የሰው ዐይነ ምድርን በመጠቀም ለከባድ ህመሞች ስለሚሰጠው ሕክምና ምን ያህል ያውቃሉ?

ከ 7 ሰአት በፊት ሪክ ዳላዌይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰ ዐይነ ምድር ላይ የሚደረገውን ክሊኒካዊ ሙከራ እንዲቀላቀሉ በተጋበዙበት ወቅት “ዐይነ ምድርን ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው የማስገባት አጠቃላይ ሐሳብ በእርግጥ እንግዳ ነገር ነው” የሚል ስሜት ነበር የተሰማቸው። የ50 ዓመቱ አዛውንት በዩናይትደ ኪንግደም (ዩኬ) በርሚንግሃም ዩኒቨርስቲ በሚካሄደው ሳምንታዊ የዐይነ ምድር የማዘዋወር የሁለት ወራት መርሃ ግብራቸውን ጨርሰዋል። ስክሌሮሲንግ […]

ሥራ ለመቀጠር ‘የባሎቻችሁን የጽሁፍ ፍቃድ አምጡ’ የሚባሉት ኢራናውያን ሴቶች

ከ 7 ሰአት በፊት “ለሥራ ቃለ መጠይቅ እያደረግኩ በነበረበት ወቅት ባለቤቴ መሥራቴን እንደሚፈቅድ የሚገልጽ የጽሁፍ ማስረጃ እንዳቀርብ ተጠይቅኩ” ይህንን ያለችው በነዳጅ እና በጋዝ ኢንጂነሪንግ የማስተርስ ዲግሪ ያላት ኢራናዊቷ ኔዳ ናት። በትምህርቷ የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰችው ኔዳ ሥራ ለመቀጠር ባለቤቷ መፍቀዱን የሚያሳይ የጹሁፍ ማስረጃ አምጪ ስትባል መዋረድ ተሰማኝ ትላለች። “ትልቅ ሰው ነኝ። የራሴን ውሳኔ መወሰን የምችል […]

የቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም (ፎካክ) ለአፍሪካ መዘመን ያለው ሚና

እኔ የምለዉ የቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም (ፎካክ) ለአፍሪካ መዘመን ያለው ሚና አንባቢ ቀን: September 15, 2024 በመላኩ ሙሉዓለም ዘመናዊነት (Modernization) የአንድ ማኅበረሰብ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሒደት ነው። ለአንድ አገር ልማትና ዘመናዊነት ለማምጣት የተለያዩ ሞዴሎች አሉ፡፡ ዘመናዊነት እንዲስፋፋ በአገሮች መካከል ትብብር፣ አጋርነትና የልምድ ልውውጥ አስፈላጊ ናቸው። የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 […]

ለብሔራዊ ፍላጎትና ጥቅም ሲባል ማዕቀቡ ይቀጥላል!!

እኔ የምለዉ ለብሔራዊ ፍላጎትና ጥቅም ሲባል ማዕቀቡ ይቀጥላል!! አንባቢ ቀን: September 15, 2024 በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የተባበሩት አሜሪካ ግዛቶች (በእንግሊዘኛ ምህፃረ ቃል ዩኤስኤ) ከዚህ በኋላ አሜሪካ እያልኩ የምገልጻት አገር ፕሬዚዳንት ቀደም ሲል የአሜሪካ መንግሥት ጥሎት የነበረን፣ በቅርቡም የተጣለበት የጊዜ ገደብ ያበቃ የነበረን፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን፣ የባለሥልጣናት ጉዞን፣ ወዘተ የሚያካትት ማዕቀብ በኢትዮጵያ ላይ ሊያስቀጥሉ መፈረማቸውን የብዙኃን መገናኛ […]

ሽኖዬ እና ጎቤ

ዝንቅ ሽኖዬ እና ጎቤ በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: September 15, 2024 ልጃገረዶች ሽኖዬ ወይም አባቢሌ እያሉ ከቤት ቤትም እየተዘዋወሩ የአዲሱን ዓመት መልካም ምኞታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ወጣቶች ይህን ባህላዊ ጨዋታ የሚጫወቱት በየቤቱና በጎዳና በቡድን በመሆን  ነው።  ከዚህ ባለፈም ወጣቶች ይተጫጩበታል።  በመስከረም ሦስተኛ ሳምንት ላይ ለሚከበረው ኢሬቻ መዳረሻም ይሆናል። በወጣቶች የሚከወነው  የሽኖዬና ጎቤ ጨዋታ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዋና ዋና […]

ለሕዝብና ለአገር ፋይዳ የሌላቸው ድርጊቶች ልጓም ይበጅላቸው!

September 15, 2024 ርዕሰ አንቀጽ በአሁኑ ጊዜ ለሕዝብና ለአገር ፋይዳ ከሌላቸው ድርጊቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱት ዓይን ያወጣ ሌብነትና ሙስና፣ ጽንፈኛ ብሔርተኝነት፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን አለማክበር፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ መጣስ፣ ለሕግ የበላይነት ፀር መሆን፣ ጥቅም የሌላቸው አሰልቺ ነገሮች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ማድረግና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ በአንድ በኩል ለአገር ልማት ይበጃሉ የሚባሉ በርካታ ዕቅዶች ተነድፈው ወደ ሥራ ይገባል፡፡ […]

ምን ያለው ነው! ሳልሞት ይፈታኛል!

ዝንቅ ምን ያለው ነው! ሳልሞት ይፈታኛል! አንባቢ ቀን: September 15, 2024 ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ባል ሳይወጣላቸው ነው የሞቱት ይባላል፡፡ በመጀመሪያ ገና በጨቅላነታቸው በዕድሜ አቻቸው ያልሆኑ ራስ አርአያ ዮሐንስን (የአፄ ዮሐንስ ልጅ) እንዲያገቡ ተደረገ፣ ራስ አርአያ ከሞቱ በኋላ ደግሞ የሰሜኑን ኢትዮጵያ ፖለቲካ ለመጠበቅ ሲባል ለራስ ጉግሣ ተዳሩ፡፡ ራስ ጉግሣ ብዙውን የሌሊት ጊዜያቸውን በጸሎት ያሳልፉት ነበር፤ ንግሥት […]

በሥነ ምድር የዘመን አቆጣጠር ስልትና ቅርሰ ሕይወት (fossils) ዕድሜ

አስተያየት September 15, 2024 በሽብሩ ተድላ (ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ) እና ገዛኸኝ ይርጉ (ፕሮፌሰር) መግቢያ ሳይንሳዊ አስተሳሰብን፣ ብሎም የሳይንስን ዕውቀት በማኸዘብ (ብዙ ሰው በቀላል መንገድ እንዲገነዘብ ማድረግ)፣ በምክንያት ላይ የተመሠረቱ፣ ብዙ ጠቃሚ ተግባራትን የሚያከናውን ኅብረተሰብን ለመመሥረት ይረዳል፡፡ ለሰው ልጅ ጥቅምን የሚያበረክቱ የቁስ አካል ይዘትና ሁኔታ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መተንተንና ለንባብ ማቅረብ፣ የሳይንሳዊ አስተሳሰባችንን እና ሳይንሳዊ  እውቀታችንን ለማዳበር […]

‹‹በጦርነቱ በሚሳተፉት በሁለቱ ኃይሎች መካከል ያለው ሥር የሰደደ አለመተማመን ፈተና ሆኖብናል›› የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል

ዜና ‹‹በጦርነቱ በሚሳተፉት በሁለቱ ኃይሎች መካከል ያለው ሥር የሰደደ አለመተማመን ፈተና ሆኖብናል›› የአማራ… ሔለን ተስፋዬ ቀን: September 15, 2024 በአማራ ክልል በሚፋለሙት የፌዴራል መንግሥትና የፋኖ ኃይሎች መካከል ያለው ሥር የሰደደ አለመተማመን ሰላም ለማውረድ የሚያደረገው ጥረት ፈተና እንደሆነበት፣ የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል አስታወቀ፡፡ የካውንስሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል […]

 የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የባንክ ሒሳብና የጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ ዕግድ ተነሳ

https://www.ethiopianreporter.com/133393/ዜና  የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የባንክ ሒሳብና የጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ ዕግድ ተነሳ ታምሩ ጽጌ ቀን: September 15, 2024 የ2016 ዓ.ም. መጨረሻ ሳምንት ዿጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በከሳሾች እነ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ (አራት ሰዎች) ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍትሐብሔር ተረኛ ችሎት ክስ ቀርቦ፣ በተከሳሾች እነ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አምስት ሰዎች) ላይ ተጥሎ የነበረው […]