በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡ ተሰማ

January 30, 2024 – Konjit Sitotaw  በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነቀምት ካምፓስ ከትላንት ጀምሮ ይህ ዜና እየተጠናቀረ እስካላበት ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ የመማር ማስተማር ሂደት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን ዋዜማ ከምንጮቿ ባሰባሰበችው መረጃ አረጋግጣለች። ዩኒቨርሲቲው ሦስት ካምፓሶች ያሉት ሲኾን፣ ከዋናው ግቢ ነቀምት ካምፓስ በስተቀር በሻምቡና ጊምቢ ካምፓሶች መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት እየተካሄደ እንደኾነ ምንጮች ለዋዜማ ገልጸዋል። በነቀምት ካምፓስ የመማር ማስተማር […]

የፌደራል መንግሥቱ ከጦርነቱ በኋላ ለትግራይ ክልል የተለያዩ ድጎማዎችን ሲያደርግ ራያን ለይቶ ትቶታል

January 30, 2024 – Konjit Sitotaw በራያ የሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ የማንነት ጥያቄያቸው ባለመፈታቱ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን የኮረም ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገብረ እግዚዓብሔር ደረጀ ለዋዜማ ተናግረዋል። ባለፈው ነሐሴ በቅርቡ ሕዝብ ውሳኔ ይደረጋል በሚል ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው፣ ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልተደረገ ተናግረዋል። የፌደራል መንግሥቱ ከጦርነቱ […]

ዕንባ ጠባቂ በአማራ እና ትግራይ የተከሰተው “ረሃብ ወይም ድርቅ” ስለመሆኑ መንግሥት ብያኔ እዲሰጥ ጠየቀ

30 ጥር 2024, 14:28 EAT በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ የጉዳት መጠን ላይ ምልከታ ያደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ መንግሥት ድርቅ አሊያም ረሃብ መከሰቱን በይፋ ብያኔ እንዲሰጥ ጠየቀ። የባለሞያዎች ቡድን ወደ ሁለቱ ክልሎች በመላክ ናሙና ወስዶ የችግሩን ስፋት እንዳጣና የገለጸው ተቋሙ፤ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የደረሰ ጉዳት እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሁኔታን በመዳሰስ የአሰራር ክፍተቶችን […]

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያና ሱማሊያ ውዝግብ ላይ መክሯል።

January 30, 2024 – Konjit Sitotaw  የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ትናንት ምሽት በኢትዮጵያና ሱማሊያ ውዝግብ ላይ መክሯል። ከምክር ቤቱ ስብሰባ ቀደም ብሎ የምክር ቤቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ፈረንሳይ፣ አፍሪካዊያኑን የምክር ቤቱ ተለዋጭ አባላት አልጀሪያን፣ ሞዛምቢክንና ሴራሊዮንን እንዲኹም ጉያናን በጉዳዩ ዙሪያ በዝርዝር ያማከረች ሲኾን፣ አራቱ አገራትም ኢትዮጵያንና ሱማሊያን ማነጋገራቸው ተገልጧል። ዓረብ ሊግና የእስልምና አገራት ካውንስል፣ የሱማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት […]

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ራሱን አጠፋ ወይስ ሰው ገደለው ?! (መላኩ ብርሃኑ )

January 30, 2024 – ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ራሱን አጠፋ ወይስ ሰው ገደለው ?! (መላኩ ብርሃኑ ) ቀኑን ሙሉ ሲያወሩ ቢውሉ መስማት የማይሰለቹኝ አራት ሰዎች አሉ።ስብሃት ገብረእግዚአብሄር፣ ዘነበ ወላ ፣ አብዱ አሊሄጂራ እና ገነነ መኩሪያ። ገነነ ከወሬው በላይ የሚያውቀው ነገር መብዛቱ ነው የሚደንቀኝ።እነዚያን በደቃቃ ፎንቶች ሊብሮ ላይ ይጽፋቸው የነበሩ መሶብ የሚሞሉ የኳስ ወሬዎችን ነፍሱን ይማረውና ታናሽ ወንድሜ […]

በአማራ እና ትግራይ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል ! = መንግስታዊው ተቋም እምባ ጠባቂ

January 30, 2024  በአማራ እና ትግራይ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ምን ያህል ሰዎች ድርቅ ባስተከተለው ረሃብ ሞቱ ? በትግራይ ክልል ፤ በማዕከላዊ ዞን 334 ሰው ከድርቁ ጋር በተያያዘ የሞተ ሲሆን ከዚህ ዞን ውስጥ የተቋሙ ቁጥጥር ቡድን ካየው የአበርገሌ ወረዳ 91 ሰው መሞቱን […]

በርካታ ሰራተኞች በተለይ የአማራ ተወላጆች ከአዲስ አበባ መስተዳደር እንደሚባረሩ ተነግሯል

January 30, 2024 – Konjit Sitotaw  በርካታ የኦሕዴድ አባላት የሆኑ ሰራተኞች ፈተናውን አልተፈተኑም። በቅርቡ የአብይ አሕመድ አገዛዝ በአማራ ተወላጆች ላይ በከፈተው ዘመቻ መሰረት ከአዲስ አበባ መስተዳደር በምዘና ፈተና ስም የአማራ ተወላጆችን ለማባረር በያዘው እቅድ መሰረት በርካቶች እንደሚባረሩ ተሰምቷል። አዲስ አበባ ውስጥ ዲሞግራፊን ለመቀየር በሚል ስር እየተከናወኑ ከሚገኙት ተግባራት አንዱ የአማራ ተወላጆችን ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ማፅዳት ነው። መረጃ […]

በኦሮሚያ ክልል ለኹለተኛ ዙር የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አድማ እየተካሄደ ነው

January 30, 2024 – Konjit Sitotaw  በኦሮሚያ ክልል ለኹለተኛ ዙር የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጠርቶታል በተባለው የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አድማ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ተግባራዊ መኾን መጀመሩን ዋዜማ ካሰባሰበቻቸው መረጃዎች መረዳት ችላለች። በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት ከተማ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ጨምሮ እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ ባንኮች፣ ንግድ ቤቶች፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ዝግ […]

የጉዲሳ ነገር !

January 30, 2024  የዝምድና ታሪክ ፟ በዕውቀቱ ስዩምበምስሉ ላይ ምኒልክና የሸዋ መኳንንት ይታያሉ ፤ በቀኝ በኩል ጫፍ ላይ ቆሞ የሚታየው ድቡልቡል ሰውየ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አያት ደጃዝማች ጉዲሣ ነው፡፡ የዚህን መስፍን ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ባጭሩ የዘገበው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር የነበረው ህሩይ ወልደሥላሴ ነው፡፡ የ”ህይወት ታሪክ“ በሚል ርእስ በ1914 ባሳመው መጽሐፉ፤ ”ወልደሚካኤል“ በሚል ርእስ ሥር […]

ኢላን መስክ በሰው አንጎል ውስጥ የሚገጠም ‘ኒውራሊንክ ቺፕ’ ይፋ አደረገ

ከ 5 ሰአት በፊት የቢሊየነሩ የቴክኖሎጂ ሰው ኢላን መስክ፤ ኒውራሊንክ የተባለው ኩባንያው ሰዎች አንጎል ውስጥ የሚገጠም ገመድ አልባ ቺፕ መሥራቱን ይፋ አድርጓል። መስክ እንዳለው ይህ ቺፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ላይ መኩራ ተደርጎበታል። የመጀመሪያ ዙር ውጤቶች እንደሚያሳዩት የኒውሮን መጠንን እና የነርቭ ‘ኢምፐልስ’ ከፍ ማለት የተስተዋለ ሲሆን ታካሚው እያገገመ ይገኛል። የኩባንያው ዓላማ የሰው ልጅን አእምሮ ከኮምፒውተር ማስተሳሰር […]