ቢሊዮን ዶላሮችን የሚያንቀሳቅሰው ሐማስ የገንዘብ ምንጩ ምንድን ነው? ድጋፍ፣ ግብር፣ ክሪፕቶካረንሲ . . .?
ከ 1 ሰአት በፊት ጋዛን ለዓመታት ሲያስተዳደር የቆው እና አሁን ከእስራኤል ጋር ከባድ ጦርነት ውስጥ የገባው ፍልስጤማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚያንቀሳቅስ ይነገራል። በዚህም የቡድኑ የገንዘብ የዝውውር ሥርዓት ውስብስብ ሲሆን፣ የገቢ ምንጩ ደግሞ ከጋዛ ሰርጥ እስከ መላው ዓለም የተዘረጋ ነው። ሐማስ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ኅብረት እና በበርካታ ምዕራባውያን አገራት […]
በግጭቶች ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ወሳኝ የምርምር ሥራቸው መስተጓጎሉን ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ ገለጹ
ከ 58 ደቂቃዎች በፊት ፕሮፌሰር ገቢሳ በትግራይ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ይሰሩት የነበረው የተዳቀለ የማሽላ ምርምር ሥራ ግጭት በመኖሩ ምክንያት መስተጓጎላቸውን ገለጹ። ፕሮፌሰር ገቢሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በትግራይ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተዳቀለ የማሽላ ምርምር ላይ እንደሚሠሩ አስታውሰው፣ በእነዚህ ክልሎች ውስጥ ባለፉት ዓመታት ግጭቶች በመኖራቸው የተነሳ ሥራቸው መስተጓጎሉን ገልጸዋል። ስትራይጋ የተሰኘውን አረም እና ድርቅን በሚቋቋሙ […]
ታሊባን ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን እያሰረ መሆኑን ተመድ ገለጸ
ከ 12 ደቂቃዎች በፊት ታሊባን አፍጋኒስታን ውስጥ ከጥቃት የተረፉ ሴቶችን ወደ እስር ቤት እየወሰደ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት አስታወቀ። ሴቶቹ የሚታሰሩት ለደኅንነታቸው ነው በሚል ሽፋን መሆኑን አክሏል። ከጥቃት የተረፉ ሴቶችን ለአእምሯዊና አካላዊ ጉዳት የሚያጋልጥ መሆኑን ተመድ ገልጿል። ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ማገገሚያና ማቆያ ማዕከሎችንም ታሊባን መዝጋቱን የተመድ ሪፖርት ይጠቁማል። በአፍጋኒስታን ወደ አመራር በተመለሰው ታሊባን ሥር የሴቶች አያያዝ […]
የእስራኤል ጦር ሦስት ታግተው የነበሩ የገዛ ዜጎቹን በስህተት መግደሉን አስታወቀ
ከ 45 ደቂቃዎች በፊት የእስራኤል ጦር ሦስት ታግተው የነበሩ የገዛ ዜጎቹን ጋዛ ውስጥ በስህተት መግደሉን አስታወቀ። የእስራኤል ጦር በሐማስ እገታ ስር የነበሩትን ሦስቱን ታጋቾችን የገደለው በጦር ቀጠና ውስጥ ለሠራዊት አባላቱ “አደጋ” ተደርገው በስህተት በመታየታቸው ነው ብሏል። ግድያውን በተመለከተ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ባወጡት መግለጫ “በከፍተኛ ሐዘን ልባችን ተሰብሯል። . . . ታግተው ቆይተው በተገደሉት ዜጎቻችን ሞት […]
አካል ጉዳተኞች በዐይናቸው መጫወት የሚችሉት አዲሱ የሙዚቃ መሣሪያ
ከ 54 ደቂቃዎች በፊት ሙዚቃ ሁሉን የሚያግባባ ቋንቋ ነው ይባላል። የሙዚቃ መሣሪያዎች ግን አካታችነት ይጎድላቸዋል። በክላሲካል ሙዚቃ ከዚህ ቀደም ያልነበረ የሙዚቃ መሣሪያ መነጋገሪያ ሆኗል። ለአካል ጉዳተኞች ታስቦ የተሠራ ነው። አሌሳንድሮ ቫዛና 26 ዓመቱ ነው። ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ሙዚቃ ይጫወታል። ፒያኖ፣ ጊታር እና ከበሮ ይችላል። በኤሌክትሪክ በሚሠራ ዊልቸር ነው የሚንቀሳቀሰው። ፍራጃይል ኤክስ የተባለ ሕመም ስላለበት እጆቹን […]
ኬንያ ነርሶችን ጨምሮ 2500 የተማሩ ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ ልትልክ ነው
ከ 48 ደቂቃዎች በፊት ኬንያ ክህሎት ያላቸውን ሠራተኞችን ለሥራ ለመላክ ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረሷን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ። ሁለቱ አገራት በደረሱት ስምምነት መሠረት ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 2ሺህ 500 የተማሩ ሠራተኞችን በመጀመሪያው ዙር ወደ ሳዑዲ እንደምትልክ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። “ከዚህ ቀደም የቤት ሠራተኞችን ነበር ስንልክ የነበረው። አሁን ግን ክህሎት ያላቸውን ሠራተኞች ወደ […]
ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለድ ያልከፈለችው በገንዘብ እጥረት አለመሆኑን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ
15 ታህሳስ 2023 ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የአንድ ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን ያልከፈለችው ሁሉንም አበዳሪዎች “በእኩል ለማስተናገድ” በሚል እንጂ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኖሮባት አለመሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር ይህንን የገለጸው ትላንት ሐሙስ ታህሳስ 4/2016 ዓ.ም. ከቦንዱ ገዢዎች ጋር የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ ዛሬ አርብ ባወጣው መግለጫ ነው። ከአንድ መቶ በላይ […]
በመርከቦች ላይ በቀጠለው ጥቃት ግዙፉ የመርከብ ጭነት አጓጓዥ በቀይ ባሕር በኩል ማለፍ አቆመ
15 ታህሳስ 2023 ግዙፉ የዴንማርክ የመርከብ ጭነት ማጓጓዣ ድርጅት ሜርስክ በደኅንነት ስጋት ምክንያት በቀይ ባሕር በኩል የሚያደርጋቸውን ጉዞዎች ማቆሙን አስታወቀ። ባለፉት ሳምንታት በቀይ ባሕር ላይ በዕቃ ጫኝ መርኮች ላይ የሚሳኤል እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቶች ሲፈጸሙ ቆይተዋል። ሜርስክ ባወጣው መግለጫ “በቅርቡ በቀጠናው በንግድ መርከብ ጭነቶች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ እና በመርከበኞች ደኅንነት ላይ ከፍተኛ አደጋን […]
በኦሮሚያ ያለውን ግጭት ተከትሎ ይፈጸማሉ የተባሉ ግድያዎች
December 15, 2023 – DW Amharic በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ሰላማዊ ዜጎችን ያልለየ ግድያ በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ይፈጸማል ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መንግስትን ወቀሰ ። እንደ ኦነግ መግለጫ ሰላማዊ ዜጎቹ የተለያዩ ስያሜዎች በመሰጠት በጠራራ ጸሃይ ሳይቀር ይገደላሉ ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ከኮንግረስማን ጆን ጀምስ ጋር በዋሽንግተን ውይይት አደረገ።
December 15, 2023 – Konjit Sitotaw የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ከኮንግረስማን ጆን ጀምስ ጋር በዋሽንግተን ውይይት አደረገ። የአፍሪካ ጉዳዮች ዴሬክተር ከሆኑት እና ባለፉት ሳምንታት በኢትዮጵያ ጉዳይ የአፍሪቃን ቀንድ ልዩ መልእክተኛ የሆኑትን አምባሳደር ማይክ ሃመርን ካናገሩት ከተከበሩ ጆን ጀምስ ጋር ጥልቅ ውይይት አድርገዋል። የምክር ቤቱ ሃላፊ ወኪሎች በወቅቱ የአምባሳደሩን እና ሌሎች ሃላፊዎችን ሪፖርትና የእለቱን ውይይት እንደገና በጥልቀት መምርመራቸውን […]