በሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ መሪዎች እንዳይገኙ አሜሪካ እያደናቀፈች ነው ስትል ሞስኮ ወቀሰች
ከ 5 ሰአት በፊት ሩሲያ ከምዕራባውያን እየደረሰባት ያለውን ጫና ለመቋቋም የአፍሪካ አገራትን ከጎኗ ለማሳለፍ ጥረት ታደርግበታለች የተባለው የሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ ነገ ይጀምራል። በሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በሚካሄደው በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ 50 የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ግማሽ የሚሆኑት አገራት በስብሰባው የሚወከሉት በመሪዎቻቸው ነው። ነገር ግን ምዕራባውያን በተለይም ባላንጣዋ አሜሪካ የአፍሪካ አገራት መሪዎች […]
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር የተናጠል ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ
ከ 1 ሰአት በፊት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉ እና ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የተናጠል ውይይት እንደሚያደርጉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት አስታወቁ። በአፍሪካ አገራት እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር በሚል ከሐሙስ ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈርቂም ወደ ሩሲያ ማቅናታቸው ተገልጿል። በሴንት ቢተርስበርግ […]
አንድ ጎሳ ባካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የተሳተፉ የሩዋንዳ ከፍተኛ ባለሥልጣን በይፋ ይቅርታ ጠየቁ
ከ 45 ደቂቃዎች በፊት የሩዋንዳ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የመጡበት ጎሳ ባዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ላይ ከታደሙ በኋላ ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ይፋዊ የይቅርታ ጥያቄ አቀረቡ። ኤስፔራንስ ኒይራሳፋሪ የተባሉት የሩዋንዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጎሳቸው ለአባላቱ መሪውን ባስተዋወቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ፀፀት እና ይቅርታ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንቷ […]
የሩሲያ እና የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለዓመታት ዝግ ወደ ነበረችው ሰሜን ኮሪያ ተጓዙ
ከ 2 ሰአት በፊት በሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ የሚመራ ቡድን ከቻይና ልዑክ ጋር በመሆን ዛሬ ሰሜን ኮሪያን ይጎበኛል። የሁለቱ አገራት ልዑካን ሰሜ ኮሪያ የምታከብረውን 70ኛ ዓመት የኮሪያ ጦርነት ፍጻሜ ክብረ በዓል ዝግጅት ላይ ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዝግጅቱ በግዙፍ ወታደራዊ ትዕይንት የሚታጀብ ነው። የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚል ድንበሯን ከዘጋች በኋላ በሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጉብኝት ሲደረግ ይህ […]
አሜሪካ ከቫግነር ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው የማሊ ወታደራዊ መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች
ከ 4 ሰአት በፊት አሜሪካ ከሩሲያው ቅጠረኛ ቡድን ቫግነር ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ሦስት የማሊ ከፍተኛ የጦር መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች። የቅጠረኛ ቡድኑ ተዋጊዎች ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድኖችን ከሚዋጋው የማሊ ጦር ጋር በመሆን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥስተ እየፈጸመ ስለመሆኑ ተገልጿል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የቫግነር ተዋጊዎች እአአ 2021 ማብቂያ ላይ በማሊ ከተሰማሩ በኋላ በአገሪቱ […]
የጋና ፓርላማ የሞት ቅጣትን ለማስቀረት ድምጽ ሰጠ
ከ 5 ሰአት በፊት ጋና የሞት ቅጣትን በማስቀረት ቅጣቱን ያስቀሩ በርካታ የአፍሪካ አገራትን ተቀላቀለች። በአሁኑ ወቅት በጋና 170 ወንድ እና ሴቶች የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የቅጣት ቀናቸውን ሲጠባበቁ ነበር። አሁን የእነዚህ ፍርደኞች ቅጣት ወደ የዕድሜ ልክ እስራት ይቀየራል። በጋና ሕግ ሰውን ለገደለ ተገቢ የሆነው ቅጣት የሞት ፍርድ ነው የሚል ጽኑ አቋም ነበር። ከግድያ በተጨማሪ በአገር ክህደት […]
የደኅንነት ስጋት የገባቸው የግልገል በለስ ከተማ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው አልተመለሱም
July 26, 2023 – VOA Amharic በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ከሦስት ሳምንታት በፊት ተፈጥሮ በነበረው ግጭት፣ ከአካባቢያቸው የተሰደዱ ነዋሪዎች፣ እስከ አሁን አለመመለሳቸውን ገለጹ፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮቹ፣ እስከ አሁን ወደ ቀዬአቸው ያልተመለሱት፣ ከሳምንታት በፊት ጥቃት የፈጸሙባቸው ታጣቂዎች፣ በዚያው በግልገል በለስ ከተማ በመኖራቸው እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ፣ ከአ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ […]
በወልዲያ ባልታወቁ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ
ከ 5 ሰአት በፊት በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ወልዲያ ከተማ ቅዳሜ ምሽት ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የከተማዋ ነዋሪ እና ባለሥልጣን ለቢቢሲ ገለጹ። ባለፈው ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም. ከምሽት ሦስት ሰዓት አንስቶ በታጣቂዎች የተከፈተው ተኩስ ለሰዓታት የቆየ ሲሆን፣ ቢያንስ ለሁለት ሰዎች ሞት እንዲሁም ለሌሎች ሁለት ሰዎች መጎዳት ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል። […]
ኢራቅና ሌሎች ሃገራት በዴንማርክ የተካሄደውን ቁርዓን የማቃጠል ድርጊት ክፉኛ አወገዙ
25 ሀምሌ 2023 ኢራቅ ሌሎች በርካታ ሙስሊሞች የሚኖሩባቸው ሃገራት፤ ‘ዳኒሽ ፓትሪየትስ’ የተባለው ቡድን ሰኞ ዕለት ቁርዓን ማቃጠሉን አወገዙ። ቀኝ ዘመሙ ቡድን ባለፈው አርብም እንዲሁ በተመሳሳይ በፌስቡክ ቀጥታ በተሰራጨ ምስል ኮፐንሃገን ከሚገኘው የኢራቅ ኤምባሲ ፊት ለፊት ቁርዓን አቃጥሏል። ይህን ተከትሎ አንድ ሺህ ገደማ ሰልፈኞች ባግዳድ ወደ ሚገኘው የዴንማርክ ኤምባሲ አቅንተዋል። ባለፈው ሳምንት በስቶክሆልም ቁርዓን እንዲቃጠል ዕቅድ […]
ሩሲያ ከዩክሬን ወደ አፍሪካ ይላክ የነበረውን እህል መተካት እንደምትችል ፑቲን አስታወቁ
July 25, 2023 – BBC Amharic 25 ሀምሌ 2023 ሩሲያ ከዩክሬን ወደ አፍሪካ ይላክ የነበረውን የእህል ወጪ ንግድ መተካት እንደምትችል ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ። ከዩክሬን ወደ አፍሪካም ሆነ ሌሎች አገራት እህል ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በጥቁር ባህር መተላለፍ ይችል ዘንድ ከተደረሰው ስምምነት ሩሲያ መውጣቷን ካሳወቀች በኋላ ነው ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት። ከቤተ መንግሥታቸው ክሬምሊን በወጣው መግለጫ መሰረት አገራቸው ለአፍሪካ […]