የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሜን ወሎ ዞን 77 ሺሕ በግጭትና ድርቅ ሳቢያ ጉዳት ደረሰበት አለ

January 1, 2025 – Konjit Sitotaw  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በቡግና እና ላስታ ወረዳዎች በግጭትና ድርቅ ሳቢያ ጉዳት የደረሰበት ሕዝብ ብዛት 77 ሺሕ መኾኑን አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። ቢሮው፣ ጉዳት ከደረሰበት ሕዝብ ውስጥ 10 ሺሕ ያህሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንደኾኑ ገልጧል። ታጣቂዎች ባካባቢው በጣሉት የእንቅስቃሴ ገደብ ሳቢያ ሕዝቡ ለአገልግሎቶች ተደራሽ ሊኾን እንዳልቻለ፣ የባንክና […]

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የመንግስት ታጣቂዎች ገደለ፤ አቆሰለ

January 1, 2025 – Konjit Sitotaw  በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ በምትገኘው ቦዶዴ ከተማ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው አማጺ ቡድን ትናንት ምሽት 12 ሰዓት ገደማ በፈጸመው ጥቃት በትንሹ ሰባት የመንግሥት ታጣቂዎች እንደተገደሉና በርካቶች እንደቆሰሉ  ከአካባቢው ነዋሪዎች ተሰምቷል። የቡድኑ ታጣቂዎች በከተማዋ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ለሰዓታት ካደረጉ የተኩስ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ፣ የሠራዊቱ አባላት አካባቢውን […]

ከትግራይ ክልል በወር 32 ሺሕ ወጣቶች በሕገጥ መንገድ እንየተሰደዱ ነው

January 1, 2025  የትግራይ ክልል የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ፣ በሥራ አጥነት ሳቢያ ከክልሉ በአማካይ በወር 32 ሺሕ ወጣቶች በሕገጥ መንገድ እንየተሰደዱ መኾኑን እንደገለጠ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በሕገወጥ መንገድ ከተሰደዱት ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ቤተሰቦች፣ ልጆቻቸው ባኹኑ ወቅት በሊቢያ በሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ተይዘው በአሰቃቂ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ኹለት ቤተሰቦች፣ ሊቢያ ላይ ለተያዙ ልጆቻቸው ማስለቀቂያ እያንዳንዳቸው […]

48 ሠዓት ሳይሞላው 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል

January 1, 2025 – Konjit Sitotaw  48 ሠዓት ሳይሞላው 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል ነገሩ እየከፋ ነው። ለምሳሌ ዛሬ ብቻ ከ21 በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ “Zamyad” የተባለ መተግበሪያ ላይ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል። በዚህ መተግበሪያ መሰረት ዛሬ ምሽት ከደቂቃዎች በፊት የተከሰተውን ጨምሮ ሁለት እጅግ አደገኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ትላንት 18 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የዛሬውን ከትላንቱ ጋር ስንደመር በአጠቃላይ 48 […]

ምርጫ ቦርድ ሕወሓትን አስጠነቀቀ

January 1, 2025  ምርጫ ቦርድ፣ ሕወሓት እስከ የካቲት 3 ቀን ድረስ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያካሂድ አሳስቧል። ቦርዱ፣ ፓርቲው በሕጉ መሠረት ጉባዔውን ከማድረጉ ከ21ቀናት በፊት ጉባዔውን የሚያካሂድበትን ትክክለኛ ቀን እንዲያሳውቅም ታኅሳስ 17 ቀን በጻፈው ደብዳቤ ማሳሰቡን ገልጧል። ፓርቲው በሕግ የተቀመጠውን ግዴታ በወቅቱ ካልፈጸመ ግን፣ ተገቢውን ውሳኔ እንደሚሰጥ ቦርዱ አስጠንቅቋል። ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ ባለፈው ዓመት መጨረሻ […]

ሩሲያ የጋዝ አቅርቦት የምታቋርጥባት ሞልዶቫ ለኃይል እጥረት ተጋልጣለች

December 31, 2024 – VOA Amharic  ሩሲያ የጋዝ አቅርቦቷን ከነገ ጀምሮ እንደምታቋርጥ በማስታወቋ፣ በኃይል እጥረት ስጋት የገባት  ሞልዶቫ በከባዱ ክረምት ለሚኖረው የማሞቂያና የመብራት ችግር  እየተዘጋጀች ነው፡፡ ለአውሮፓ ኅብረት አባልነት በታጨችው ሞልዶቫ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጠው ንብረትነቱ የሩሲያ መንግሥት የሆነው ጋዝፕሮም ሀገሪቱ የ709 ሚሊዮን ዶላር ውዝፍ የመብራት ዕዳ አለባት በማለቱ ነው፡፡ የተባለውን የዕዳ መጠ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ […]

ህወሓት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ የሚችልበት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን እንደማያውቅ ምርጫ ቦርድ ገለጸ

December 31, 2024 – BBC Amharic  ቦርዱ ታኅሣሥ 22/2017 ዓ. ም. በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ህወሓት ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ አሳስቧል።መግለጫው ቦርዱ ለህወሓት ደብዳቤው እስከጻፈበት ቀን ድረስ ፓርቲው ከተመዘገበ በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ቦርዱ አያውቅም ብሏል። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በመላው ዓለም በድምቀት ተከበረ

ከ 8 ሰአት በፊት አዲሱ የፈረንጆች ዓመት 2025 በመላው ዓለም በድምቀት ተከብሯል። ኪሪባቲ የተባለችው ደሴት 2025ን በመቀበል ከዓለም ቀዳሚዋ ስትሆን ማክሰኞ ከሰዓት ነው አዲሱን ዓመት ያከበረችው። ቀጥሎ ኒው ዚላንድ እና የተወሰኑ የአውስትራሊያ ክፍሎች በዓሉን አክብረዋል። ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሕንድ እና ስሪ ላንካ በሰዓት አቆጣጠራቸው ቅደም ተከትል ከሌሎች ሀገራት ቀደም ብለው በዓሉን ያከበሩ ሀገራት ናቸው። አዲሱን […]

ኢላን መስክ በማኅበራዊ ሚድያ ስሙን ወደ ኬኪየስ ማክሲመስ ቀየረ

ከ 6 ሰአት በፊት የዓለማችን ቱጃሩ ሰው ኢላን መስክ የማኅበራዊ ሚድያ ስሙን ቀየረ። መስክ ገዝቶ ንብረቱ ባደረገው የቀድሞው ትዊተር የአሁኑ ኤክስ ማኅበራዊ ገፅ ስሙን ወደ “ኬኪየስ ማክሲመስ” መቀየሩን አስታውቋል። ጉምቱው የቴክኖሎጂ ሰው መስክ የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ሰው ነው። ኢላን መስክ የማኅበራዊ ሚድያ ስሙን ለምን እንደቀየረ እስካሁን ማብራሪያ አልሰጠም። መስክ ስሙን ብቻ ሳይሆን ‘ፕሮፋይል’ […]

ጂሚ ካርተር ለመንግሥቱ ኃይለማርያም የላኩት ደብዳቤ

ከ 9 ሰአት በፊት “በቅርቡ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ግጭት አስመልክቶ በተናገርኩት ንግግር የተፈጠረው አለመግባባት እጅግ አስገርሞኛል” ይላል ጂሚ ካርተር ከ46 ዓመታት በፊት ለቀድሞው ፕሬዝደንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የላኩት ደብዳቤ። ጥር 19/1978 ፕሬዝደንት ጂሚ ለሊቀ መንበር መንግሥቱ የላኩት ደብዳቤ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነታቸው በሻከረበት ወቅት የተፃፈ ነው። ደብዳቤው ‘ኦፊስ ኦፍ ዘ ሂስቶሪያን’ የተሰኘው የአሜሪካ መንግሥት ታሪክ […]