የቁም እንስሳት አቅራቢዎች በደረሰኝ እንዲሸጡ ትዕዛዝ በመተላለፉ ላኪዎች ሥጋት ተፈጥሮብናል አሉ
በተመስገን ተጋፋው February 16, 2025 የቁም እንስሳት አቅራቢ ነጋዴዎች በደረሰኝ እንዲሸጡ መንግሥት ትዕዛዝ በማስተላለፉ ምክንያት፣ ሥጋ ላኪዎች የአቅርቦት ችግር እንደገጠማቸውና ከገበያ ውድድር ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሥጋት እንዳላቸው ተናገሩ፡፡ የአቢሲኒያ ቄራ ድርጅት ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ መንግሥት የቁም እንስሳት የሚያቀርቡ ነጋዴዎችን በአንድ ጊዜ በደረሰኝ እንድትሸጡ በማለቱ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል ሲሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ […]
ፈተና የበዛበት አመጋገብ እንዴት ይፈታ?
አበበ ፍቅር February 12, 2025 ምን እየሰሩ ነው? https://www.ethiopianreporter.com/138297 አቶ አብነት ተክሌ የሥነ ምግብ ባለሙያ ሲሆን የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪውን ምግብና ምግብ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ነው ያጠናው፡፡ በመጀመሪያ ዲግሪው በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ‹‹ፉድ ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ›› በሚል ለአራት ዓመታት ያጠና ሲሆን ማስተርሱን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ‹‹ፉድ ሳይንስ ኤንድ ኒውትሬሽን በሚል ተመርቋል፡፡ ተመርቆ […]
የትራምፕ ጋዛን የመሰልቀጥ ውጥንና የተቃውሞ ድምፆች
ወደ ፍርስራሽነት የተቀየሩ የጋዛ አካባቢዎች ዓለም የትራምፕ ጋዛን የመሰልቀጥ ውጥንና የተቃውሞ ድምፆች በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: February 12, 2025 የጋዛ ሰርጥ በሜዲትራኒያን ባህር 41 ኪሎ ሜትር የሚሆነውን ይጋራል፡፡ በሰርጡ አገረ መንግሥት እንዳይኖራቸው ተደርገው 2.3 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ይኖራሉ፡፡ ጋዛን በደቡብ ምዕራብ ግብፅ፣ በምሥራቅና ሰሜን ደግሞ እስራኤል ያዋስኗታል፡፡ የራሴ ብላ የምታስተዳድረው የባህርም ሆነ የአየር ክልል እንዳይኖራትም ተከልክላለች፡፡ እስራኤል […]
የጤናው ዘርፍ ባለፉት ስድሥት ወራት
ማኅበራዊ የጤናው ዘርፍ ባለፉት ስድሥት ወራት አበበ ፍቅር ቀን: February 16, 2025 የወባ በሽታ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ የጤናና የማኅበራዊ ቀውስ መንስዔ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2024 ያወጣው መረጃም 263 ሚሊዮን ሰዎች የወባ በሽታ ተጠቂ እንደነበሩ ያሳያል፡፡ ከተመዘገበው ውስጥ 94 በመቶ የሚሆኑት የወባ ተጠቂዎች ከአፍሪካ ሲሆኑ፣ 95 በመቶ (597,000) የሚሆነው ሞት የተመዘገበውም […]
የባሕር ዳርና ድሬዳዋ ኤርፖርቶች የሲቪል በረራዎች ቁጥጥር ስርዓታቸውን አሳደጉ
ማኅበራዊ የባሕር ዳርና ድሬዳዋ ኤርፖርቶች የሲቪል በረራዎች ቁጥጥር ስርዓታቸውን አሳደጉ ናርዶስ ዮሴፍ ቀን: February 16, 2025 በኢትዮጵያ ከሚገኙት አራት ዓለም አቀፍ ኤርፖርቶች መካከል የሆኑት የባህር ዳርና የድሬዳዋ ኤርፖርቶች፣ የአየር በረራዎች ቁጥጥር ክፍሎች ከጥር ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ማናቸውንም እስከ 25 ሺሕ ጫማ ከፍታ ድረስና ወደ ጎን እስከ 60 ኖቲካል ማይልስ (Nautical Miles) ድረስ ያለውን የአየር […]
አዳዲስ የሕክምና ቴክኖሎጂዎች እንደሚተዋወቁበት የሚጠበቀው መድረክ
ኢትዮ ሄልዝ ዓውደ ርዕይን አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጥ ማኅበራዊ አዳዲስ የሕክምና ቴክኖሎጂዎች እንደሚተዋወቁበት የሚጠበቀው መድረክ የማነ ብርሃኑ ቀን: February 16, 2025 በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የሕክምና አገልግሎት ፍላጎት ለማሳካት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችና መፍትሔዎችን የሚያቀርቡ በአሥር አገሮች የሚገኙ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል የተባለው ዘጠነኛው ኢትዮ ሄልዝ ዓውደ ርዕይ ከየካቲት 13 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሚሌኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ […]
የአየር ንብረት ለውጡን ጫና ለመቋቋም
ማኅበራዊ የአየር ንብረት ለውጡን ጫና ለመቋቋም የማነ ብርሃኑ ቀን: February 16, 2025 በመስኖ ልማትና አየር ንብረት ለውጥ ላይ የተሻለ ትብብርና ግንኙነቶችን ለመፍጠር ያስችላል የተባለ ዓለም አቀፍ ‹‹የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባዔ›› ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በዓድዋ ሙዚየም ተካሂዷል፡፡ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በጉባዔው መክፈቻ ወቅት እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን […]
በአሰቃቂው የጋዛ ጦርነት በከባድ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ ሦስት ሕጻናት ታሪክ
16 የካቲት 2025, 07:14 EAT የ11 ዓመት ታዳጊው ዘካሪያ የሚኖረው በጋዛ ነው። በጋዛ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖችን ማየቱን ይናገራል። በመማሪያ ክፍል ውስጥ መገኘት በነበረበት በዚህ ዕድሜው፣ ዘካሪያ በጋዛ ውስጥ ከሚገኙ ጥቂት ሆስፒታሎች በአንዱ፣ አል አቅሳ፣ በበጎ ፈቃደኝነት እየሠራ ነው። በዚህ ሆስፒታል ውስጥ ሙታን እና ቁስለኞችን ከአምቡላንሶች ወደ ሕክምና ክፍሎች ያመላልሳል። በርካታ አምቡላንሶች […]
የጂቡቲው ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ስድስተኛው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆኑ
15 የካቲት 2025 ተቀራራቢ ፉክክር በተካሄደበት ምርጫ የጂቡቲው ዕጩ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ስድስተኛ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ። ከኬንያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጋር ለስድስት ዙር በተካሄደ የምርጫ ሂደት የጂቡቲው ተወካይ አሸናፊ ሆነዋል። የ60 ዓመቱ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ለ20 ዓመታት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሆነው እየሠሩ […]
ፕሮጀክት 2025፡ ቀኝ አክራሪዎች ለትራምፕ ያቀረቡት ጂቡቲ እና ሶማሊላንድን የሚጠቅሰው ፍኖተ ካርታ
16 የካቲት 2025, 07:13 EAT ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ፕሮጀክት 2025 የተሰኘው ቀኝ አክራሪዎች አስተዳደራቸው ሊከተለው ይገባል ብለው የተመኙት እና የነደፉት ፍኖተ ካርታ እየተነሳ ይገኛል። ዘጠኝ መቶ ገጾች ያሉት ይህ ፍኖተ ካርታ የፕሬዚዳንቱን ሥልጣን አስፍቶ የሚያጠናክር እና ወግ አጥባቂ ማኅበራዊ ራዕይን ያነገበ ነው። ፕሮጀክት 2025 የሚያቀርባቸው ሃሳቦች ጽንፈኛ ናቸው በሚል በርካታ ትችቶች መቅረባቸውን […]