በኦሮሚያ ሕዝቡ ለአካላዊ፣ ስነ ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጋልጧል

December 9, 2023  ኢሰመጉ፣ በኦሮሚያ ክልል በታጣቂዎች በሚፈጸሙ “ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች” ሳቢያ ሕዝቡ ለአካላዊ፣ ስነ ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጋልጧል ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኢሰመጉ፣ የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ አካላት ወንጀል ሠርቶ ተጠያቂ ያለመኾን ባህል እንዲቀር ወንጀለኞች ለሕግ የሚቀርቡበትን ሥርዓት እንዲዘረጉ አሳስቧል። የክልሉ መንግሥት በቅርቡ በአርሲና ቄለም ወለጋ ዞኖች በበርካታ ንጹሃን ላይ ግድያ የፈጸሙና […]

አማራ ባንክን ከ460 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ዳርገዋል የተባሉት የባንኩን ዋና ስራ አስፈፃሚ ተባረሩ

December 9, 2023  ዋዜማ- አማራ ባንክ በዘርፈ ብዙ የአስተዳደር ቀውሶች ሲታመስ ሰንብቶ ባንኩን ከ460 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ዳርገዋል የተባሉት የባንኩን ዋና ስራ አስፈፃሚና ሌላ አንድ አመራር ከሀላፊነት ማሰናበቱን ዋዜማ አረጋግጣለች። በባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ የተፃፈውና (ዋዜማ የተመለከተችው) ለቦርድ አባላት የተሰራጨው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዋና አቶ ኄኖክ ከበደ ታደሰና […]

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ( ሸኔ) ታጣቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን አግተው ወሰዱ

December 9, 2023 – Konjit Sitotaw  የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ዋጫሌ ወረዳ፣ ጃቴ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ከሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። የቡድኑ ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ 75 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ከተማ ከዋናው አስፋልት መንገድ ላይ እገታውን የፈጸሙት፣ ረቡዕ’ለት ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ […]

ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር ያደረገችው ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ

December 9, 2023 – Konjit Sitotaw  ኢትዮጵያ በ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ አከፋፈል ላይ ከአበዳሪዎቿ ጋር ያደረገችው ድርድር ትናንት ያለ ውጤት እንደተጠናቀቀ ሮይተርስ ዘግቧል። ኢትዮጵያ በቀጣዩ ሰኞ በተቀመጠው ቀነ ገደብ የ33 ሚሊዮን ዶላር የቦንድ ወለድ መክፈል እንደማትችል ለአበዳሪዎቿ ማሳወቋን ዘገባው ጠቅሷል። ድርድሩ ያለ ውጤት መጠናቀቁ፣ ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳዋን መክፈል የማትችልበት ደረጃ ላይ መድረሷን ሊያሳይ እንደሚችል ዘገባው አመልክቷል። ኢትዮጵያ […]

የተጣላ ሳይታረቅ የማይከበረው አዲስ ዓመት – ድሽታ ግና

9 ታህሳስ 2023 በመላው አገሪቱ የሚከበረው የኢትዮጵያ ይፋዊ አዲስ ዓመት መስከረም 1/2016 ዓ.ም. ተጀምሮ ሦስተኛ ወሩን አገባዷል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ማኅበረሰቦች የራሳቸው የሆነ የአዲስ ዓመት አከባበር እና ባሕላዊ ሥነ ሥርዓቶች አሏቸው። በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የመስከረም ወር የዓመቱ መጀመሪያ ሲሆን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙት አሪዎች ደግሞ መስከረም ወይንም ታማ 10ኛ ወራቸው ነው። […]

እስራኤል ታጋች ለማስለቀቅ የወሰደችው እርምጃ ከሽፎ አንድ ታጋች መገደሉን ሐማስ ገለጸ

9 ታህሳስ 2023, 09:36 EAT የእስራኤል ወታደሮች አንድ ታጋችን ለማስለቀቅ ጋዛ ውስጥ ባካሄዱት ባልተሳካ ወታደራዊ ዘመቻ ታጋቹ መገደሉን የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ገለጸ። ወታደራዊ ቡድኑ ባሰራጨው ቪዲዮ ላይ ባልተሳካው የእስራኤል ታጋች የማስለቀቅ እርምጃ በደረሰ ጉዳት አንድ ታጋች መገደሉን አመልክቷል። በምሥሉ ላይ አንድ ታጋች በዚያ ስፍራ ለ40 ቀናት መያዙን ሲናገር የሚሰማ ሲሆን፣ ይህም ቪዲዮ የተቀረጸው በኅዳር ወር […]

ከቀጣሪ ድርጅቷ 28 ሚሊዮን ዶላር የሰረቀችው የሂሳብ ሠራተኛ የ50 ዓመት እስር ተፈረደባት

9 ታህሳስ 2023 ከቀጣሪ ድርጅቷ 28 ሚሊዮን ዶላር የሰረቀችው ደቡብ አፍሪካዊት የሂሳብ ሠራተኛ የ50 ዓመት እስር ተፈረደባት። ሂለዴጋርድ ስቲንካምፕ የተባለችው ይህች ሴት በድርጅቱ ውስጥ በሠራችባቸው 13 ዓመታት ውስጥ ብቻዋን 28 ሚሊዮን ዶላር የመስረቋ ዜና አገሬውን ጉድ አሰኘቷል። ሂለዴጋርድ ለዓመታት በስም ባልተጠቀሰ የአንድ ጤና ተቋም የሂሳብ ሠራተኛ ሆና ስትሰራ የቆየች ሲሆን፣ በእነዚህ ዓመታት ኃላፊነቷን እና ሙያዋን […]

የቻይና ነጭ ሽንኩርት ለአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ነው ሲሉ አንድ የምክር ቤት አባል አስጠነቀቁ

9 ታህሳስ 2023, 10:38 EAT አንድ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል አገራቸው ከቻይና የምታስገባው ነጭ ሽንኩርት በአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት በመሆኑ የሚያስከትለው ተጽእኖ እንዲመረመር ጥሪ አቀረቡ። የሪፐብሊካን ፓርቲው ተወካይ እንደራሴ ሪክ ስኮት ለአሜሪካ መንግሥት ንግድ መሥሪያ ቤት በጻፉት ደብዳቤ ላይ፣ ከቻይና የሚመጣው ነጭ ሽንኩርት ንጽህናው በተጠበቀ ሂደት ያልተመረተ መሆኑን በማመልከት ጉዳትን ያስከትላል ብለዋል። ቻይና በዓለም ላይ […]

በጋዛ ከሐማስ ሌላ ስንት የፍልስጤማውያን ታጣቂ ቡድኖች አሉ? እነማንስ ናቸው?

9 ታህሳስ 2023 በቅርቡ የሐማስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ሙሳ አቡ ማርዙክ በጋዛ ያሉ ሁሉም ታጋቾች በሐማስ ቁጥጥር ስር እንደማይገኙ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። አመራሩ በቃለ መጠይቁ አንዳንድ ታጋቾች በመስከረም 26ቱ ጥቃት ተሳታፊ በሆኑ “በተለያዩ አንጃዎች” ተይዘው እንደሚኙ ተናግረዋል። ቢቢሲ ቬሪፋይ በዚያ ጥቃት ከሐማስ ጎን ተሰልፈው ተሳታፊ የሆኑ አምስት ቡድኖችን ለይቶ ነበር። ምንም እንኳን እነዚህ ቡድኖች በእስራኤል […]

ቭላድሚር ፑቲን ለአምስተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ አስታወቁ

9 ታህሳስ 2023, 08:08 EAT የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአምስተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን በመጪው መጋቢት ወር በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ። ፑቲን ከሦስት ወር ገደማ በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ተፎካካሪ ሆነው እንደሚቀርቡ ይፋ ያደረጉት በዩክሬን ጦርነት ተሳታፊ ለሆኑ ወታደሮች ሽልማት በሰጡበት መድረክ ላይ ነው። የአገሪቱ ምርጫ አስፈጻሚ ኃላፊዎች ቀጣይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከመጋቢት 6 እስከ […]