ሁቲዎች በቀይ ባሕር የምታልፍ መርከብን መትተው ሦስት መርከበኞችን መግደላቸው ተዘገበ

ከ 6 ሰአት በፊት የሁቲ አማጺያን በአንዲት የጭነት መርከብ ላይ ረቡዕ ዕለት በፈጸሙት የሚሳኤል ጥቃት ሦስት የመርከቧ ሠራተኞች መገደላቸውን እና ሌሎች መቁሰላቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ። የየመን ታጣቂ ቡድኖች በቀይ ባሕር በኩል በሚያልፉ የጭነት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመሩ ወዲህ በመርከበኞች ላይ የሞት አደጋ ሲያጋጥም ይህ የመጀመሪያው ነው። ጥቃት የተፈጸመባት የባርቤዶስ ሰንደቅ ዓላማን የምታውለበልበው ‘ትሩ ኮንፊደንስ’ […]

ማይክ ሐመር በፕሪቶሪያው ስምምነት፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ግጭቶች ላይ ሊወያዩ ነው

ከ 6 ሰአት በፊት የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል በተደረሰው ስምምነት አፈጻፈም ግምገማ ላይ በመሳተፍ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ስላሉ ግጭቶች ሊወያዩ ነው። በትግራይ ሲካሄድ የነበረውን ጦርነት ለማስቆም በተደረገው ጥረት ውስጥ ጉልህ ሚና እንደነበራቸው የሚነገርላቸው አምባሳደር ሐመር፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሂደትን በተመለከተ በሚካሄደው ግምገማ ላይ መሳተፍ ዋነኛ […]

እስራኤል በኃይል በያዘችው መሬት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የሰፈራ ቤቶችን ግንባታ እቅድ አጸደቀች

ከ 5 ሰአት በፊት እስራኤል በኃይል በያዘችው ዌስት ባንክ ከ3 ሺህ 400 በላይ አዳዲስ የሰፈራ ቤቶችን ለመገንባት የወጣውን እቅድ አጸቀደች። ከነዚህ ቤቶች ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት የሚገነቡት በምስራቅ ኢየሩሳሌም በምትገኘው ማሌ አዱሚም ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ከቤተልሔም በስተደቡብ በሚገኙት ኬዳር እና ኤፍራት አቅራቢያ ነው ተብሏል። ግንባታው ከሁለት ሳምንታት በፊት በማሌ አዱሚም አቅራቢያ ለደረሰው የፍልስጤም ጥቃት ምላሽ […]

አፕል እና ማይክሮሶፍት በኮንጎ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ አድርሰዋል የሚለውን ክስ የአሜሪካ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ

ከ 5 ሰአት በፊት የአሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በማዕድን ማውጣት ሥራ የተሰማሩ አምስት ኩባንያዎች በህጻናት ላይ የጉልበት ብዝበዛ ያደርሳሉ በሚል የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ክስ የቀረበባቸው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አፕል፣ ማይክሮሶፍት፣ ቴስላ፣ ዴል ቴክኖሎጂ እና የጉግል ቤተሰብ ኩባንያ የሆነው አልፋቤት ናቸው። ክሱ የቀረበው በዋናነት እነዚህ ኩባንያዎች የኮባልት ምርት ስለሚገዙ በህጻናት የጉልበት ብዝበዛው ላይ […]

በዚህ ዓመት የአፍሪካ ሀብታም እና ድሃ አገራት የትኞቹ ናቸው?

5 መጋቢት 2024 አፍሪካ በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ቢሆንም ባሉባት ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮች እንዲሁም የደኅንነት እጦት፣ ሙስና፣ የእርስ በርስ ጦርነቶች እና በሽብር እንቅስቃሴዎች ምክንያት በድህነት ውስጥ ትገኛለች። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ባለንበት የአውሮፓውያን ዓመት በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ሀብታም እና ድሃ አገራትን ዝርዝር አውጥቷል። በዚህም የአገራቱን ሀብት ወይም ድህነት ለመመዘን የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት፣ […]

‘ባርቢኪው’ – ሄይቲን እያሸበረ ያለው የቀድሞው የፖሊስ መኮንን፤ የአሁኑ የወሮበሎች ቡድን መሪ

ከ 6 ሰአት በፊት በአገሪቱ የሚገኙ ዋነኛ እስር ቤቶች በወሮበላ ቡድኖች ተወሮ በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ካመለጡ በኋላ የሄይቲ መንግሥት በመላ አገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። የካሬቢያን ደሴቶች አካል የሆነችው አገር በአመፅ እየታመሰች ነው። የወሮበላ ቡድኖች የዋና ከተማዋ ፖርት-አው-ፕሪንስን 80 በመቶ ክፍል ተቆጣጥረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪዬል ሄንሪ መንግሥት ሥልጣን ይልቀቅ እያሉ ነው። ያ ካልሆነ በአገሪቱ የእርስ […]

ፈተና ላይ የነበረ ተማሪ በጥይት የመታው ባንግላዴሻዊ አስተማሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

ከ 5 ሰአት በፊት ባንግላዴሽ የሚገኝ አንድ የሕክምና ኮሌጅ አስተማሪ የሆነው ግለሰብ ተማሪ በጥይት መምታቱን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ዋለ። አስተማሪው ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ቢውልም ከሥራ የታገደው ግን ከሁለት ቀናት በኋላ ነው። ራይሀን ሼሪፍ ከሥራው የታገደው ተማሪዎች ረቡዕ ዕለት ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ ነው። በጥይት የተመታው ተማሪ ቀዶ ጥገና የተደረገለት ሲሆን አሁንም ሆስፒታል እንደሚገኝ ተሰምቷል። ቢቢሲ ዶክተር […]

በአማራ ክልል ያገረሸው ውጊያ

የባህር ዳር ከተማ ገጽታ ፖለቲካ በዮናስ አማረ March 6, 2024 ‹‹ግማሾቹ ወንድሞቼ ፋኖ፣ ግማሾቹ ደግሞ የአገር መከላከያ ወታደሮች ናቸው፤›› ስትል ሐዘን በተቀላቀለበት ድምፅ ትናገራለች፡፡ ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገችው የባህር ዳሯ ነዋሪ፣ ‹‹እንዲህ ካለው ሕይወት ሞቶ መገላገል ይሻላል፤›› ስትል ነው ሳግ በተቀላቀለበት ድምፅ እያሳለፈች ያለውን ሕይወት ለሪፖርተር የተናገረችው፡፡ ከሰሞኑ በባህር ዳር አካባቢ ስለተፈጠረው ሁኔታ እንድታስረዳ የተጠየቀችው የባህር […]

ሩሲያን ከጀርመን ያወዛገበው የጦር ምስጢር

የጀርመን መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ (ከመሀል) ለዩክሬን ረዥም ርቀት ተተኳሽ ሚሳኤል አልሰጥም ማለታቸው አስተችቷቸዋል (አሶሺየት ፕሬስ) ዓለም ሩሲያን ከጀርመን ያወዛገበው የጦር ምስጢር ምሕረት ሞገስ ቀን: March 6, 2024 ከዓመት በፊት በሩሲያና በዩክሬን መካከል የተጀመረውን ጦርነት በፖለቲካዊ ውይይት ለመፍታት ጥረት ቢደረግም፣ ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ለዩክሬን የወገኑት አሜሪካና አውሮፓውያኑ የውክልና ጦርነታቸውን ከሚያካሂዱበት ዩክሬን ምድር ከ31 ሺሕ በላይ ዩክሬናውያን፣ […]

በጣት መፈረም ሲያበቃ የአገር ዕድገት ይፋጠናል

ልናገር በጣት መፈረም ሲያበቃ የአገር ዕድገት ይፋጠናል አንባቢ ቀን: March 6, 2024 በዳዊት አባተ (ዶ/ር) የትምህርት ዕድል ማግኘት በዓለም አቀፍ የተደነገገ የዜጎች ሰብዓዊ መብት ነው፡፡ ይሁን እንጅ ስለአገራችን የትምህርት ሥርዓት በአብዛኛው የሚነገረውና የምንሰማው ስለመደበኛ ትምህርት ነው፡፡ ከዚህም በጠበበ መልኩ ለከፍተኛ ትምህርትና ለድህረ ምረቃ ፕሮግራም ትኩረት የሚሰጥ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ስለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ዝቅተኛ […]