ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ገበያ የምትሸጠው የቡና ምርት አውሮፓ ኅብረት ያወጣውን አዲስ የደን ጭፍጨፋ ደንብ

February 4, 2024 – Konjit Sitotaw  የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን፣ አገሪቱ ለአውሮፓ ገበያ የምትሸጠው የቡና ምርት አውሮፓ ኅብረት ያወጣውን አዲስ የደን ጭፍጨፋ ደንብ ያከበረ መኾኑን ለማረጋገጥ ኮሚቴ ማቋቋሙን ሪፖርተር ዘግቧል። ኮሚቴው፣ ከባለሥልጣኑ፣ ከቡና አምራችና ላኪ ማኅበራት፣ ከቡና አምራች ገበሬዎች፣ ከኢምባሲዎችና መንግሥታዊ ካልኾኑ ድርጅቶች የተውጣጡ አባላትን እንዳካተተ ዘገባው ጠቅሷል። አውሮፓ ኅብረት፣ አባል አገራቱ ከውጭ የሚገዙት ቡና ደኖችን […]

በአማራ ክልል የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አንድምታው

February 4, 2024 – DW Amharic  አማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ የተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ ም ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ አፅድቋል፡፡ ምክር ቤቱ የጊዜውን መጠናቀቅ ተከትሎ ትናትን ባደረገው ልዩ ስብሰባ አዋጁ ለሌላ 4 ወራት እንዲራዘም ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ለእንስሳት የርህራሄ እና የእንክብካቤ ባህል እንዲዳብር የምትሰራው ወጣት

February 4, 2024 – VOA Amharic  ፌቨን መለሰ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም ትኩረት ያልተሰጠውን የእንስሳት እንክብካቤ ባህል እንዲዳብር ጥረት እያደረጉ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል አንዷ ናት።የጎዳና ውሾች ምገባን ጨምሮ ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን እና ርህራሄ የተነፈጋቸው እንስሳቶችን ለመርዳት በምታደረጋቸው ለየት ያሉ እንቅስቃሴዎች የብዙዎቹን ቀልብ የሳበቸውን ወጣት ሀብታሙ ስዩም አነጋግሮቷል። ፋይሉ ከስር ተያይዟል። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ […]

የአፍሪካ ዋንጫ፡ ደቡብ አፍሪካ በበረኛዋ ታግዛ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ስታልፍ አይቮሪ ኮስት ግስጋሴዋን ቀጥላለች

ከ 9 ሰአት በፊት በአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ያለምንም ጎል በተጠናቀቀው የኬፕ ቨርዴ እና ደቡብ አፍሪካ ግጥሚያ የባፋና ባፋናዎቹ ግብ ጠባቂ ሮንዊን ዊሊያምስ አራት መለያ ምቶችን በማዳን ቡድኑን ለግማሽ ፍጻሜ አብቅቷል። በጨዋታው ድንቅ ኳስ ማዳን ችሎ የነበረው አምበሉ ዊሊያምስ በመለያ ምቱ ደግሞ የቤቤን፣ የዊሊ ሴሜዶን፣ ላሮስ ዱአርቴን እና ፓትሪከክ አንድራዴን ኳሶች አድኗል። የኬፕ ቨርዴው […]

ሶማሊያዊያን ‘ፓይሬቶች’ እንደ አዲስ የሀገሪቱን የባሕር ጠረፍ ማሸበር ጀምረዋል?

ከ 7 ሰአት በፊት የሶማሊያ የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች እንደ አዲስ መርከቦችን ዒላማ ማድረግ ጀምረዋል። ይህ ክስተት ከአስርት ዓመታት በፊት የነበረውን ትዝታ አየመለሰ ነው። በወቅቱ የታጠቁ የሶማሊያ ፓይሬቶች የባሕር ጠረፉን ተቆጣጥረው መርከቦችን በማገት ሚሊዮን ዶላሮች ክፍያ ይጠይቁ ነበር። ይህ ዓለምን አስጨንቆ የነበረ ዝርፊያ ሀገራት ተደራጅተው የሥፍራውን ደኅንነት ለመጠበቅ ባደረጉት ሙከራ ቀዝቅዞ ነበር። ነገር ግን ከሰሞኑ ታጣቂዎች […]

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምን ውጤት አመጣ? ወደፊትስ በምን ሊቋጭ ይችላል?

3 የካቲት 2024 ካለፈው ዓመት አጋማሽ ወዲህ በአማራ ክልል የነበረው መረጋጋት እየተበላሸ ከሚያዝያ ወር በኋላ በነበረው ጊዜ ብሶበት ወደ ለየለት ግጭት ተገብቶ ክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ከገባ ስድስት ወራት ሆኖታል። ጥቂት በማይባሉ ስፍራዎች የግብርና ሥራ ተስተጓጉሏል፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በመደናቀፉ የሚፈለገው ምርት እና አገልግሎት በቀላሉ አይገኝም። መሠረታዊዎቹ የመድኃኒት እና የሸቀጦች ዋጋ አልቀመስ ብሏል። የመንግሥት አገልግሎት […]

ከስደተኛነት ተነስቶ በተለያዩ አገራት የግንባታ ኩባንያ ያቋቋመው ኤርትራዊ

4 የካቲት 2024, 08:04 EAT ኤርትራ በጦርነት በምትታመስባቸው ዓመታት እናቱ ሕይታቸውን ለመታደግ ወደ ጎረቤት አገር ይዘውት ተሰደዱ። ኤርትራ ነጻ አገር እስክትሆን ድረስ የፊደል ዘር የቆጠረው በሰው አገር፣ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ነው። ወደ ኤርትራ ከተመለሱ በኋላም ቢሆን፣ ሕይወት ከስደት የሚያስቀረው አልሆነም። ዛሬ የራሱን ድርጅት መሥርቶ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን ቀጥሮ ያሠራል። የምህንድስና ባለሙያ የሆነው በረከት ጎይቶም […]

የናሚቢያው ፕሬዝደንት በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ

4 የካቲት 2024, 08:31 EAT በሀገራቸው መዲና ዊንድሆክ ካለ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ የቆዩት የናሚቢያው ፕሬዝደንት ሃጌ ግይንጎብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ምክትል ፕሬዝደንት ናንጎሎ ምቡምባ እንዳስታወቁት ሃጌ የሞቱት ቅዳሜ ለሊት ለእሑድ አጥቢያ ነው። “ሕይወታቸው ስታልፍ ባለቤታቸው ማዳም ሞኒካ ጌይንጎስ እና ልጆቻቸው ነበሩ” ሲሉ ምክትል ፕሬዝደንቱ ገልጠዋል። የ82 ዓመቱ ፕሬዝደንት የካንሰር ተጠቂ መሆናቸውን ይፋ ካደረጉ ቆይተዋል። […]

የቀድሞው የፓኪስታን መሪ ኢምራ ካን ትዳራቸው እስላማዊ አልነበረም ተብለው 7 ዓመት ተፈረደባቸው

4 የካቲት 2024, 09:18 EAT የፓኪስታን ፍድር ቤት የቀድሞው መሪ ኢምራን ካን እና ባለቤታቸው ትዳራቸው ሕጋዊ አልነበረም ሲል የሰባት ዓመት እሥር ፈርዶባቸዋል። ችሎቱ እንዳለው በአውሮፓውያኑ 2018 ካን ከቡሽራ ቢቢ ጋር የመሠረቱት ጋብቻ እስላማዊ እና ሕጋዊ ያልሆነ ነው። ኢምራን ካን ባለፈው ሳምንት ነው ከባለቤታቸው ጋር በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ናቸው ተብለው እሥር የተፈረደባቸው። ነገር ግን የ71 ዓመቱ […]

በጋዛ ያለው ጦርነት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ሊስፋፋ ይችላል?

4 የካቲት 2024, 08:05 EAT በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 7 ሐማስ፤ እስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ነው የመካከለኛው ምስራቅ ሰላም መናጋት የጀመረው። በሐማስ ጥቃት 1300 ሰዎች ተገድለዋል። ለዚህ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ወታደራዊ ዘመቻ የጀመረችው እስራኤል ጋዛን እንዳይሆን አድርጋታለች። በጋዛ በደረሰው ጥቃት ደግሞ እስካሁን ከ26 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያስ ተገድለዋል። በዚህ ምክንያት ሁሌም ግጭት የማያጣው ቀጣና ወደላቀ ውጥረት አምርቷል። […]