሩብ ዓመት በዳሰሰበት መግለጫው በሁለተኛው ሩብ ዓመት ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ይጀምራል። እአአ ጥቅምት 2022 ሥራ የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከ2.7 ሚሊዮን […]

ከፍርድ ውጪ ለዓመታት ታስረዋል የተባሉ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች እንዲለቀቁ ተጠየቀ

ከ 20 ደቂቃዎች በፊት ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለዓመታት ታስረዋል የተባሉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራሮች እንዲለቀቁ ጠየቀ። ሂዩማን ራይትስ ዋች ባወጣው መግለጫ ሰባቱ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች በፖለቲካ ተሳትፏቸው ብቻ ለሦስት ዓመታት ያህል በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት የፍትሕ ሥርዓቱን ማሻሻል እንዳለበት ማሳያ ነው ብሏል። የሰብዓዊ መብት […]

ትዊተር አርማውን ከምናውቃት ወፍ ወደ ‘ኤክስ’ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ኢላን መስክ ገለጠ

ከ 5 ሰአት በፊት የትዊተር ባለቤት ኢላን መስክ የትዊተር ‘ሎጎ’ ከተለመደው የወፍ ምልክት ወደ ‘ኤክስ’ [X] ሊቀይር መሆኑን ገልጧል። ነገር ግን ኢላን መስክ ይህን አደርጋለሁ ብሎ ከመፈፀም ይቦዝናል፤ አሊያም ቁም ነገር ሳይሆን ዋዛ ሆኖ ይገኛል። የቢዝነስ አርማውን ወደ ኤክስ ኮርፕ የቀየረው መስክ “እንደውም ይህን ሊሆን የሚገባው ቀድሞ ነበር” ብሏል። ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ቢሊየነሩ ልክ እንደ ቻይናው […]

ሩስያ ሞስኮ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ ስትል ዩክሬንን ወቀሰች

ከ 5 ሰአት በፊት ሩስያ ሰኞ ንጋት ዩክሬን ሞስኮ ከተማ ላይ በፈጸመችው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት በሁለት ሕንጻዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገለጸች። የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ሁለቱ ድሮኖች ተመትተው እንዲወድቁ መደረጋቸውን እና በድሮን ጥቃቱ ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አስታውቋል። በሩስያ መንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደረው ታስ የተባለው የዜና ወኪል ሁለተኛው ድሮን መከላከያ ሚኒስቴር ቢሮ አቅራቢያ ተመትቶ […]

ጠጥተው ሲያሸከረክሩ የተገኙት የኒው ዚላንድ ፍትሕ ሚንስትር ከሥራ ተሰናበቱ

ከ 2 ሰአት በፊት የኒው ዚላንድ የፍትሕ ሚንስትር ኪሪ አለን አልኮል ጠጥተው ማሸከርከራቸው በመረጋገጡ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥራ ተሰናበቱ። የፍትሕ ሚንስትሯ ሲያሸከረክሩት የነበረው መኪና ግጭት ከደረሰበት በኋላ በተደረገ የትንፋሽ ምርመራ የአልኮል መጠጥ መውሰዳቸው ተደርሶባታል። ይህንን ተከትሎም ሚንስትሯ ወዲያውኑ ተፈጻሚ የሚሆን በገዛ ፍቃድ ከሥራ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። የ39 ዓመቷ ኪሪ አለን በግዴለሽነት በማሽከርከር እና በፖሊስ ላለምታሰር በመገዳደር የሚል […]

ከሥራ የተሰናቱ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች 100 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው በፍርድ ቤት ተወሰነ

July 24, 2023 – EthiopianReporter.com  ከሥራ የተሰናቱ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች 100 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው በፍርድ ቤት ተወሰነ የፋብሪካውን ንብረት የዘረፉ እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል ተብሏል የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከሥራ አሰናነበትኳቸው ካላቸው 1,500 የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መካከል ለ965 ያህሉ 100 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው ፍርድ ቤት መወሰኑን፣ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ሠራተኞቹ በስኳር ኢንዱስትሪ…

ከሕንፃ ከፍታና ፕላን አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚደረግ ግንባታ እንዲቆም ታዘዘ

July 24, 2023 – EthiopianReporter.com  ከሕንፃ ከፍታና ፕላን አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚደረግ ግንባታ እንዲቆም ታዘዘ በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ራማዳ ሆቴል አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም ዓይነት ግንባታ እንዳይፈቀድና የተፈቀዱ ሕንፃዎችም ግንባታ እንዲቆም፣ የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አዘዘ፡፡ ተቋሙ ውሳኔውን ለማስተላለፍ የወሰነው ካለፈው ዓመት ጀምሮ የተለያዩ የከተማ ስታንዳርዶችን…

የጂቡቲ አሽከርካሪዎችን እንግልት ለሚቀንሰው የ142 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ የ40 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ፀደቀ

July 24, 2023 – EthiopianReporter.com  የጂቡቲ አሽከርካሪዎችን እንግልት ለሚቀንሰው የ142 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ የ40 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ፀደቀ የመንገዱ መገንባት እንግልት ቢቀንስላቸውም ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል አሽከርካሪዎች ገልጸዋል የአዲስ አበባና የጂቡቲ አካል ለሆነውና የአሽከርካሪዎችን እንግልት እንደሚቀንስ የተገለጸው ከሚኤሶ – ድሬዳዋ እየተገነባ ላለው የ142 ኪሎ ሜትር መንገድ፣ የዓለም ባንክ ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ…

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ረቂቅ መመርያዎች ለመዘጋት ይዳርጉናል አሉ

July 24, 2023 – EthiopianReporter.com  የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ረቂቅ መመርያዎች ለመዘጋት ይዳርጉናል አሉ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በቅርቡ ያዘጋጃቸው ረቂቅ መመርያዎች፣ ለመዘጋት እንደሚዳርጓቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገለጹ፡፡ ተቋማቱ በማኅበራቸው በኩል እንደገለጹት በመመርያዎቹ የተቀመጡ መሥፈርቶችን ለማሟላት ብዙዎቹ ተቋማት ስለማይችሉ፣ ለመዘጋት እንደሚዳረጉ ሥጋታቸውን ተናግረዋል፡፡ በተለይ ከፈቃድ አሰጣጥና ፈቃድ ዕድሳት…

ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ንረትን በአጭር ጊዜ ማረጋጋት ቀዳሚ ትኩረቱ መሆኑን አስታወቀ

July 24, 2023 – EthiopianReporter.com ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ንረትን በአጭር ጊዜ ማረጋጋት ቀዳሚ ትኩረቱ መሆኑን አስታወቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዋነኛነት ትኩረት አድርጎ እየሠራ ከሚገኝባቸው ሦስት ጉዳዮች ውስጥ ቀዳሚው፣ የዋጋ ንረትን በአጭር ጊዜ ማረጋገጥ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ለ20ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት አድርጎ ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው…