የ71 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የቦና ዙሪያ የመኪና አደጋ
January 1, 2025 – VOA Amharic በሲዳማ ክልል ምስራቅ ሲዳማ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ፣ የተከሰተውና የ71 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የመኪና አደጋ ምክኒያት በገላና ወንዝ ላይ ድልድይ የተሠራበት ከፍተኛ መታጠፊያና ቁልቁለት መኾኑን የዐይን እማኞች እና ትራፊክ ፖሊስ ተናገሩ። አካባቢው ተደጋጋሚ አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች እንደሚከሰትበት የአከባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የክልሉ እና ፌዴራል መንግሥታት የመፍትሔ ርምጃ እንዲወስዱ አ… … ሙሉውን ለማየት […]
ኢትዮጵያ በአዲሱ የሰላም አስከባሪ ኃይል መሳተፍ እንዳትከለከል አንድ የሶማሊያ ባለሥልጣን አስጠነቀቁ
January 1, 2025 – VOA Amharic አዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በሰዓታት ውስጥ ሥራውን ይጀምራል፡፡ ታዲያ አንድ የሶማሊያ ክፍለ ግዛት ባለሥልጣን “ኢትዮጵያ በእንግሊዝኛ የምሕጻር መጠሪያው አውሶም በተባለው ተልዕኮ እንዳትሳተፍ መደረግ የለባትም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች የሚገኙበት የጁባላንድ ክፍለ ግዛት ምክትል ፕሬዝደንት መሐሙድ ሰይድ አደን ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ አገ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ […]
አዲስ አበባ ከሚገኙ ከ20 ሺሕ በላይ የሚኾኑ ሕንጻዎች መካከል የአደጋ መከላከያ ያላቸው 42ቱ ብቻ ናቸው ተባለ
January 1, 2025 አዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ በከተማዋ ከሚገኙ ከ20 ሺሕ በላይ የሚኾኑ ሕንጻዎች መካከል የአደጋ መከላከል መስፈርቶችን የሚያሟሉት 42ቱ ብቻ እንደኾኑ መናገሩን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። ሕጋዊ የሕንጻ መስርቶችን ባላሟሉ የተቋማትና የግለሰቦች ሕንጻዎች ላይ ሕጋዊ ርምጃ መውሰድ እጀምራለኹ በማለት ኮሚሽኑ ማስጠንቀቁን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ የከተማዋ አስተዳደር፣ ከአራት ፎቅ በላይ ያላቸው ሕንጻዎች በሙሉ […]
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሜን ወሎ ዞን 77 ሺሕ በግጭትና ድርቅ ሳቢያ ጉዳት ደረሰበት አለ
January 1, 2025 – Konjit Sitotaw የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በቡግና እና ላስታ ወረዳዎች በግጭትና ድርቅ ሳቢያ ጉዳት የደረሰበት ሕዝብ ብዛት 77 ሺሕ መኾኑን አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። ቢሮው፣ ጉዳት ከደረሰበት ሕዝብ ውስጥ 10 ሺሕ ያህሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንደኾኑ ገልጧል። ታጣቂዎች ባካባቢው በጣሉት የእንቅስቃሴ ገደብ ሳቢያ ሕዝቡ ለአገልግሎቶች ተደራሽ ሊኾን እንዳልቻለ፣ የባንክና […]
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የመንግስት ታጣቂዎች ገደለ፤ አቆሰለ
January 1, 2025 – Konjit Sitotaw በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ በምትገኘው ቦዶዴ ከተማ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው አማጺ ቡድን ትናንት ምሽት 12 ሰዓት ገደማ በፈጸመው ጥቃት በትንሹ ሰባት የመንግሥት ታጣቂዎች እንደተገደሉና በርካቶች እንደቆሰሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች ተሰምቷል። የቡድኑ ታጣቂዎች በከተማዋ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ለሰዓታት ካደረጉ የተኩስ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ፣ የሠራዊቱ አባላት አካባቢውን […]
ከትግራይ ክልል በወር 32 ሺሕ ወጣቶች በሕገጥ መንገድ እንየተሰደዱ ነው
January 1, 2025 የትግራይ ክልል የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ፣ በሥራ አጥነት ሳቢያ ከክልሉ በአማካይ በወር 32 ሺሕ ወጣቶች በሕገጥ መንገድ እንየተሰደዱ መኾኑን እንደገለጠ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በሕገወጥ መንገድ ከተሰደዱት ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ቤተሰቦች፣ ልጆቻቸው ባኹኑ ወቅት በሊቢያ በሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ተይዘው በአሰቃቂ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ኹለት ቤተሰቦች፣ ሊቢያ ላይ ለተያዙ ልጆቻቸው ማስለቀቂያ እያንዳንዳቸው […]
48 ሠዓት ሳይሞላው 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል
January 1, 2025 – Konjit Sitotaw 48 ሠዓት ሳይሞላው 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል ነገሩ እየከፋ ነው። ለምሳሌ ዛሬ ብቻ ከ21 በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ “Zamyad” የተባለ መተግበሪያ ላይ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል። በዚህ መተግበሪያ መሰረት ዛሬ ምሽት ከደቂቃዎች በፊት የተከሰተውን ጨምሮ ሁለት እጅግ አደገኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ትላንት 18 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የዛሬውን ከትላንቱ ጋር ስንደመር በአጠቃላይ 48 […]
ምርጫ ቦርድ ሕወሓትን አስጠነቀቀ
January 1, 2025 ምርጫ ቦርድ፣ ሕወሓት እስከ የካቲት 3 ቀን ድረስ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያካሂድ አሳስቧል። ቦርዱ፣ ፓርቲው በሕጉ መሠረት ጉባዔውን ከማድረጉ ከ21ቀናት በፊት ጉባዔውን የሚያካሂድበትን ትክክለኛ ቀን እንዲያሳውቅም ታኅሳስ 17 ቀን በጻፈው ደብዳቤ ማሳሰቡን ገልጧል። ፓርቲው በሕግ የተቀመጠውን ግዴታ በወቅቱ ካልፈጸመ ግን፣ ተገቢውን ውሳኔ እንደሚሰጥ ቦርዱ አስጠንቅቋል። ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ ባለፈው ዓመት መጨረሻ […]
ሩሲያ የጋዝ አቅርቦት የምታቋርጥባት ሞልዶቫ ለኃይል እጥረት ተጋልጣለች
December 31, 2024 – VOA Amharic ሩሲያ የጋዝ አቅርቦቷን ከነገ ጀምሮ እንደምታቋርጥ በማስታወቋ፣ በኃይል እጥረት ስጋት የገባት ሞልዶቫ በከባዱ ክረምት ለሚኖረው የማሞቂያና የመብራት ችግር እየተዘጋጀች ነው፡፡ ለአውሮፓ ኅብረት አባልነት በታጨችው ሞልዶቫ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጠው ንብረትነቱ የሩሲያ መንግሥት የሆነው ጋዝፕሮም ሀገሪቱ የ709 ሚሊዮን ዶላር ውዝፍ የመብራት ዕዳ አለባት በማለቱ ነው፡፡ የተባለውን የዕዳ መጠ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ […]
ህወሓት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ የሚችልበት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን እንደማያውቅ ምርጫ ቦርድ ገለጸ
December 31, 2024 – BBC Amharic ቦርዱ ታኅሣሥ 22/2017 ዓ. ም. በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ህወሓት ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ አሳስቧል።መግለጫው ቦርዱ ለህወሓት ደብዳቤው እስከጻፈበት ቀን ድረስ ፓርቲው ከተመዘገበ በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ቦርዱ አያውቅም ብሏል። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ