የገደሉት ሕዝብን ብቻ ሳይሆን!!የኢትይጵያዊነት ብሔራዊ ማንነትንም ነው!!

Mengistu Musie  የኢትይጵያዊነት ብሔራዊ ማንነትንም ነው!! ============================== የሐገር ሉአላዊነትን፤ ዳርድንበር ሀገራዊ አንድነት የማይገባቸው የመንደር ዘረኛ መሪወች ለአለፉት 35 አመታት በእነሱ ይሁንታ ትልቅ የባህር በር አሳልፈው ሰጡ። ሁለት ወንድማማች/እህታማማች ሕዝብን አለያዩ። ዞረው ተመልሰው ባነሱት ጦርነት 100,000 ሽሆችን የአንድ ሐገር ሕዝባችንን አጨራረሱ። ሐገሬ ብሎ ይኖር የነበረውን ዜጋ አይደለህም በሚል ጨርቅ ማቁን ሳይዝ ቤት ንብረቱን ትቶ ተገዶ እንዲሄድ […]

ፕሮፌሰር በዩ ሲታወሱ

እኔ የምለዉ ፕሮፌሰር በዩ ሲታወሱ አንባቢ ቀን: September 22, 2024 በአምባቸው ወረታ (ዶ/ር) በዩ ብዩ የምጠራቸው የዛሬ ባለታሪክ በደንብ ቀርቤ የማውቃቸው  ከ2007 ጀምሮ ነው። እሳቸው  የዶክትሬት ዲግሪ (Ph.D) አማካሪዬና መምህሬ ሆነው ብቅ አሉ። በዩ ተማሪን ማቅረብ፣ ማዳመጥና ጊዜ መስጠት የሚችሉ ሰው ነበሩ። እንደ ሌሎቹ ተማሪዎች  ከፍተኛ ዝግጅት አድርጌ አንብቤ ለጨዋታ የማልቀርባቸው እኔ ብቻ  ነበርኩኝ ብዬ […]

የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የብር ዋጋ መውረድ (የመጨረሻ ክፍል)

እኔ የምለዉ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የብር ዋጋ መውረድ (የመጨረሻ ክፍል) አንባቢ ቀን: September 22, 2024 በነጋድራስ ካሳ ባለፉት ሁለት ክፍሎች የአገራችን የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የብር ዋጋ መዳከም ምክንያትና መንስዔዎችን በመመልከት፣ መንግሥት (በብሔራዊ ባንክ) አሁን የወሰደው የምንዛሪን ግብይት ተንሳፋፊ (Floating) ማድረግ ጥቅሙንና ጉዳቱን ከሞላ ጎደል ለመመልከት ሞክረናል፡፡ ሲጠቃለልም ተንሳፋፊ ግብይት ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ የውጭ […]

ሳይቦርቁ የጨረጨሱት ‹‹ሉዓላዊነት›› እና ‹‹የራስን ዕድል በራስ ወሳኝነት››

ተሟገት ሳይቦርቁ የጨረጨሱት ‹‹ሉዓላዊነት›› እና ‹‹የራስን ዕድል በራስ ወሳኝነት›› አንባቢ ቀን: September 22, 2024 በበቀለ ሹሜ ባለፈው ሳምንት ጽሑፌ የምንገኝበት ዘመን እንኳን ደሃ አገሮች የደረጁትም ለብቻቸው ተገድበው መኖር የማይችሉበት ዘመን እንደሆነ፣ የአገሮች ዕጣ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እርስ በርስ የሚወሳሰን እየሆነ እንደመጣ፣ የአንድ አገር የውስጥ ጉዳይ የጎረቤትም የአካባቢም እንዲያም ሲል የዓለም ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል፣ ይህ ሁሉ […]

የልማት ውጥኑ ከእኩል ተጠቃሚነት ጋር ይጣጣም!

September 22, 2024 ርዕሰ አንቀጽ ኢትዮጵያ በዓለም ፊት የሚያኮሯት አንፀባራቂ ታሪኮች ባለቤት ብትሆንም፣ በፀረ ኮሎኒያሊስት ትግል ተወዳዳሪ ባይገኝላትም፣ በተለያዩ ጊዜያት ሊወሯት የመጡትን በሙሉ አሳፍራ በመመለስ ብትታወቅም፣ ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ጥቁር ሕዝቦች ተምሳሌት የሆነችና ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መፈጠር መነሻ ምክንያት መሆኗ ቢታወቅም፣ ይህንን የተከበረና ኩሩ ሕዝብ አንገት ሲያስደፋ የኖረው ድህነት ግን አንደኛው የጨለመ ገጽታዋ ማሳያ ነበር፣ […]

‹‹ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለመጠቀም መወሰን ጥልቅ ጥናትና ትልቅ ዕቅድ ያስፈልጋል›› አቶ በረከት ተስፋዬ፣ የኢነርጂ ዘርፍ ባለሙያና አማካሪ

ሲሳይ ሳህሉ September 22, 2024 ቆይታ አብዛኛውን ጊዜ በግል ሥራ በመሰማራት፣ ኮሌጅ በባለቤትነት በማስተዳደር፣ በኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ ባለሙያነትና በማማከር ሥራ ይታወቃሉ፡፡ ካለፉት አሥር ዓመታት ወዲህ ደግሞ በኢነርጂና በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ዘርፍ በግል ኩባንያዎች ውስጥ በማርኬቲንግና በቢዝነስ ልማት ኃላፊነት ሠርተዋል፡፡ በአንድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ኩባንያ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያና በአፍሪካ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዙሪያ ያሉ ሁኔታዎችን በመከታተል ጥናት በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሚጀምረው የሁለተኛ ዲግሪ የኤሌክትሪክ ሞቢሊቲ ፕሮግራም በአማካሪነት አገልግለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በፀሐይ ኢነርጂና በማገዶ ቆጣቢ ፕሮጀክት ለጀርመን ልማት ድርጅት (ጂአይዜድ) አማካሪ በመሆን እየሠሩ ናቸው፡፡ አቶ በረከት ተስፋዬ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ ወደ […]

‹‹ክርክሩና ውዝግቡ ለስፖርቱም ሆነ ለአትሌቱ መሠረታዊ ችግር በሆነው የማዘውተሪያና የትራክ ጉዳይ አለመሆኑ አስገርሞኛል››

በፓሪስ ኦሊምፒክ በ10,000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ያስመዘገበው በሪሁ አረጋዊ ሽልማቱን ሲቀበል (ፎቶ ኦሊምፒክ ኮሚቴ) ስፖርት ‹‹ክርክሩና ውዝግቡ ለስፖርቱም ሆነ ለአትሌቱ መሠረታዊ ችግር በሆነው የማዘውተሪያና የትራክ ጉዳይ አለመሆኑ… ደረጀ ጠገናው ቀን: September 22, 2024 ብሔራዊ አትሌቶች ኦሊምፒክና የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመጣ ቁጥር፣ በተለይም በአመራሮች መካከል የሚስተዋለው ውዝግብ ሕግና ሥርዓትን ባከበረ መልኩ፣ መፍትሔ ሊበጅለት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ብሔራዊ […]

ያልተተኮረው የሥዕልና ሠዓሊያን ተግዳሮት

ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ ኪንና ባህል ያልተተኮረው የሥዕልና ሠዓሊያን ተግዳሮት የማነ ብርሃኑ ቀን: September 22, 2024 ጥልቅ መልዕክቶች ከሚተላለፉባቸው የጥበብ ዘርፎች አንዱ ሥዕል ነው፡፡ በሥዕል ጥበብ ኑሯችን ይቀልማል፡፡ በብሩሽ፣ ሸራና ወረቀት ላይ ሕይወታችን ይኳላል፡፡ ዕንባችን እንደጅረት ይፈሳል፣ ሳቃችንም እንደ አደይ እንደ መፀው (አበባ) ይደምቃል፡፡ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ድሎቻችንን እንዲሁም ውድቀታችንን ከሚነግሩን የሥነ ጥበብ ውጤቶች መካከል ሥዕልን […]

ትዝታዋ የቀረው የፒያሳዋ ዳላስ

ዝንቅ ትዝታዋ የቀረው የፒያሳዋ ዳላስ አንባቢ ቀን: September 22, 2024 ፍቅረኛህን ‹‹ማሀሙድ ጋር ጠብቂኝ›› ስትላት ተሳስታ ማዶ ተሻግራ ከጠበቀችህ እድለኛ ናት፡፡ ካንተ በላይ የሚያስደስቷትን ሙዚቃዎች እየሰማች ነው ማለት ነው፡፡ ከዳላስ ሙዚቃ ቤት፡፡ ይህ ቤት የየመን ዝርያ ባላቸው ሐበሾች የተያዘ ነው፡፡ ከፒያሳ ፍቅር እንዲይዝህ ከሚያስችሉ አዚሞች አንዱ ነው፤ ዳላስ፡፡ በማለዳ ፒያሳ ከመጣህ በነ‹‹ያኒ›› ዜማ ትታደሳለህ፡፡ በሩቅ […]

‹‹ሄቦ›› የየም የዘመን መለወጫ

ዝንቅ ‹‹ሄቦ›› የየም የዘመን መለወጫ በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: September 22, 2024 ሄቦ ከጭጋግና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ምዕራፍ መሻገሪያ የም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡ በዓሉ የአዲስ ዓመት መባቻ በመሆኑ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ተወላጆች ከወላጆቻቸው ጋር የሚገናኙበት እንደሆነ ይነገራል፡፡ የዘንድሮው የሄቦ በዓል መስከረም 20 እና 21 ቀን 2017 ዓ.ም. በዞኑ ዋና ከተማ ሳጃ […]