በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የቡናና ሻይ ባለሥልጣን የኬላ ሠራተኞች በተጨማሪ በኮንትሮባንዲስቶች ላይ ክትትል እየተደረገ ነው ተባለ

July 12, 2023 – EthiopianReporter.com በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የቡናና ሻይ ባለሥልጣን የኬላ ሠራተኞች በተጨማሪ በኮንትሮባንዲስቶች ላይ ክትትል እየተደረገ ነው ተባለ ከሰሞኑ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ የቡናና ሻይ ባለሥልጣንና የጉምሩክ ኮሚሽን የኬላ ሠራተኞች በተጨማሪ፣ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው በተባሉ ኮንትሮባንዲስቶች ላይ ክትትል እየተደረገ ነው ተባለ፡፡ በጅማ፣ በወለጋ፣ በደሴ፣ በቱሉ ዲምቱ፣ በጎጃም፣ በአቃቂ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡሌ…

የአውሮፓው ፍርድ ቤት ለደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ካስተር ሴሜኒያ ያደላ ውሳኔ አስተላለፈ

11 ሀምሌ 2023 የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት በሴት አትሌቶች ውስጥ መገኘት ካለበት የቴስቴስትሮን መጠን ጋር በተያያዘ የሁለት ጊዜ የ800 ሜትር የኦሊምፒክ ወርቅ አሸናፊዋ ካስተር ሴሜኒያን ደግፎ ውሳኔ አስተላለፈ። በተለየ የጾታ ዕድገት የተወለደችው የ32 ዓመቷ ደቡብ አፍሪካዊት አትሌት፣ በሰውነቷ ውስጥ ያለውን የቴስቴስትሮን መጠን የሚቀንስ መድኃኒት ሳትወስድ እንዳትወዳደር በዓለም አትሌቲክስ ታግዳ ነበር። የሦስት ጊዜ የ800 ሜትር […]

ሰሜን ኮሪያ፤ አሜሪካን ካስፈራራች በኋላ አህጉር ተሻጋሪ ሚሳዔል ተኮሰች

ከ 5 ሰአት በፊት ሰሜን ኮሪያ አህጉር ተሻጋሪ ባለስቲክ ሚሳዔል ሳትተኩስ እንዳልቀረ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ገለጹ። ረዥም ርቀት ተጓዡ ሚሳዔል አንድ ሰዓት ከተጓዘ በኋላ የጃፓን ድንበር አካባቢ ካለ ውሃ ረቡዕ ጠዋት ወድቋል። ፒዮንግያንግ ይህን ሙከራ ያደረገችው አሜሪካ ሰላይ አውሮፕላን ይዛ ወደ ድንበሬ ዘልቃ ገብታለች የሚል ወቀሳ ካቀረበች በኋላ ነው። ሰሜን ኮሪያ ከዚህ በኋላ መሰል አውሮፕላኖችን […]

የአዳዲስ ክልሎች መፈጠር በደቡብ ኢትዮጵያ ሲነሳ ለቆየው ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል?

ከ 6 ሰአት በፊት ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ ተግባራዊ የሆነው ፌደራላዊ የአስተዳደር አወቃቀር 14 ክልሎች ነበሩት። ብዙም ሳይቆይ ደቡብ ክልሎች በአንድ ተጣቃለው፣ የአዲስ አበባ ክልልነት ወደ ከተማ አስተዳደርነት ሲለወጥ ቁጥሩ ወደ 9 ወርዶ ቆይቷል። የክልልነት ጥያቄ ሲነሳበት ከቆየው የደቡብ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሦስት አዳዲስ ክልሎች በመውጣታቸው፣ የፌደራል መንግሥቱ አባል ክልሎች ቁጥር አሁን ወደ […]

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሱዳን ጉዳይ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ግብፅ አቀኑ

ከ 2 ሰአት በፊት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ንግግር ለማስጀመር በግብፅ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ካይሮ አቀኑ። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከግብፁ አቻቸው አብደል ፈታህ አል-ሲሲ በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት የሱዳን ጎረቤት አገራት መሪዎች በሚያደርጉት ውይይት ላይ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ ረፋድ ወደ ካይሮ መጓዛቸውን ገልጸዋል። በሳምንቱ መጀመሪያ […]

አፍሪካን እና አፍሪካውያንን ብዙ እያሳጣቸው ያለው እጅግ ውዱ የአየር ቲኬት ዋጋ

ከ 6 ሰአት በፊት ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በበለጠ በአፍሪካ አህጉር ለአየር ቲኬት ከፍተኛ ገንዘብ ይጠየቃል። በአህጉሪቱ ያሉ ተጓዦች ለአየር ቲኬት እና ለግብር ብዙ ገንዘብ ይከፍላሉ። ከዋጋ አንጻር ወደ አፍሪካዊ አገር ከመብረር ይልቅ ወደ ሌላ አህጉር መብረር የተሻለ ነው። ለመሳያነት ከጀርመኗ መዲና በርሊን ወደ ቱርክ ትልቋ ከተማ ኢስታንቡል መብረር ቢፈልጉ ለአየር ቲኬት በዛ ቢባል የሚጠየቁት 150 […]

የኢራኑን ፕሬዝዳንት ታሪካዊ የተባለ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በኬንያ ጀመሩ

ከ 2 ሰአት በፊት የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ በአፍሪካ ታሪካዊ የተባለ ጉብኝታቸውን ከኬንያ ጀመሩ። ፕሬዝዳንቱ መጀመሪያ ያቀኑት ወደ ኬንያ መዲና ናይሮቢ ነው። ናይሮቢ የሚገኘው ስቴት ሃውስ በተሰኘው የፕሬዝዳንቱ መናገሻ ለኢራኑ ፕሬዝዳንት አቀባበል እንዲሆን በማለት 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል። አልፎም የኢራኑ ፕሬዝዳንት የኬንያ አቻቸው በተገኙበት ወታደራዊ ትዕይንት ተከናውኗል። ራይሲ አሁን ከኬንያው መሪ ዊሊያም ሩቶ ጋር ስለሁለትዮሽ […]

የቡድን 7 ሃገራት ለዩክሬን ልዩ የሆነ የደኅንነት ማዕቀፍ ይፋ ሊያደርጉ ነው

ከ 4 ሰአት በፊት የቡድን 7 ሃገራት ረዥም ጊዜ የሚቆይ ለዩክሬን የሚሆን ልዩ የደኅንነት ማዕቀፍ በኔቶ ስብሰባ ላይ ይፋ ሊያደርጉ ነው። ማዕቀፉ የጦር መሣሪያ፣ ሥልጠና እና የደኅንነት መረጃ ማጋራትን ያካትታል። የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እንዳሉት ስምምነቱ ለፕሬዝደንት ፑቲን “ጠንካራ መልዕክት” ያስተላልፋል። ይህ የሆነው የዩክሬን ፕሬዝደንት ዜሌንስኪ፤ ኔቶ የኪየቭን የመቀላቀል ጥያቄ ችላ ብሏል ብለው […]

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አደጋ እንደተጋረጠበት ተጠቆመ

July 12, 2023 – VOA Amharic በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) መካከል፣ ባለፈው ጥቅምት ፕሪቶርያ ላይ በተፈረመው የሰላም ስምምነት አተገባበር ላይ ታይተዋል የተባሉ ክፍተቶች ካልተፈቱ፣ ሒደቱን አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ። የአፍሪካ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት፣ አደረግኹት ባለው ክትትል፣ በሰላም ስምምነቱ ይዘት እና ስፋት፣ እንዲሁም በትግበራው ሒደት ላይ የተ… … ሙሉውን ለማየት ወይም […]

በወለጋ አምስት ወጣቶች እጃቸው ወደኋላ ታስሮ እና ዓይናቸው ተሸፍኖ ከነሕይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ መጣላቸው ተሰማ

July 11, 2023 ከነሕይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ የተጨመሩ ወጣቶች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ተባለ ሰሞኑን አምስት ወጣቶች እጃቸው ወደኋላ ታስሮ እና ዓይናቸው ተሸፍኖ ከነሕይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ ተጥለው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲዘዋወር ተስተውሏል፡፡ አዲስ ማለዳም ስለ ክስተቱ ባደረገቸው ማጣራት ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎችን ያነጋገረች ሲሆን፤ ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሰዎች ወጣቶቹ ላይ ድርጊቱ የተፈጸመው በምዕራብ ወለጋ […]