ታንዛኒያ ውስጥ የተደፈረው ኬንያዊው ተሟጋች “ለመኖር እየታገልኩ ነው” አለ
ከ 5 ሰአት በፊት ማስጠንቀቂያ፦ ይህ ጽሑፍ አንዳንድ አንባቢዎችን ሊረብሹ የሚችሉ ዝርዝሮችን ይዟል። በርካቶች የኬንያ መንግሥትን እና ባለሥልጣናትን በመገዳደር በደፋርነቱ የሚያውቁት ኬንያዊው ተሟጋች ቦኒፌስ ምዋንጊ በታንዛኒያ ወሲባዊ ስቅይቶች እንደተፈጸሙበት ለቢቢሲ ተናገረ። በታንዛኒያ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በደረሰበት እንግልት እና ወሲባዊ ጥቃቶች “ለመኖር እየታገልኩ ነው” ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። “የተለያያዩ ቁሶችን ጭምር በመጠቀም አጸያፊ ተግባር መፈጸማቸው […]
በአገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችንና የሕክምና መሣሪያዎችን ከውጭ መግዛት በሕግ ተከለከለ
ማኅበራዊበአገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችንና የሕክምና መሣሪያዎችን ከውጭ መግዛት በሕግ ተከለከለ ፅዮን ታደሰ ቀን: June 4, 2025 መድኃኒቶች ወይም የሕክምና መሣሪያዎች በአገር ውስጥ አምራቾች የሚመረቱ ከሆነ በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ከውጭ ግዥ መፈጸም ተከለከለ፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በማዕከል የሚፈጸሙ የመድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች የግዥ አፈጻጸም መመርያ ይፋ አድርጓል፡፡ ከትናንት ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. […]
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ
ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነርና አቶ አህመድ ሺዴ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር በፎረሙ ላይ በተሳተፉበት ወቅት ቢዝነስ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ ፅዮን ታደሰ ቀን: June 4, 2025 የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍን በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሊደረግ መሆኑን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ለሁለት ቀናት የተዘጋጀው የኢትዮ ቤልጂየም ቢዝነስ […]
አሠሪዎች ሠራተኞችና የክልል መንግሥታት መዋጮ የሚያደርጉበት ተጠባቂው የቤቶች ፈንድ
ቢዝነስ አሠሪዎች ሠራተኞችና የክልል መንግሥታት መዋጮ የሚያደርጉበት ተጠባቂው የቤቶች ፈንድ ዳዊት ታዬ ቀን: June 4, 2025 የመኖሪያ ቤቶች ግንባታና ዕድሳት ሊውል የሚችል የረዥም ጊዜ ብድር አገልግሎት ለመስጠት ያስችላሉ የተባሉ ሁለት ተቋማትን ለማቋቋም የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሊመከርበት እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ በቅርቡም ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ የሚጠበቀው ረቂቅ የቤቶች ኮርፖሬሽንና የቤቶች ፈንድን ለማቋቋም የሚያስችል ነው፡፡ […]
የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕግ አግባብን የተከተለ ፍተሻና ብርበራ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ
ዜና የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕግ አግባብን የተከተለ ፍተሻና ብርበራ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: June 4, 2025 የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ማክሰኞ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሕግ አግባብን የተከተለ ፍተሻና ብርበራ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ። ኅብረተሰቡ ለፀጥታው ሥራ ስኬታማነት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፣ […]
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ባለሥልጣናት መካከል እየተጠናከረ የመጣው የቃላት ጦርነት
ከ 2 ሰአት በፊት ከዕለት ዕለት የግንኙነታቸው መበላሸት ይፋ የወጣው ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ቀጥተኛ ባለሆነ መንገድ በነገር እየተጎነታተሉ፣ አንዳቸው ሌላቸውን እየወቀሱ እና እየከሰሱ ይገኛሉ። የአገራቱ መንግሥታት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተለያዩ አጋጣሚዎች በተዘዋዋሪ የሚያቀርቡት ክስ እና የቃላት ምልልስ ከዕለት ዕለት እየጠነከረ የመጣ ይመስላል። ማክሰኞ ግንቦት 26/2017 ዓ.ም. የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር በይፋዊ የኤክስ ገጻቸው ላይ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር […]
መስክ የፕሬዝደንት ትራምፕ የግብር ሕግን “አሳፋሪ እና አስጸያፊ” ሲል ኮነነ
ከ 7 ሰአት በፊት ኢሎን መስክ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን የግብር እና የወጪ ሕግ “አሳፋሪ እና አስጸያፊ” ሲል ኮነነው። የባለብዙ ትሪሊዮን ዶላር የታክስ እፎይታ እና ተጨማሪ የመከላከያ ወጪዎችን ጨምሮ የአሜሪካ መንግሥት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲበደር የሚፈቅደው ይህ ሕግ በግንቦት ወር በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል። ማክሰኞ ዕለት በኤክስ ገጹ ላይ በለጠፈው ጽሑፍ ላይ “ይህንን ሕግ ለማጽደቅ ድምጻቸውን የሰጡ […]
የእስራኤል ጦር በጋዛ የእርዳታ ማከፋፈያዎች “የጦርነት ቀጠና” ናቸው ብሎ ዘጋ
ከ 6 ሰአት በፊት የእስራኤል ጦር በጋዛ ወደ እርዳታ ማከፋፈያዎች የሚወስዱ መንገዶች እንደ “የጦርነት ቀጠና” ተደርገው እንደሚወሰዱ በማስጠንቀቅ ረቡዕ ዕለት እንደሚዘጉ አስታወቀ። ባለፈው ሳምንት ስራ የጀመረው እና በአሜሪካ እና እስራኤል የሚደገፈው አወዛጋቢው የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን የማዕከላቱን “አደረጃጀት እና ቅልጥፍና መጨመር የሚያስችሉ ማሻሻያ ስራዎች” ለመስራት በሚል እንደሚዘጋ ተናግሯል። ድርጅቱ እሰራቸዋለሁ ካላቸው የማሻሻያ ስራዎች በተጨማሪ የእስራኤል መከላከያ […]
የቻይና ዜጎች ‘አደገኛ በሽታ አምጭ ተህዋሲያን’ ወደ አሜሪካ በማስገባት ተከሰሱ
ከ 5 ሰአት በፊት ሁለት የቻይና ዜጎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ‘አደገኛ የስነ ሕይወት ተህዋሲያን’ ያሉትን ፈንገስ ወደ አሜሪካ በማስገባት ክስ ተመሰረተባቸው። ያንኩንግ ጂያን እና ዙያንግ ሊዊ የተባሉ ሴት እና ወንድ ቻይናዊያን በማሴር፣ ሕገ ወጥ እቃዎችን በማስገባት፣ ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ እንዲሁም ቪዛ በማጭበርበር መክሰሱን የሚቺገን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ አስታውቋል። የ34 ዓመቱ ዙያንግ ሊዊ ፈንገሱን በዲትሮይት […]
ካናዳ ጥገኝነት ጠያቂዎችን የሚገድብ ረቂቅ ሕግ አቀረበች
ከ 4 ሰአት በፊት የካናዳ መንግሥት የጥገኝነት ጠያቂዎችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ እና ለባለስልጣናቱ የበለጠ ስልጣን የሚሰጥ ረቂቅ ሕግ አቀረበ። የካናዳ የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ሊና ዲያብ ጠንካራ የድንበር ቁጥጥር የአገሪቱን የኢሚግሬሽን ስርዓት በማሳደግ፤ የተደራጀ ወንጀልን እና በሕገ ወጥ መንገድ የሚገቡ አደንዛዥ እፆችን እነ የጦር መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር ያለመ ነው ብለዋል። ሕጉ ካናዳ ከአሜሪካ ጋር የምትጋራውን ድንበር ለመቆጣጠር ለፖሊስ […]