“ለኑሮ ውድነት መባባስ ደላሎች አንድ ምክንያት ናቸው” ተባለ
December 27, 2024 – VOA Amharic በኢትዮጵያ ህገወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች ሸማቹን ማኅበረሰብ ለተባባሰው የኑሮ ውድነት ዳርገውታል ሲሉ የሸማች መብት ተቆርቋሪ ማኅበራትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይከሳሉ፡፡ ነጋዴዎች በበኩላቸው “መንግሥት ግብርን ጨምሮ ሕጋዊ ነጋዴው ላይ የሚያደርሰው ጫና በርትቷል” ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ዶክተር ዳኪቶ አለሙ … … ሙሉውን ለማየት […]
የትግራይ ወርቅ በኤርትራ ይወጣል መባሉ ፤ የትግራይ ተቃዋሚዎች እና ኤርትራ
December 27, 2024 – DW Amharic ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ ከትግራይ በኤርትራ በኩል በኮንትሮባንድ ይወጣል ተብሎ የሚቀርብ መረጃ የኤርትራ መንግስት አስተባበለ። የኤርትራ መንግስት ቃልአቀባይ የማነ ገብረመስቀል በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ውንጀላው ‘መሰረተቢስ’ ብለውታል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በሰሜን እና ወሎ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያስከተለው ችግር
December 27, 2024 – DW Amharic የትምህርት ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት የተዘጉባቸዉ አካባቢዎች ላይ ያሉ ህፃናት በቤተሰቦቻቸዉ አስገዳጂነት እድሜያቸዉ ሳይደርስ እየተዳሩ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ቤተልሄም ሰሎሞን ገልጸዋል። መምሪያዉ ከተቀበላቸዉ 100 ያለእድሜ ጋብቻ ሊፈፀም ነዉ ጥቆማ ዉስጥ ማስቆም የቻለዉ ስምንቱን ነዉ ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
የዶናልድ ትራምፕ የመስፋፋት ፍላጎት እና ግብረ መልሱ
December 27, 2024 – DW Amharic ፕሬዝዳንት ተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ ካናዳን፣ ግሪንላንድንና የፓናማ ካናልን ወደአሜሪካ ግዛትነት የመጠቅለልን ሃሳብና ዛቻን እያንሸራሸሩ ነው። ይሄው ሃሳባቸው ከየሃገራቱ ተቃውሞና ግራ መጋባትን አስተናግዷል። የፖለቲካ ተንታኞች ይሄንኑ ቃላቸውን እንደ ጸብ አጫሪነት አልያም እንደ መደራደርያ መሳርያነት እየተጠቀሙበት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
„ሄር ሂሴ“ ዩኔስኮ እውቅና የሰጠው የሂሳ ማህበረሰብ ያልተፃፈ ባህላዊ ሕግ
December 27, 2024 – DW Amharic የሶማሌ ህዝብ አካል የሆነው የሂሳ ማህበረሰብ መተዳደርያ ሕግ እውቅና እንዲያገኝ ከአምስት አመታት በላይ ያስቆጠሩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። ከአምስት አመት በፊት የተመሰረተው ሲቲ ሄሪቴጅ ሄር ሂሴን በአለም ዓቀፉ የትምህርት ፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችሉ ስራዎች ለመስራት የተቋቋመ ማህበር ነው።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ ተተኪን በተመለከተ ድምጽ ሊሰጥ ነው
ከ 3 ሰአት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮን (አትሚስ) የሚተካው ሌላኛው ተልዕኮ ላይ ድምጽ ለመስጠት ሊሰበሰብ ነው። በምክር ቤቱ ጊዜያዊ የአሰራር ደንብ መሰረት በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአትሚስ ተልዕኮ ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 31፣ 2024 ድረስ ተራዝሞ ነበር። በዩናይትድ ኪንግደም የተዘጋጀው […]
ሰሞኑን በዩኒቨርስቲዎች የተፈጠረው “ተቃውሞ” መነሻው ምንድን ነው?
ከ 1 ሰአት በፊት የዩኒቨርስቲዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ በተደረገ በቀናት ውስጥ የሦስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚቀርብላቸው ምግብ “ጥራት እና መጠን” ቀንሷል በማለት ተቃውሞ አነሱ። ከሁለት ሳምንት በፊት ትምሕርት ሚኒስቴር በምግብ ዋጋ ንረት ምክንያት “የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ በጀት” ላይ ማሻሻያ መደረጉን ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል። በዚህም 22 ብር የነበረው የአንድ ተማሪ ዕለታዊ የምግብ በጀት ወደ 100 […]
የደቡብ ኮሪያ የፓርላማ አባላት የአገሪቱ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት እንዲከሰሱ ጥያቄ አቀረቡ
ከ 5 ሰአት በፊት የደቡብ ኮሪያ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ተጠባባቂ መሪ ሃን ዳክ-ሱን እንዲከሰሱ ጥያቄ አቀረቡ። ፓርላማው ወታደራዊ ህግ በመደንገግ ከስልጣን የተነሱትን የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮልን ለመክሰስ ድምጽ ከሰጠ ሁለት ሳምንታት እንኳን ሳይሞላ ነው የአሁኑ ክስ የቀረበው። ጥያቄው የቀረበው ሃን በዋነኛው ተቃዋሚ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዲፒ) የተጠቆሙት የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት […]
ትራምፕ ለገበያ ያልቀረቡትን ግሪንላንድ እና ፓናማ ካናል ለምን መቆጣጠር ፈለጉ?
ከ 6 ሰአት በፊት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካን ከዩክሬን ጦርነትና ሌሎችም የውጭ አገራት ጉዳዮች በነጠሉ ንግግሮች ነበር ለምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበረው። በንግድ አጋሮች ላይ የክፍያ ገንዘብ ለመጨመርና የአገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ ቃል ሲገቡ ተደምጠዋል። ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ወጣ ያሉ ሐሳቦችን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ እየተናገሩ ነው። እንደ ቀልድ ካናዳ የአሜሪካ ግዛት ናት ከማለት ጀመሩ። […]
ሕንዳውያን ሕይወታቸው አደጋ ላይ እየጣሉ ወደ አሜሪካ የሚጎርፉት ለምን ይሆን?
ከ 6 ሰአት በፊት ባለፈው ጥቅምት ወር የአሜሪካው ኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ማስፈጸሚያ (አይሲኢ) የሕንድ ዜጎችን በቻርተርድ አውሮፕላን ወደ አገራቸው ልኳል።በተመሳሳይ መንገድ ሕንዳውያን ከአሜሪካ ተጠርንፈው የመላካቸው አዝማሚያ እየጨመረ ነው። በረራው ተራ የሚባል ዓይነት አልነበረም።በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ሕንዳውያንን ወደ አገራቸው ለማባረር ከተደረጉት በርካታ በረራዎች መካከል አንዱ ነው።በእያንዳንዱ በረራ ከ100 በላይ መንገደኞች ናቸው የሚሳፈሩት።እነዚህ አውሮፕላኖች “በአሜሪካ ውስጥ ለመቆየት […]