የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዛሬ አንጎላን ይጎበኛሉ
December 2, 2024 – VOA Amharic ባይደን የደቡብ ምዕራባዊ አፍሪካዋን ሀገር በመጎብኘት የመጀመሪያ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ናቸው። ጉብኝታቸው በዋናነት ከአፍሪካ አህጉር የሚወጡ ውድ ማዕድኖች እየተስፋፋ ወደሚገኘው የአንጎላ ወደብ የሚያጓጉዘው የባቡር መሥመር ላይ ያተኮረ እንደሚሆንም ተመልክቷል። በተጨማሪም የአህጉሪቱ ዕድገት አውታሮች ይጠናከሩ ዘንድ ዲሞክራሲ እና መረጋጋት እንደሚያስፈልግ ያሰምሩበታል፡፡ የቪኦኤዋ የኋይት ሐውስ … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ መጋዘን ውስጥ 350 ሺህ የአፍሪካ ቅርሶች ተገኙ
ከ 35 ደቂቃዎች በፊት በካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ መጋዘን ውስጥ 350,000 መሆናቸው የተገመተ የአፍሪካ ቅርሶች፣ የእጅ ጽሑፎች፣ የሰው ቅሪተ አካሎች፣ ፎቶግራፎች እና የተፈጥሮ ታሪክ ናሙናዎች ተገኙ። ዩኒቨርሲቲው ካከማቻቸው ስብስቦች ውስጥ ግብፅ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አርኪዎሎጂያዊ ቅርሶች እና የእጅ ጽሑፎች ያላት አፍሪካዊ አገር ነች ተብሏል። ዶ/ር ኢቫ ናሙሶኬ ከካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ቅርሳ ቅርሶቹን ለመለየት ከዩኒቨርስቲው የቤተ-መጻሕፍት ሠራተኞች፣ አስተዳዳሪዎች፣ ቤተ-መዛግብት […]
በትግራይ ማኅሌት ተኽላይን አግቶ በመግደል ከተከሰሱት አንደኛው ሞት ተፈረደበት
ከ 3 ሰአት በፊት የመቀለ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ ያለው ተከሳሽ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ። በ16 ዓመቷ ማኅሌት ተኽላይ ላይ የግድያ ወንጀል በመፈፀም ተከሰው በእስር ላይ ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል የሞት ፍርድ የተፈረደበት አወት ነጋሲ የተባለው ተከሳሽ እንደሆነ ተገልጿል። ሁለተኛው ተከሳሽ ናሆም ፍፁም ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል። የ16 ዓመቷ ማኅሌት […]
በአዲስ አበባ ከታህሳስ ጀምሮ የባንክ አካውንት ለመክፈት የ’ፋይዳ’ መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ ሊሆን ነው
2 ታህሳስ 2024 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከቀጣዩ ወር ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ደንበኞች የባንክ አካውንት ለመክፈት “ፋይዳ” የተሰኘውን የዲጂታል መታወቂያ በግዴታነት እንዲያቀርቡ አዘዘ። ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ደንበኞች የትኛውንም የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ መገደድ እንደሚጀምሩ ባንኩ አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ፤ የ“ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በአስገዳጅነት ጥቅም […]
ግብፃዊው የኢፕስዊች አምበል “በሃይማኖቱ ምክንያት” የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ባንዲራ አላደርግም አለ
ከ 6 ሰአት በፊት በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የሚጫወተው ኢፕስዊች ታውን አምበል የሆነው ሳም ሞርሲ “በሃይማኖቱ ምክንያት” የቀስተ ደመና ኅብረ ቀለማት ያሉትን የአምበሎች መለያ አላደርግም ማለቱ ተሰማ። ኢፕስዊች ባለፈው ቅዳሜ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር በነበረው ጨዋታ የቀስተ ደመና ቀለማት ያሉትን የአምበሎች መለያ ሳያጠልቅ ነው ሜዳ የገባው። የፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ለመተሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን [ኤልጂቢቲኪው+] ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት አምበሎቻቸው […]
ከኒው ዮርክ ወደ ፓሪስ ሳትከፍል ተደብቃ የበረረችው ግለሰብ ማንነቷ ታወቀ
ከ 7 ሰአት በፊት ከኒው ዮርክ ወደ ፓሪስ ሳትከፍል ተደብቃ የተጓዘችው ግለሰብ ማንነቷ ታወቀ። ግለሰቧ የ57 ዓመቷ ስቬታላና ዳሊ ትባላለች። አሁን የምትገኘው ፈረንሳይ ሲሆን፣ ወደ አሜሪካ ላለመመለስ ውዝግብ መፍጠሯ ተዘግቧል። ትኬት ሳትቆርጥ በዴልታ አየር መንገድ በኩል ከኒው ዮርክ ጄኤፍኬ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ፓሪስ ቻርልስ ደ ጉል አውሮፕላን ማረፊያ የተጓዘችው ግለሰብ ሩስያዊት መሆኗ ተገልጿል። ቪዛ ስለሌላት […]
የጃጉዋር አዲሱ የኤሌክትሪክ መኪና መነጋገሪያ ሆነ
ከ 7 ሰአት በፊት ውድ የቤት መኪናዎች በማምረት የሚታወቀው ጃጉዋር አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ዲዛይን ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ ከቀናት በፊት ይህን መኪና ለማስተዋወቅ በሚል የለቀቀው ማስታወቂያ በብዙዎች ዘንድ አከራካሪ ሆኖ ነበር። ታይፕ 00 የተባለው የኤሌክትሪክ መኪና ይፋ ሲደረግ ማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች በሁለት ጎራ ተከፋፍለው ሐሳባቸውን ሲሰጡ ታይተዋል። ግማሹ የአዲሱን መኪና ዲዛይን ወዶታል፤ የተቀረው ደግሞ እምብዛም አይደለም […]
የሙሴቬኒ ቀንደኛ ተቃዋሚ እንዴት ከኬንያ ተሰውሮ በኡጋንዳ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ተገኘ?
ከ 8 ሰአት በፊት የሙሴቬኒ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆነው ኪዛ ቤሲግዬ ከኬንያ ድንገት ጠፍቶ በኡጋንዳ ወታደራዊ ፍርድ ቤት መታየቱ ብዙዎችን ያስደነገጠ ክስተት ሆኗል። ሁለቱ ሀገራት ምስጢራዊ የሆነ መረጃ እየተለዋወጡ ነው የሚለው ጉዳይ በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ዘንድ ፍርሀት የፈጠረ ይመስላል። የቤሲግዬ ባለቤትና አጋሮች የተቃዋሚ ፓርቲ መሪውን እንዴት አፍነው የወሰዱት ሰዎች ኬንያዊያን በመምሰል አታለው እንደወሰዱት ይፋ አድርገዋል። ዘገባዎች እንደሚያሳዩት […]
ከሞት ለማምለጥ 9 ቢሊዮን ዶላር ስታሰባስብ የነበረችው ቪዬትናሚዊት ባለሃብት ይግባኝ ውድቅ ሆነ
ከ 6 ሰአት በፊት የ68 ዓመቷ ቪዬትናሚዊቷ ባለሃብት ትሩንግ ማይ ላን ባለፈው ሚያዝያ በዓለም ላይ ትልቁ የባንክ ማጭበርበርን በማቀናበር ጥፋተኛ ተብላ የሞት ፍርድ ፍርድ ተፈርዶባታል። ቱጃሯ ይህን ፍርድ ለመቀልበስ ይግባኝ ጠይቃ እየተጠባበቀች ዕዳዋን ለመክፈል 9 ቢሊዮን ዶላር እያሰባሰበች ነበር። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ማክሰኞ በዋለው ችሎት የባለሀብቷን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ የሞት ቅጣቷ ተፈፃሚ እንዲሆን ወስኗል። […]
አራት ጊዜ ከእስራኤል የአየር ጥቃት ብታመልጥም ልጆቿን ያጣችው እናት
ከ 8 ሰአት በፊት ሪሀብ ፋውር አራት ጊዜ ከቤቷ ተፈናቅላለች። ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈናቀለችው ከዓመት በፊት ነበር። የእስራኤልን የአየር ጥቃት በተደጋጋሚ ብትሸሽም ማምለጥ ቀላል አልሆነም። ሊባኖስ ውስጥ የትኛውም ቦታ ደኅንነቱ የተጠበቀ አይደለም። እስራኤል ጥቃት ያደረሰችው የ33 ዓመቷ ሪሀብ እና ባለቤቷ በሚኖሩበት መንደር ነው። ባለቤቷ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ በውሃ አገልግሎት ዘርፍ ይሠራ ነበር። የአየር ድብደባ ሲፈጸም የስምንት […]